Ethiopian Banking Information -EBI- የኢትዮጵያ የባንክ መረጃ

Ethiopian Banking Information -EBI- የኢትዮጵያ የባንክ መረጃ We provide you the latest and fundamental information about Ethiopian Banking Sector.

ዳሸን ባንክ ከ25 ቢሊየን ብር በላይ በቴሌብር የብድር አገልግሎት አቀረበ!ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በነበረው ስራቴጂካዊ አጋርነት ባለፉት አራት ዓመታት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የብድ...
17/09/2026

ዳሸን ባንክ ከ25 ቢሊየን ብር በላይ በቴሌብር የብድር አገልግሎት አቀረበ!

ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በነበረው ስራቴጂካዊ አጋርነት ባለፉት አራት ዓመታት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የብድር አገልግሎት በቴሌብር በኩል ማቅረቡን ገልጿል።

እስከ መስከረም 2019 ዓ.ም በቴሌብር ላይ በሚገኙት መላና እንደኪሴ ከ3.2 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የብድር አገልግሎት ባንኩ ያቀረበ ሲሆን ከ15.7 ሚሊየን በላይ የብድር ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል።

ባንኩ የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ የሚያከናውናቸውን ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ውጤቶችን ይፋ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የንግድ ባንኮች የቀረበውን ዶላር ሙሉ በሙሉ መግዛት ሳይችሉ መቅረታቸውን...
17/09/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ውጤቶችን ይፋ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የንግድ ባንኮች የቀረበውን ዶላር ሙሉ በሙሉ መግዛት ሳይችሉ መቅረታቸውን ሠምተን ነበረ።

በመስከረም 9፣ 2026 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ጨረታ ብሔራዊ ባንክ 125 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ ያቀረበ ቢሆንም፤ 20ዎቹ ተሳታፊ የንግድ ባንኮች የጠየቁት 120 ሚሊዮን ዶላር ብቻ በመሆኑ 5 ሚሊዮን ዶላር ሳይሸጥ ቀርቷል።

በዚሁ ጨረታም አንድ ዶላር በአማካይ በ160.53 ብር ተመን የተሸጠ ሲሆን፣ የብር የመግዛት አቅም መጠነኛ (የ1.16%) መሻሻል አሳይቷል።

ግን እንዴት ተረፈ ምክንያቱ ምንድን ነው?
🤔 የፋይናንስ ዘርፍ ተንታኞች እና የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፤ ይህ ሁኔታ የተፈጠረው በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ስለቀነሰ ሳይሆን፣ በንግድ ባንኮች ላይ የተፈጠረ የብር እጥረት (Birr liquidity crunch) በመኖሩ ነው። ባንኮች ዶላር ለመግዛት የሚያስችል በቂ የሆነ የብር ክምችት ስለሌላቸው የቀረበውን ሙሉ ዶላር መግዛት አልቻሉም።
ባለፈው ነሐሴ ወር በተካሄዱት ጨረታዎች ባንኮች ከቀረበው ዶላር እስከ አራት እጥፍ የሚደርስ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተው እንደነበር የሚታወስ ነው።

👇 ይህ የባንኮች የብር እጥረት በገበያው ላይ ምን አይነት ተጽእኖ ይኖረዋል ብለው ያስባሉ? ሃሳቦን በኮመንት ያጋሩን!

(ምንጭ፡ Capital Ethiopia)

ለፈገግታ 😂
13/09/2026

ለፈገግታ 😂

ገንዘብ አስቸኳይ ሆኖባችሁ ወይም ለቢዝነሳችሁ ማሳደጊያ ማስያዣ አጥታችሁ ተቸግራችኋል? በሀገራችን ያለ ምንም ማስያዣ (Collateral-free) ብድር በማቅረብ ላይ ከሚገኙ ተቋማት ውስጥ ፦...
11/09/2026

ገንዘብ አስቸኳይ ሆኖባችሁ ወይም ለቢዝነሳችሁ ማሳደጊያ ማስያዣ አጥታችሁ ተቸግራችኋል? በሀገራችን ያለ ምንም ማስያዣ (Collateral-free) ብድር በማቅረብ ላይ ከሚገኙ ተቋማት ውስጥ ፦

