19/01/2024
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን, [18/01/2024 05:02]
[ Album ]
ብቁና ተወዳዳሪ ሙያተኛ እንዲኖር ለማድረግ የሙያ ብቃት ምዘና አይተኬ ሚና እንዳለዉ ተገለፀ፡፡
ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያዉን ግማሽ ዓመት የምዘና ዘርፍ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ ፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍቅሩ ገቢሳ ባስተላለፉት መልዕክትና የመድረኩን አላማ ሲገልጹ ጥራቱ የተጠበቀ የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለን ከቴ/ሙያ ተቋማት እና ከኢንዱስትሪ ተጠሪዎች ጋር በዘርፉ ያከናወናቸውን ስራዎችና ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በጋራ በመገምገም ጥንካሬዎቻችን እና ክፍተቶችን አንጥሮ በማዉጣት የተስተዋሉትን ክፍተቶች በቀጣይ ቀሪ 6ወራት የእቅድ አካል በማድረግ እና በመተግበር የተገልጋዮቻችንን እርካታ በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን, [18/01/2024 05:04]
አክለዉም በልምድ እና በተለያዩ ስልጠና የሚገኙ የተለያዩ የሙያዎችን ብቃት በምዘና ማረጋገጥ ሀገራችን በዝቅተኛና በመካከለኛ ደረጃ የምትፈልገውን የበቃ ሙያተኛ ለኢንዱስተሪው ለመመገብና ኢንዱስትሪው በእውቀት፣ በክህሎትና በአስተሳሰብ ብቁና ተወዳዳሪ ሙያተኛ እንዲኖረው ለማድረግ የሙያ ብቃት ሚና አይተኬ እንደሆነ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ ገልፀዋል ፡፡
የ6 ወሩን የምዘና እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የቅ/ጽ/ቤቱ የቴ/ሙ/ብ/ም/አ/ዝ/አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጅላሎ አብደላ ሲሆኑ የቅ/ጽ/ቤቱ የ6ወሩ የምዘና እቅድ 7454 ስሆን ክንዉኑ 5449 ( 73 % ) መሆኑንና ከተመዘኑት ዉስጥ ብቁ የሆኑት 2642 ብቻ (48.4 % ) መሆኑን የገለፁ ሲሆን የምዘና ስራ የአፈፃፀም መመሪያን ለተሳታፊዎቹ ያቀረቡት የቴ/ሙያ ብቃት ምዘና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ነጋ ጉማታዉ ሲሆኑ በመመሪያ ዉስጥ የተካተቱትን ተግባራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገቢዉ መንገድ በመፈፀም ኃላፊነቱን መወጣት እንደለበት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም በቀረቡ ሰነዶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ለተነሱት ጥያዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ የእለቱ መድረክ ተቋጭቷል፡፡
ምንጭ፡- የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA