08/12/2024
#2023 | ባሻር አል-አሳድ ለሲቪል ሰራተኞች እና ጡረተኞች 100% የደመወዝ ጭማሪ አድርገው ነበር !
በሶሪያ ውስጥ የመንግስት ስራዎች በጣም ተፈላጊ ነበሩ። ለሰዎች የስራ ዋስትና ሰጥተው ነበር (መባረራቸው ያልተሰማ ነበር)፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ጭማሪም የተረጋጋ ነበር። እንደ መምህራን፣ ዶክተሮች እና የሰራዊት አባላት ያሉ አብዛኞቹ የመንግስት ሰራተኞች በቀን ውስጥ ለጥቂት ሰዓታት ብቻ የሚሰሩ እና በቂ ህዝባዊ በዓላት ያላቸው በመሆኑ ውጥረት እምብዛም አይታይባቸውም ነበር።
በሒደት ግን የሶሪያ ሲቪል ሰርቫንቶች ለኑሮ እና ለጉዞ የሚያወጡትን ወጪ ለመሸፈን በሚከፈላቸው አነስተኛ ክፍያ በመናደዳቸው ከስራ መልቀቃቸው እየጨመረ መጣ።
ሁኔታዉ በሀገሪቱ ከሚደረገዉ የእርስ በርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ አዝማሚያው ሊስፋፋ ይችላል በሚል ስጋት የሶሪያ ገዥ አካል የመንግስት ተቋማት ስራቸውን እንዲቀጥሉ የካሮትና ዱላ ዘዴን እየተጠቀመ ነበር። ነሃሴ 2023፣ የሶሪያው ፕሬዝዳንት ባሻር አል-አሳድ ለሲቪል ሰራተኞች እና ጡረተኞች 100% የደመወዝ ጭማሪ ማድረጋቸውን አስታወቁ። አገዛዙ የአንድ ጊዜ ጉርሻዎችንም ሲሰጥ ቆይቷል። የመንግስት ሰራተኞች በሚያዝያ ወር ተጨማሪ 75,000 ፓውንድ፣ እና ሌላ 100,000 ፓውንድ በነሐሴ ወር አግኝተዋል። መንግስት ከቀረጥ ነፃ የሆነውን አበል ከ50,000 ፓውንድ ወደ 92,000 ፓውንድ ጨምሯል፣ ይህም ማለት አብዛኛው የመንግስት ሰራተኞች ምንም አይነት የገቢ ታክስ አይከፍሉም።
ይሄንን ሁሉ እርምጃ መቋቋም ያልቻለዉ የሶሪያ ኢኮኖሚ በስራ ላይ የሚገኝ አንድ የመንግስት ሰራተኛም አማካይ ወርሃዊ ደሞዝ ከ100,000 የሶሪያ ፓውንድ ያነሰ ወይም ወደ 23 ዶላር አካባቢ ሆነ። በሌላ መንገድ፣ በ2011 የእርስ በርስ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ 80 በመቶ የሚጠጋ ዋጋ አጥቷል።
የኢኮኖሚና የፖለቲካ ኃይሎች እነዚህን አዝማሚያዎች እያባባሱት መጡ። በአል አሳድ አስተዳደር ተስፋ የቆረጡ የሶሪያ መንግሥት ሰራተኞች አማፂ ሀይሎችን ከመቀላቀል እስከ መደገፍ ገቡ። የሶሪያ ፓውንድ ውድመት፣ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ግሽበት፣ አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦች እጥረት እና የዩክሬን ጦርነት አለም አቀፍ እንድምታ በሶሪያ ያለውን የኑሮ ውድነት በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር በገቢ እና ወጪ መካከል ታይቶ የማይታወቅ ልዩነት ፈጠረ።
የአላሳድ መንግስት ከደመወዝ ጭማሪ እና ጉርሻ በተጨማሪ የስራ መልቀቂያ ፍሰቱን አስቸጋሪ ለማድረግ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል። ለምሳሌ>
🌴ስራ የሚለቁ ሰራተኞችን በሽብርተኝነት እስከ መፈረጅ
🌴ከስራ መልቀቅ የህዝብ ሴክተርን መክዳት በሚል እንደ ፖለቲካዊ እርምጃ ወይም ፀረ-መንግስት ተግባር አድርጎ መቅጣት
🌴ማመልከቻ ሊፀድቅ የሚችለው ሰራተኛው በዲፓርትመንቱ የማይፈለግ ከሆነ ብቻ ነዉ የሚል ዉሳኔ አፅድቋል
🌴የስራ መልቀቂያ ውሳኔዎች በብሔራዊ መረጃ ኤጀንሲ መጽደቅ አለባቸዉ በሚል የቢሮክራሲ ደረጃዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የብዙ ሰራተኞች የመልቀቂያ ጥያቄዎች ዉድቅ ተደርገዋል።
🌴እምቢ ብለዉ የለቀቁት በፀጥታ ሃይሎች ምርመራ እየተደረገ እርምጃ ተወስዶ ሰራተኞችን በስራቸው ለማቆየት ተሞክሯል።
መምህራን ኔትወርክ - እዉቀት ነፃ ያወጣል
መረጃዎች ከፈለጋችሁ ከስር ያሉ Link join አድርጉ 👇👇
https://t.me/EducationEthiopiaa
https://t.me/EducationEthiopiaa