05/02/2022
በሞሮኮ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ለቀናት የቆየውን ታዳጊ ሕይወት ለማትረፍ ጥረቱ ቀጥሏል - BBC News አማርኛ
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Getachew Duchisho, Education, Hawassa, Addis Ababa.
21/01/2022
4ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች
****************
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
1. ምክር ቤቱ በቀዳሚነት የተወያየው የመንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎትን አደረጃጀት፣ ስልጣን እና ተግባራቱን ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ የመንግስት ኮሙኑኬሽን ሥራን በተቀናጀና በተናበበ አኳኋን በማከናወን ብዙሃኑን ተደራሽ የሚያደርግና ወቅታዊ ሁኔታዎችን ባማከለ መንገድ ትክክለኛ መረጃን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ማድረስ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ እንዲሁም ዜጎችን በሀገራዊ ልማትና በአካታች የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት በብቃት ለማሳተፍና ለአዲሱ ምዕራፍ ጉዞ፣ ለሀገራዊ ለውጦችና ብልጽግ ስኬት ተገቢውን ሚና መጫወት እንዲችሉ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ የአገልግሎቱን እደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር የሚወስን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ከዛሬ ጥር 12 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ ሰራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያበረከተውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጎልበት ዘርፉ አስተማማኝ፣ የተቀናጀ፣ ዘመናዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ እንዲራመድ ማድረግ በማስፈለጉ፣ እንዲሁም የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎትን አስመልክቶ የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚ አካላት ተግባሮቻቸውን ተናበውና ተቀናጅተው በውጤታማነት መፈጸም የሚያስችላቸው የህግ ማእቀፍ በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተወያይቶ ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
3. የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎትን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ ደንብ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ነው፡፡ የመንገድ ደህንነት ስራዎችን የሚመራ ጠንካራ መዋቅራዊ አደረጃጀት አለመኖሩ በሀገራችን ጎልተው ለሚታዩት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ችግሮች አንዱ መንስኤ መሆኑ ስለታመነበት፤ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የመንገድ ደህንነት ተግባራት በትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ ሚኒስቴር እና በተለያዩ የትራንስፖርት መዋቅሮች የተበታተኑ በመሆኑ ባልተቀናጁ እቅዶች እንዲመራ መደረጉ ውጤታማ ሊያደርገው ባለመቻሉ፣ እንደዚሁም በተለያዩ መዋቅሮች ውስጥ የነበረው የመንገድ ደህንነት አደረጃጀትም ቢሆን ምከር ከመስጠትና ግንዛቤ ከመፍጠር የዘለለ ድርሻ ያልነበረው ከመሆኑ አንጻር በመንገድ ደህንነት ረገድ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ አለመቻሉ ለደንቡ መሻሻል ምክንያት ሆኗል፡፡ ስለሆነም በመሰረታዊነት የዘርፉን ችግር መፍታት እንደሚያስችል የታመነበት ረቂቅ ደንብ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
4. ቀጥሎ ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው በአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን የተሳለጠና ደህንነቱ የተረጋገጠ የመንገድ ትራንስፖርት እንዲኖር ወሳኝ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የአሽከርካሪዎች የማሽከርከር ብቃት ስለሆነ ብቃት ያላቸውን አሸከርካሪዎች ለማፍራት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ ስርዓት መቅረጽና የህግ እውቅናና ድጋፍ መስጠት የሚገባ በመሆኑ እንዲሁም ከብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን አካላት ተግባርና ሃላፊነት በግልጽና በዝርዝር መደንገግ በማስፈለጉ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
5. ምክር ቤቱ የባለሞተር ተሽከርካሪዎች የፍጥነት ወሰን ረቅቅ ደንብ ላይ የተወያየ ሲሆን የተሽከርካሪ ፍጥነት ዋነኛ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ እንደመሆኑ ለችግሩ ተገቢው መፍትሄ ካልተበጀለት በፍጥነት ምክንያት እየደረሰ የሚገኘውን ከፍተኛ የሆነ የሰው ሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት መቀነስ የማይቻል በመሆኑ፤ በ1961 ዓ.ም የወጣው የተሽከርካሪዎች የፍጥነት ወሰን ደንበ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የትራፊክ ፍሰት፣ የመንገድ እድገት እና የአሽከርካሪዎች ባህሪ ለማረቅና ለመምራት የሚያስችል ባለመሆኑ ከጊዜው ጋር የሚራመድ የህግ ማእቀፍ በማስፈለጉ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
