ዶ/ር ሀና ሊሻን- የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም

ዶ/ር ሀና ሊሻን- የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም

Share

Consultant pediatrician and Pediatric Rheumatologist at Tikur Anbessa Specialized Hospital

የህፃናት ቁርጥማት ወይም የመገጣጠምያ ብግነት (Juvenile idiopathic arthritis- JIA) //NEW LIFE// 12/08/2025

Had a talk about Juvenile ideopathic arthritis ( JIA) with EBS. We have to advocate for children with JIA as kids have arthritis too!!! Have a look.

ከ EBS ጋር ሥለ ሕፃናት ቁርጥማት እና የ መገጣጠምያ ብግነት ቆይታ ነበረን. በሽታው ብዙ ሥለማይታወቅ ለህብረተሠቡ በዚህ መልክ ማድረስ ግድ ይለናል. ይመልከቱ. ይጠቅሞታል!!!

የህፃናት ቁርጥማት ወይም የመገጣጠምያ ብግነት (Juvenile idiopathic arthritis- JIA) //NEW LIFE// Children need healthy joints to run, jump, and play freely. However, for unknown reasons, an autoimmune disease called juvenile idiopathic arthritis (JIA) ca...

Photos from Arthritis Kids South Africa's post 16/03/2024
Photos from ዶ/ር ሀና ሊሻን- የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም's post 28/10/2023

It was a pleasure to participate in this international conference with world-renowned experts in FOP, Dr. Fred Kaplan, Prof. Chris Scott, and the entire team. I am delighted to have collaborated with the FOP AFRICA/TIN SOLDIERS team, Vanda Harries and the whole team in editing and reviewing the Amharic edition of the FOP parents guide for Ethiopian parents of FOP patients!
I appreciate the acknowledgement. I will also keep my vow to become an advocate for these patients and all those with rheumatologic diseases !!!

21/10/2023

To your surprise, Ethiopia doesn't have a formally trained pediatric rheumatologist. Pediatric rheumatology is a field of study that focuses on joints, tendons, ligaments, bones, muscles, and the immune system of children. It is a growing field of science that, compared to the other subspecialties, has fewer sub-specialists all over the world. Thanks to , I am humbled to have started this journey to become one of them. As part of the education, expanding your knowledge and enhancing your personal and professional development through conferences is important.

08/09/2023

🤔🤔🤔ልጄ ትኩሳት አለዉ። ጆሮውን እየያዘ ማልቀስ ከጀመረም 2 ቀኑ ነው። ምን ይሆን⁉️⁉️
የወላጅ ጥያቄ

አዘጋጅ፦ ዶ/ር ሀና ሊሻን ( በ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ ህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር).
fb.me/DrHannaLishanPediatrician

✅የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media) የመሀለኛው የጆሮ ክፍል በኢንፌክሽን ሲጠቃ ነው፡፡

✅ኢንፌክሽን በአብዛኛው በባክቴሪያ እና በ ቫይረስ ምክንያት ሊከሰት ይችላል

🤔🤔🤔 አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ⁉️⁉️

👉 አለርጂ (allergy)
👉 ጉንፋን
👉 የሳይነስ ኢንፌክሽን (sinus infection)
👉 ከ6 ወር እስከ 3 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሆኑ ህጻናት
👉 ለተበከለ አየር መጋለጥ
👉 በተደጋጋሚ ለሲጋራ ጭስ መጋለጥ
👉 ቀዝቃዛ የአየር ንብረት

🤔🤔🤔ምልክቶቹስ ምን ምን ናቸው⁉️⁉️

👉 ትኩሳት
👉ማስመለስ
👉ተቅማጥ
👉ማልቀስ ከወትሮ በተለየ
👉 መነጫነጭ
👉እንቅልፍ ማጣት
👉የጆሮ ህመም
👉 ራስ ምታት
👉 ከጆሮ ፈሳሽ መውጣት
👉 የመስማት ችሎታ መቀነስ
👉 የሰውነት ሚዛንን መጠበቅ አለመቻል

🤔🤔🤔 ካልታከመ ሊያስከትል ሚችለው መጥፎ ችግር አለ⁉️⁉️

🚫 ማጂራት ገትር (meningitis)

🤔🤔🤔 ህክምናውስ⁉️⁉️

👉 ማንኛውንም ኢንፌክሽን ሲኖር ቶሎ መታከም በተለይ የመተንፈሻ አካል ህመም ሲኖር
👉 አጋላጭ ሁኔታዎችን በተቻለ መጠን መቀነስ
👉 የተገለፁት የህመም ምልክቶች ሲኖሩ ቶሎ ወደ ህክምና መውሰድ

መልካም ጊዜ!

📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌

ለተለያዩ የልጆች መረጃዎች ከታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን እና Facebook- like....telegram- join....በማድረግ ይከታተሉን
ለወዳጅ ዘመዶም share በማድረግ ያድርሱ 🔊🔊🔈

Facebook=

fb.me/DrHannaLishanPediatrician

Telegram=

t.me/Drhannalishanpediatrician

ዶ/ር ሀና ሊሻን- የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም Consultant pediatrician and Pediatric Rheumatologist at Tikur Anbessa Specialized Hospital

ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ በድንገት ሰርፕራይዝ አደረጋት!#church #mezmur #new #tewodros_yosef #በድንኳኔ 05/08/2023

ምን አይነት መባረክ ነው
ፈጣሪ ካሰበበት ያድርስሽ የኔ ቆንጆ !!!
እሼ ዘመንህ ይባረክ!!!

ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ በድንገት ሰርፕራይዝ አደረጋት!#church #mezmur #new #tewodros_yosef #በድንኳኔ ህጻን ትንሳኤ ተስፋዬ የ14 አመት ልጅ ስትሆን እናትዋ በወሊድ ጊዜ ባጋጠማት ህመም ምክንያት ሙሉ የሰውነት አካሉዋን ማንቀሳቀስ እና እንደፈለገች ማውራት የማትችል ብትሆንም ለወደፊት ት.....

24/07/2023

👨‍👦አንድ አባት ልጄ ትምህርት በጀመረ በ 3 ቀኑ ምግብ አልበላ አለኝ።አንገቴ ውስጥም ያመኛል አለኝ እና ቶንሲል ሳይዘው አይቀርም እባክሽ እይልኝ አለኝ👨‍👦

🤔🤔ቶንሲል ለመሆኑ ምንድነው?

👅በ አፋችን የኃላ ግድግዳ በቀኝ እና በግራ በኩል የሚቀመጡ ጠቃሚ እና ተፈጥሮአዊ እጢዎች ናቸው።

🤔🤔የቶንሲል ጥቅም ምንድን ነው?

👉በአፍና በአፍንጫ የሚገቡ ተዋህስያንን አጣርቶ ወደ ሳንባ እንዳይገቡ ማስቀረት።
👉 የ በሽታ መከላከያ ወታደሮችን (antibodies) ማምረት
👉 ባጠቃላይ የሰውነትን በርን ከጠላት መከላከል ነው ስራው‼️

⁉️ ቶንሲል እና እንጥል አንድ ናቸው⁉️

❌ አይደሉም

👉 እንጥል (Uvula) 👅 በ አፋችን የኃላ ግድግዳ መሀል ላንቃ ላይ የሚንጠለጠል አካል ነው።

✍ ታድያ የቶንሲል ኢንፌክሽን/ ህመም (tonsillitis) ምንድነው?

👉ከ አቅም በላይ በሆነ ባክቴርያ ወይም ቫይረስ መወረር እና የመቆጣት ባህሪ ማሳየት ነው።

🤔🤔🤔የህመሙ ምልክቶችስ ???

👉ትኩሳት ፣
👉ለመዋጥ መቸገርህመም
👉 የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉 ራስ ምታት ፣
👉የአፍ መጥፎ ሽታ ፣
👉የአንገት ንፍፊት እብጠት ፣
👉ማንኮራፋት ፣
👉 አልፎ አልፎ የ ጆሮ
👉አልፎ አልፎ የድምጽ መቀየር ( መነፋነፍ)

❌በተለምዶ የቶንሲል ህመም ሲኖር ቦታው ላይ በሚኖሩ ለውጦች/ የ ሰዉነት መቆጣት ምክንያት እንጥል ወረደ በሚል ሰበብ እንጥልን ማስቧጠጥም ሆነ ማስቆረጥ በፍፁም አይመከርም ‼️

⁉️ ህፃን ልጅ እንዴት ሊይዘው ይችላል⁉️

👉ተመሳሳይ ችግር ካለበት ልጅ በትንፋሽ ጠብታ ወይንም በትንፋሽ ጠብታ በተበከለ እጅ ንክኪ

⁉️ በመጨረሻም ስለዚህ ለልጄ ምን ላርግለት አለኝ ⁉️

👉የህመም እና ትኩሳት ማስታገሻ መድሃኒት
👉 እንደ ቶንሲሉ ህመም መነሻ = ጸረ ባክቴሪያ መድሃኒት 💊💊
👉በቂ ፈሳሽ ማሶሰድ እና ረፍት ማስደረግ
👉የውሃ እንፋሎት ማጠን
👉ሞቅ ያለ የብርቱካን ጭማቂ ማጠጣት
‼️‼️ እሱም ታድያ ሌላ ልጅ እንዳያስይዝ መድሀኒቱን ከጀመረበት ጀምሮ ለ 24 ሰአት ከ ት/ቤት ማስቀረት‼️‼️

አዘጋጅ፦ ዶ/ር ሀና ሊሻን ( በ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ ህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)

🔊🔊🔈ውድ ቤተሰቦች በሚቀጥለው ክፍል በተደጋጋሚ ቶንሲል መያዝ የሚያመጣው ተጓዳኝ ችግር እና መፍትሄዎቹን ይዘንላቹ እንቀርባለን። ከታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን እና like....join....በማድረግ ይከታተሉን‼️‼️ ለወዳጅ ዘመዶም share በማድረግ ያድርሱ 🔊🔊🔈

