02/08/2023
የሞረትና ጅሩ ወረዳና የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመቀናጄት በክረምት በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር በእነዋሪ ከተማ ውስጥ የአካባቢ ብክለት የተፈጠረባቸውን ቦታ በመለየት የደረቅ ቆሻሻ የማሶገድ ስራ መስራትና የአቅመ ደካማ እና የአረጋውያን የቤት ጥገና ስራ ተከናውኗል።
ሁሉም ሰው አካባቢውን መንከባከብ አለበት
02/08/2023
የሞረትና ጅሩ ወረዳና የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመቀናጄት በክረምት በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር በእነዋሪ ከተማ ውስጥ የአካባቢ ብክለት የተፈጠረባቸውን ቦታ በመለየት የደረቅ ቆሻሻ የማሶገድ ስራ መስራትና የአቅመ ደካማ እና የአረጋውያን የቤት ጥገና ስራ ተከናውኗል።
29/07/2023
በሞረትና ጅሩ ወረዳ አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ 2014 ዓ.ም ለ2015ዓ.ም በጀት አመት የመንግስት ሰራተኛውን የተከለው ችግኝ በሚታየው ደረጃ ላይ ይገኛል።
13/07/2023
በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ብክለት ባስከተሉ 147 ፕሮጀክቶች የእርምት እርምጃ መውሰዱን የአማራ ክልል አካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ።
የአማራ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እና አስፈጻሚ አካላት የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸጸም ላይ እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ላይ አስፈጻሚ አካላት የተቋማቸውን ዓመታዊ የሥራ ጥንካሬ እና ጉድለቶችን ለሚከታተላቸው ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።
የግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ውኃ ሃብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጠሪ የሆነው የአማራ ክልል አካባቢና ደን ጥበቃ ባለሥልጣንም በበጀት አመት የፈጸማቸውን የተግባር አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን ሪፖርቱን ያቀረቡት የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ኀላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ 75 ፕሮጀክቶች አካባቢን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚበክሉ ተለይተው በበጀት ዓመቱ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ታቅዶ በተሠራው ጠንካራ የቁጥጥር እና ክትትል ስራ 147 ፕሮጀክቶች አካባቢን በከፍተኛ ደረጃ የሚበክሉ እና ሕግን የጣሱ ሆነው በመገኘታቸው የእርምት እርምጃ መወሰዱን ገልፀው በፕሮጀክቶች ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች ጤናማ አካባቢ እንዲኖራቸው እና ጤናቸው ከስጋት የወጣ እንዲሆንም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ተስፋሁን በጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ደብረብርሃን፣ ደሴ፣ ወልዲያ እና ደብረ ማርቆስ ከተማ ከ1600 በላይ በሚሆኑ የኤሌክትሪክ ትራንስፈርመሮች በተደረገው ጥናት የነዋሪዎችን ጤና የሚጎዱ ኬሚካሎችን የያዙ ፒሲቢ የተባሉ ኬሚካሎች ያሉባቸው 421 ትራንስፎርመሮችን በመለየት ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል ብለዋል።
በክልሉ የሚገኙ ፋብሪካዎች ከአካባቢ ብክለት ነፃ ይሆኑ ዘንድ በጥናት የተደገፈ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ስለመሆኑም ኃላፊው ለምክር ቤቱ አንስተዋል።
ለአፈር ምርታማነት እና ለሥነ ምህዳር አስጊ የሆኑ እንደ አቀንጭራ፣ የወፍ ቆሎ እና የመሳሰሉ መጤ አረሞች ስርጭት በመለየት 60 ሽህ ሄክታር አረም ለመቆጣጠር ታቅዶ 177, 171 ሄክታር መቆጣጠር መቻሉንና
በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም የጣና ሐይቅን ከእንቦጭ አረም ለመከላከል 1900 ሄክታር አረም ለማስወገድ ታቅዶ 1504 ሄክታር ማስወገድ መቻሉንና አሁንም አረሙን ከሃይቁ የማስወገድ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ለቋሚ ኮሚቴው አንስተዋል።
ባለስልጣኑ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት እና ውጤቶቻቸው ዝውውርን ለመቆጣጠር በትኩረት ሲሠራ መቆየቱንም ገልፀው
ቁጥራቸው በመመናመን ላይ ያሉ የዱር እንስሳትን በልዩ ትኩረት መጠበቅና መንከባከብ ሌላው የባለሥልጣኑ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ መሠራቱን አሳውቀዋል።
በቀበሌ ደረጃ የአካባቢ ጥበቃ መዋቅር አለመኖር፣የአየር ንብረት ለውጥና የቆሻሻ አወጋገድ ሥራዎች በአመራሩ ትኩረት አለማግኘት እና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች አለመወገድ ደግሞ በቀጣይነት መስተካከል ያለባቸው ጉድለቶች ሆነው ተነስተዋል።
04/07/2023
22/05/2023
29/01/2023