Digital Dagu media

Digital Dagu media

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Digital Dagu media, Afar, Addis Ababa.

Digital Dagu media has been created primarly for Looking for Future Best career Path and Advertizing Some Busines moreover working on to strength positive thinking.

29/03/2026
28/03/2026
Photos from FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)'s post 28/03/2026

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

እንደ ግመሎቹ ለፈተና የማይበገር፣ እንደ አዋሽ ለሀገሩ ታማኝ፣ ኢትዮጵያን እንደ እሳት አጥር ሆኖ ወደ ጠበቀው የጀግኖች ማኅደር አፋር፣ ሠመራ ገብተናል።

በሠመራ ሡልጣን ዓሊሚራህ ሐንፋሬ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለሠመራ ከተማ ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

በክልሉ በሚኖረን ቆይታ ሀገር እና ሰንደቅ ዓላማውን ወዳዱ የአፋር ሕዝብ፣ በበረሃው ሙቀትና በጭነት ክብደት እንደማይረቱት ግመሎቹ፣ በብርታት ሀገር ለመለወጥ፣ ሠርቶም ለመበልጸግ እያከናወናቸው የሚገኙትን የልማት ሥራዎች የምንመለከት ይሆናል።

20/03/2026

السلام عليكم ورحمةالله وبركاته
🌙عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 🌴كل عم وأنتم بخير🌙

19/03/2026

Qiid Mubaarak!!!
inkih tan Muslimiin Ummattak!!!

19/03/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mucamad Ascabtu, Kaamol Ayyo Moggolla, Titu Titu, Abdella Shumbahri, Ćééďám Máĺĺí Fíńqíśá, Yasen Edo, Iraawis Qafar, Acmad Macammad Qeelibarqo

18/03/2026

ሰበር ዜና፦ የዒድ አል-ፊጥር በዓል አርብ (የጁምዓ ዕለት) መሆኑ ተረጋገጠ!

መካ — ሳዑዲ ዓረቢያ በዛሬው ዕለት ረቡዕ ምሽት በመላው ሳዑዲ ዓረቢያ ሲከናወን የቆየው የሸዋል ጨረቃ ፍለጋ ውጤት ይፋ ሆኗል። በዚሁ መሠረት የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ ምክንያት፣

ነገ ሐሙስ የረመዳን 30ኛው ቀን ሆኖ የሚጾም ሲሆን፣ ታላቁ የዒድ አል-ፊጥር በዓል ከነገ በስቲያ አርብ (ጁምዓ) መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም (March 20, 2026) እንደሚውል የሳዑዲ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይፋ አሳውቋል።

በዓሉ ከአርብ የጁምዓ ዕለት ጋር በመገጣጠሙ ልዩ ድምቀት ይኖረዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ይህ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።

ረመዳንን በሰላም እንዳጠናቀቅን ሁሉ፣ በዓሉንም ከቤተሰብ እና ከወዳጅ ዘመድ ጋር በጋራና በመረዳዳት እንድታሳልፉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ዒድ ሙባረክ! መልካም በዓል!

Via GN

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

04/06/2023

Rookâ xaagu

😢Innaa lillaahi wa innaa ilayhi raajiquun!🥲

🤲Yalli jannatti Qarus kaa abay

Logya Magaalah Xiinissoh saqalah suge Gifta ibraahim Macammadaay i.l.l 26/09/2015 issi cakki geem timixxige.

usuk meqe numuy,Qafariinô gooriiy;Qadliino kee agiiranna le lubaakak Sugte.
😭kay buxah maraay;Wadaay kee Inkih tan Qafar ummattah yalli imaan kee Sabri yaceem Qaagitna.

Qafar Qunxaaneytih farani Egla

15/05/2023

ጨምዳዳው መቶ ብር
ማንነትን የመቀበል ቁልፍ

የማንነትህን ዋጋ የሚወስነው ምንድን ነው? አንዳንድ ሰዎች የማንነታቸውን ዋጋ የሚመዝኑት ካሳለፉት መከራና ከደረሰባቸው ችግር አንጻር ነው፡፡ የደረሰባቸውን የኑሮ ውጣ ውረድ በአካላቸውና በኑሮአቸውም ላይ ያደረሰውን ጉዳት በቀጥታ ከማንነታቸው ዋጋ ጋር ያዛምዱታል፡፡ ሲቸገሩና ሲጎሳቆሉ የማንነታቸውን ዋጋ ይቀንሱታል፡፡ በአንጻሩ ነገሮች በመልካም ሲሄድላቸውና የተሳካላቸው ሲመስላቸው ለራሳቸው የሚሰጡትን ዋጋ ከፍ ያደርጉታል፡፡ ሰዎችም ካለማቋረጥ ይህንኑ መልእክት ለህሊናው እንዲናገሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡ ውጤቱም የወደቀ ማንነትን ነው፡፡

በአንድ በዝቅተኝነት ስሜት የተመቱ ሰዎች ለምክር በሚመጡበት ማእከል ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል፡፡ ችግራቸው አንድ ነው፣ የኑሮአቸው ሁኔታ በራሳቸው ላይ ያላቸውን አመለካከት ደብድቦ ጥሎታል፡፡ በራሳቸው ላይ የወደቀ አመለካከት አላቸው፡፡ ይህ ሰው በምን መልኩ ከዚህ አመለካከት ሊያወጣቸው እንደሚችል ካሰበ በኋላ አንድን ምሳሌ ነገራቸው፡፡