Facebook=
http://fb.me/DrHannaLishanPediatrician

Telegram=

t.me/DrHannaLishanPediatrician

31/12/2022

✅አንድ ተከታያችን በጠየቀችን መሰረት ስለ ስፖርት ትንሽ ልንላቹህ ወደድን

🤔🤔🤔ስፖርት ለ ህጻናት ምን አይነት ጥቅም አለው⁉️⁉️⁉️

👉ጥሩ እንቅልፍ እንዲኖራቸው
👉ሰዉነታቸዉን ያፍታታላቸዋል
👉ጠንካራ እንዲሆኑ ያግዛል (ጠንካራ አጥንት እና ጡንቻ)
👉ሃይል ስለሚፈልግ አላስፈላጊ ስብ ያቃጥላል
👉በ ጥሩ ትኩረት ትምህርታቸዉን እንዲማሩ
👉በራስ የመተማመን አቅማቸዉን ያዳብራል
👉ከ ማህበራዊ ሂወት ጋር ያላምዳቸዋል

🤔🤔🤔መች ነው አንድ ህጻን ለስፖርት ዝግጁ ነው ሚባለው⁉️⁉️⁉️

✅የሚከተሉትን አራት ነገሮች በየትኛዉም እድሜ ካሟላ ብቁ እንደሆነ ይታሰባል
👉ቀላል የሰዉነት እንቅሲቃሴዎችን እንደ መሮጥ፣ መዝለል፣ በአንድ እግር መቆም ወይም መዝለል፣ መወርወር እና በእግር መምታት ሲችሉ( ይሀንንም ከ 3 እስከ 5 አመት እድሜ ባለው በደንብ እንደሚችሉ ይታሰባል)
👉የመጫወት ወይም ስፖርት የመስራት ፍላጎት ካላቸው

✅ከ 6 አመት በላይ ላሉ እና የቡድን ጨዋታ (team and organized sports) ለሚጫወቱ ደግሞ

👉ትእዛዝ እና መመሪያ መከተል የሚችሉ
👉ስሜታቸዉን መግለጽ እና መቆጣጠር የሚችሉ ከሆኑ

🤔🤔🤔በየትኛው እድሜ ምን አይነት ስፖርት እና ለምን ያህል ጊዜ ይጫወቱ⁉️⁉️⁉️
✅ከ 3 አመት በታች

👉ለ ቡድን ጨዋታም ሆነ ለተቀናጀ እንቅስቃሴ በዚህ እድሜ ዝግጁ አይደሉም
👉በራሳቸዉም ሆነ ከበተሰብ ጋር ግን እዚም እዛም የመሮጥ ዕንቅስቃሴ ማድረግ ይችላሉ

✅ከ 3 እስከ 6 አመት

👉በዚህም እድሜ ለተቀናጀ እንቅስቃሴ ዝግጁ አይደሉም
👉ከመመሪያ ይልቅ በ ሙከራ፣ ለሎች ሚያደርጉትን በመድገም እና አዲስ ነገር ለማወቅ ባላቸው ፍላጎት ነው ሚማሩት
👉በዚህ እድሜም ከተቀናጀ እንቅስቃሴ ይልቅ መሰረታዊ ክህሎት ላይ ማተኮር ያስፈልጋል
👉በመመርያ መጫወት እና ዉድድር ማድረግም በዚህ እድሜ አይመከርም
👉መሮጥ፣ መዋኘት ፣ እጅ ኳስ መቀባበል ፣ እግር ኳስ ፣ የ ልጆች ቅርጫት ኳስ

✅ከ 6 እስከ 9 አመት

👉በዚህ እድሜ መሰረታዊ ክህሎቶችን ስላዳበሩ የተቀናጀ ስፖርት መስራት ይችላሉ
👉ሩጫ፣ ዋና፣ እግር ኳስ፣ ቴኒስ፣ ጂምናስቲክስ፣ ማርሻል አርትስ

✅ከ 10፟ አመት ቡሃላ

👉ዉስብስብ ለሆኑ እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ዉድድር በዚህ እድሜ ዝግጁ ናቸው

መልካም ጊዜ!

📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌

ለተለያዩ የጤና መረጃዎች ከታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን እና Facebook- like....telegram- join....tik tok follow በማድረግ ይከታተሉን
ለወዳጅ ዘመዶም share በማድረግ ያድርሱ 🔊🔊🔈

Facebook=

fb.me/DrHannaLishanPediatrician

Telegram=

t.me/Drhannalishanpediatrician

tiktok.com/

✅ ለ ነፃ የምክር አገልግሎትም ሆነ በ አካል ቀርበው ልጆትን ለማስመርመር በዚህ ስልክ ደዉለው ያነጋግሩ‼️

0902500239
ICMC General Hospital

ዶ/ር ሀና ሊሻን- የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም Consultant pediatrician and Pediatric Rheumatologist at Tikur Anbessa Specialized Hospital

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Tikur Anbessa Hospital, Zambia Street
Addis Ababa