🏦 አበዳሪ ተቋማቱና የብድር አማራጮቻቸው
1. ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ (Coopbank): በ'ምቹ' አፕሊኬሽን አማካኝነት ግንባር ቀደም ሆኖ እያበደረ ይገኛል። ጥሩ የሂሳብ እንቅስቃሴ፣ ንግድ ፍቃድ እና መታወቂያ ካላችሁ በቀላሉ ብድር ማግኘት ትችላላችሁ።

2. አቢሲኒያ ባንክ: በ'አፖሎ' (Apollo) አፕሊኬሽን የባንክ እንቅስቃሴያችሁን መሰረት አድርጎ እስከ 100,000 ብር ድረስ ያበድራል።

3. ዳሽን ባንክ: ከቴሌብር ጋር በመተባበር 'መላ' በተሰኘው አገልግሎት የ10 ቀን፣ የ20 ቀን፣ የ45 ቀን እና እስከ 6 ወር የደሞዝ ብድር አማራጮችን አቅርቧል።

4. ስንቄ ባንክ: በተመሳሳይ ከቴሌብር ጋር በመተባበር 'ዋቢ' በተሰኘ አገልግሎት አጭር ጊዜያዊ ብድሮችን ይሰጣል።

5. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): በ CBE Fast loan, በሲቢኢ ብር (CBE Birr) እና በቴሌብር በኩል ተመሳሳይ ያለማስያዣ የብድር አማራጮችን አዘጋጅቷል።

6. አዋሽ ባንክ: 'ጥላ' በተሰኘው የዲጂታል መተግበሪያ ከቴሌብር ጋር በመቀናጀት ፈጣን ብድር ያቀርባል።

7. የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት: በቡድን ዋስትና (Group Guarantee) መልክ ያለምንም ማስያዣ ብድር ማግኘት የምትችሉባቸው ተቋማት ናቸው።

📋 ብድሩን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ኮመን መስፈርቶች

~ ጥሩ የብድር ታሪክ (Credit History): የወሰዱትን ብድር በወቅቱ የሚመልሱ ከሆነ የብድር መጠኖት እያደገ ይሄዳል።

~የአካውንት እንቅስቃሴ: ባንኮች አቅማችሁን የሚመዝኑት በሂሳብ እንቅስቃሴያችሁ (Transaction) ስለሆነ ይህ በጣም ወሳኝ ነው።

~ ህጋዊ ሰነዶች: የታደሰ ንግድ ፍቃድ ወይም መታወቂያ።

⚠️ እንደ ማሳሰቢያ

ከባንኮች በዲጂታል የምታገኙት ያለ ማስያዣ ብድር ወለዱ በጣም ከፍተኛ ነው። ስለዚህ ይህን ብድር በጣም አዋጭ ለሆነ ቢዝነስ ወይም እጅግ አስቸኳይ ለሆነ ችግር ብቻ ተጠቀሙበት እንጂ፤ የቅንጦት እቃዎችን ለመግዛት እንዳትጠቀሙበት እንመክራለን!

👇 እናንተስ ያለምንም ማስያዣ ብድር ለማግኘት ከነዚህ ውስጥ የትኛውን ትመርጣላችሁ? እስኪ ኮሜንት ላይ አጋሩን።

(ጠቃሚ መረጃዎችን በቀጣይም ለማግኘት ፔጁን Like እና Follow ማድረጎን አይርሱ!)