በእጁ አንድ ድፍን መቶ ብር ይዟል፡፡ ወደ ሰዎቹ ዘወር አለና፣ “የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?” አላቸው፡፡ የሁሉም መልስ እንደተጠበቀው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡ የሚቀጥለው ጥያቄ፣ “ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል” የሚል ነበር፡፡ ሁሉም በመሽቀዳደም ምን ሊገዛ እንደሚችል መናገር ጀመሩ፡፡ በመቀጠልም፣ ይህንን መቶ ብር በመዳፉ አጅግ ጨመደደው፣ ከዚያም ወደ መሬት ጣለውና ረገጠው፡፡ በእጁ አንስቶ ከጨመደደው በኋላ ያንኑ ጥያቄ ጠየቃቸው፣ “የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?”፡፡

የሁሉም መልስ እንደቀድሞው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛውንም ጥያቄ ደገመው፣ “ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል?” የሚል ነበር፡፡ መልሳቸው እንደቀድሞው ነበር፡፡ ከዚያም መልእክቱን አስተላለፈላቸው - “ይህ ብር ተጨማደደ፣ ወደቀ፣ ተረገጠ፣ … ዋጋው ግን ያው ነው፡፡ የእናንተም ዋጋ እንዲሁ ነው፡፡ ምንም አይነት ነገር በሕይወታችሁ ቢያልፍ፣ ዋጋችሁ ግን ያው ነው - የውጪ ገጠመኛችሁና ሁኔታችሁ የማንነታችሁን ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር አይችልም”፡፡

“አንተነትህን የያዘው የሆንከው ማንነትህ አይደለም፣ ነኝ ብለህ ያሰብከው ሃሳብህ እንጂ” - Unknown Source

ከተወለድክባት ቀን ጀምሮ ያለፍክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ተመልከታቸው፡፡ የወደቅክባቸውንና የተነሳህባቸውን፣ ያዘንክባቸውንና የተደሰትክባቸውን፣ የብቸኝነትህን ጊዜና በወዳጆች የተከበብክባቸውን ጊዜአት … አስባቸው፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች የተለያዩ የስሜት ከፍታዎችንና ዝቅታዎችን እንድታሳልፍ ዳርገውሃል፣ ሆኖም በማንነትህ ላይ ጥቂት እንኳ የዋጋ መቀነስ ተጽእኖ የላቸውም፡፡ ማንነትህ፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፍም ያው ማንነትህ ነው፡፡
ስኬታማ ሆንክም አልሆንክ፣ ባለጠጋ ሆንክም አልሆንክ፣ እነዚህ ነገሮች ከማንነትህ ጋር በፍጹም አይገናኙም፡፡

በማንነትህ ላይ ያለህ አመለካከትና ለማንነትህ የሰጠኸው ዋጋ ግን በስኬታማነትህ ላይ ታላቅ ተጽእኖ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ያለፈው ታሪክህ፣ አሁን የምታልፍበት የኑሮ ጫናም ሆነ ያለህና የሌለህ ነገር በአንተነትህ ዋጋ ላይ ተመን እንዲያስቀምጡበት የምታደርገው አንተው ብቻ ነህ፡፡ ሰው የመሆንህ ክቡርነት በፍጹም በዋጋ ሊተመን ስለማይችል፣ ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት አይችልም፡፡ በራስህ ላይ ያለህ ግምት ግን ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አመልካችነቱ የስሜትን ከፍታና ዝቅታ እንጂ የማንነትን ዋጋ ከፍታና ዝቅታ አይደለም፡፡

ዋጋህን ሳትቀናንስ፣ ካለፈውና ከአሁኑ ሁኔታህ ላይ አይኖችህን አንስተህ በፊትህ ወዳለው መልካም የወደፊት ስኬት እንድትዘልቅ የሚከተሉትን እውነታዎች ማሰላሰሉ ጠቃሚ ነው፡፡

1. ሰዎች የሚሰጡህን ቅጽል ስም አትቀበል
“ቅጽል ስሞች በሰው ላይ የመጣበቅ ባህሪይ አላቸው፤ በተለይም ክፉ ቅጽል ስሞች እንደማይለቁ ማስቲሾች ናቸው” – Thomas Chandler

2. የሆነልህን እንጂ የሆነብህን አትቁጠር
“ከሃዘኖችህ ይልቅ ሃሴቶችህን፣ ከጠላቶችህ ይልቅ ደግሞ ወዳጆችህን ቁጠር” - Irish Proverb

3. ራስህን አክብር
“ለራሳችን ያለንን ክብር አሳልፈን ካልሰጠናቸው በስተቀር ሰዎች ሊወስዱብን አይችሉም” - Mahatma Gandhi

(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Photos from ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች's post 12/05/2023
Photos from Qafar Qunxaaneytih farani Egla's post 07/05/2023

🎉Qafar Qunxaaneytih farani egla Qafar afih barteenit dooqasse🎉
🤙Qafar Qunxaaneytih farani egla Qunxa-garabluk 3,2015- Caxah alsa 30,2015 fan: Qafar af Barisak Sugte barteenit Qaxmeqe gurral; Baxaabaxsa le Caflatal Dooqasse.

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Afar
Addis Ababa