6. በመቀጠል ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው የአሽከርካሪ ክብደትና መጠንን ለመወሰንና ለመቆጣጠር በወጣው ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ለመደገፍ የትራንስፖርት ዘርፍ አስተዋጽ ከፍተኛ በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሽከርካሪዎች መጠንና የመጫን አቅም ከፍ እያለ በመሄዱ የመንገዶቻችንን ደረጃ መሰረት በማድረግ በመንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችን ክብደት እና መጠን በመወሰን በመንገዶች ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ጉዳትና ብልሽት ለመቀነስ ብሎም ለማስቀረት፤ በመንገድ ትራፊክ ደህንነት ላይም ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ ለማስወገድ እንዲሁም በሀገራችን በፍጥነት እያደገ የመጣውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ይቻል ዘንድ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
7. ቀጥሎ ምክር ቤቱ የተወያየው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲቋቋም ዋና አላማው የነበረው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ የፌዴራል መንግስትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንዲሁም ከስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ውጭ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በአነስተኛ ታሪፍ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ነበር፡፡ የአገልግሎቱን ተደራሽነት በማስፋት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሙሉ ቀን አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች እየኖሩ በፌደራል መንግስት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት የሚያገለግሉ ሰራተኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ደንብ ቁጥር 298/2oo6ን የሚያሻሽል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደን ላይ ነው፡፡ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን ማጠናከር በሀገሪቱ ከፋይናንስ እንቅስቃሴ እድገትና ከቴክኖሎጂ መዘመን ጋር እየተሳሰሩ የመጡትን የፋይናንስ ወንጀሎችን በተለይም በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እንዲሁም ሽብርተኝነትን እና የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜት በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል እንዲሆን፤ በተጨማሪም ሀገራችን ከተቀበለቻቸው እና ካጸደቀቻቸው ከዓለም አቀፍ የትብብር ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ትስስር በመፍጠር የወንጀል መንስኤዎችን፣ ስጋቶች እና ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል የህግ እና የአሰራር ክፍተቶችን መሙላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያይቶ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
21/01/2022
08/01/2022
Ayyaanu🌲 Keerunniha🌲🌼Fayyimmanniha🌲🌼Baxillunniha 🌲🌼Mittimmanniha🌲🌼Lophonniha🌲🌼Shooshanqenniha🌲🌼🌲🌼Ikko'ne! 🌲Qoleno🌼Gobbankera🇪🇹🌲💚Keere💛💙Dagankera❤Baxille🌲🌼Mittimma🌼Oonke🌼Ha'mii'ni! Ledeno, 🌼Buxane🌼Buljitannoha🌼🌲Hudidhinori🌼🌲Duubbannoha🌼🌲Qarraataamu🌼🌲Qawaaxxidhannoha🌼Dadillitinori🌲🌼Sheshifattannoha🌼Wi'litannori🌼Hindiiddo🌼Feyamantannoha ikkonke!🌼 Jaalla'ya Keeri Ayyaana Ikko'ne💖💖!
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
ኢሳይያስ 9፥6
እንኳን ለጌታችን እና ለመድሐንታች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
02/01/2022
አሜሪካ በሀገራችን ዙሪያ አዲስ እቅድ አዘጋጅታለች!!!
የምዕራባውያንን የውስጥ ሚስጥር አፈንፍኖ ይፋ የሚያወጣው የፈረንሳዩ "Press Tv Francias's" የመረጃ አውታር ኢትዮጲያን በተመለከተ አዲስ ሚስጥራዊ መረጃን በድሕረ ገፁ ይዞ ወጥቷል።
የኢትዮጲያ ጦር የትግራይ ክልል አማፂያን የያዙትን የአማራ'ና አፋር ክልል ከተቆጣጠሩ ቡኃላ የአሜሪካ መንግስት በሕውሐት ላይ ያለውን የጋራ ውል ሊስርዝ መሆኑን የመረጃ ማዕከሉ ዘግቧል። ለዚህም እንደ ምክንያት የተጠቀስው አማፂያኑ የሕውሐት ስራዊት በወረራ በያዛቸው ከተሞች የፈፀመው ግፍ የሕዝብን የቁጣ ማዕበልን ቀስቅሶ የመተላለፊያ ቀዳዳውን መድፈኑ ዩኤስን ተስፋ ማስቆረጡን በስፋት አስነብቧል።
አሜሪካ በኢትዮጲያ የምታደርገው የእጅ አዙር ጦርነት የቋመጡበት የድል ተስፋው ተመናምኗል ያለው የመረጃ አውታሩ አዲሱን እቅዷንም እንዲሁ ይፋ አድርጓል። ዋሽንግተን በሉዓላዊ ሐገራቶች የውስጥ ጉዳይ ጥቅሟን ያማከለ የውክልና ጦርነት ስትፈፅም ሴናተሮቾን በሁለት ጎራ ከፍላ አንዱ የመንግስት ሌላኛው የተቃዋሚ ቡድን ደጋፊ አድርጋ ታስቀምጣለች።
በሁለቱም የተፋላሚ ቡድኖች ውስጥ የሚገኙት የአሜሪካ ሴናተሮች አሽናፊውን ቡድን ከአሜሪካ ማዕከላዊ መንግስት ጋር ድፕሎማት በመሆን በሽምግልና በወዳጅነት ለማስተሳስር የተጣለበት ማዕቀብ ተነስቶለት ኢኮኖሚው የሚያንስራራበትን ሁኔታ እንዲመቻች ይማፀኑታል። Press Tv Francain's የመረጃ አውታር የዋይት ሐውስ የወደፊት እቅድ በኢትዮጲያ የፌደራል መንግስቱን አቋም ሲደግፉ የነበሩ ሴናተሮቹን'ና ፖለቲከኞቹን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ትስስሩን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ስራ እንደሚሆን ዘግቧል።
አሜሪካ በኢትዮጲያ ያለው ጦርነት በድርድር መቋጫን ያግኝ በማለት አማፂያኑን ሕውሐትን ከሞት ለመታደግ በቱርክ፤ ቻይና'ና ሩሲያ ለኢትዮጲያ መንግስት የሚያደርጉትን የመሳሪያ ድጋፍ እንዲያቆሙ ያደረገችው ጥረት አለመሳካቱን ተከትሎ ሕውሐትን አውላላ ሜዳ ላይ ጥላዋለች ሲል የመረጃ ማዕከሉ አስታውቋል።Ahmed Habib Alzarkawi
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ኢትዮጲያ አሽንፋለች 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
19/12/2021
ወያነ ዛፍ!!!