የአማራ ባንክ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለባንኩ ዕድገት ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና እና ሽልማት ተሰጣቸው። ባንኩ በስካይላይት ሆቴል ባካሄደው የዕውቅና መ...
10/09/2026

የአማራ ባንክ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለባንኩ ዕድገት ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና እና ሽልማት ተሰጣቸው።

ባንኩ በስካይላይት ሆቴል ባካሄደው የዕውቅና መርሃ-ግብር ላይ የአማራ ባንክ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እንዲሁም በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ ለነበሩት አቶ ሳሙኤል ታደሰ ለአገልግሎታቸውና ላበረከቱት አስተዋጽዖ ዕውቅና በመስጠት ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።

ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እና አቶ ሳሙኤል ታደሰ ለእውቅናው ምስጋናቸውን አቅርበው፤ በአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ያገለገሉበትን ጊዜ እንደ ጠቃሚ ሙያዊ ተሞክሮ በማስታወስ፣ ለባንኩ የወደፊት ስኬት እና እድገት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

መልእክት ከ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ። አዲሱ አመት ባንኩ እና ደንበኞቹ ያጋጠማቸውን መንገጫገጭ በድል የሚወጡበት እንዲሆን ፔጃችን ይመኛል።
10/09/2026

መልእክት ከ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ።
አዲሱ አመት ባንኩ እና ደንበኞቹ ያጋጠማቸውን መንገጫገጭ በድል የሚወጡበት እንዲሆን ፔጃችን ይመኛል።

በብሄራዊ ባንክ ዛሬ ከቀረበው 125 ሚሊየን ዶላር ፈላጊ ያገኘው 120 ሚሊየኑ ብቻ ነው 5 ሚሊየኑ ተመለሰ። ጨረታው ላይ የተሳተፉት ሃያውም ባንኮች ተሳክቶላቸዋል። የጨረታው አማካይ ሬት ካለ...
09/09/2026

በብሄራዊ ባንክ ዛሬ ከቀረበው 125 ሚሊየን ዶላር ፈላጊ ያገኘው 120 ሚሊየኑ ብቻ ነው 5 ሚሊየኑ ተመለሰ።

ጨረታው ላይ የተሳተፉት ሃያውም ባንኮች ተሳክቶላቸዋል።

የጨረታው አማካይ ሬት ካለፈው ትንሽ ጭማሪ አሳይቷል ከ160.20 ወደ 160.53

በአዲሱ የ CBE Fast Loan 10,000 ብር መበደር የሚፈልግ (የሚችል) ሠው በአንድ ወር እና በሁለት ወር ለመክፈል ስንት እንደሚሆን ተመልከቱ።
09/09/2026

በአዲሱ የ CBE Fast Loan 10,000 ብር መበደር የሚፈልግ (የሚችል) ሠው በአንድ ወር እና በሁለት ወር ለመክፈል ስንት እንደሚሆን ተመልከቱ።

ብሔራዊ ባንክ ለነገ የ125 ሚሊየን ዶላር ጨረታ አዘጋጅቷል!
08/09/2026

ብሔራዊ ባንክ ለነገ የ125 ሚሊየን ዶላር ጨረታ አዘጋጅቷል!

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 38.7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንና የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ሰምተናል። ነገር ግን ከነዚህ ትላልቅ ቁጥሮች በስተጀርባ ያለው...
08/09/2026

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 38.7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንና የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ሰምተናል። ነገር ግን ከነዚህ ትላልቅ ቁጥሮች በስተጀርባ ያለው እውነተኛ ምስል ምን ይመስላል? የ'shega' ትንታኔ የሚያሳየን ሁለት አስገራሚ እውነታዎች አሉ፦

📉 1. ትርፉ በእርግጥ ከየት መጣ?
ባንኩ ያሳወቀው ይህ ከፍተኛ ትርፍ በአብዛኛው የተገኘው ከባንኩ መደበኛ የዕለት ተዕለት አሰራር (ብድር ከመስጠትና ወለድ ከመሰብሰብ) አይደለም። ይልቁንም መንግስት፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች መክፈል ያልቻሉትን የተበላሸ ብድር ከባንኩ ጫንቃ ላይ ስላነሳለት ነው። ይህ የመንግስት እገዛ ባይኖር ኖሮ፣ የባንኩ መደበኛ የስራ እንቅስቃሴ ወደ 3 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ያሳይ ነበር።

🥇 2. የተቀማጭ ገንዘብ ጭማሬውስ?
የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በአንድ ዓመት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል። ይሁንና ይሄ የሆነው ህዝቡ በድንገት ቁጠባ ስላበዛ አይደለም! እንደ አይ ኤም ኤፍ (IMF) መረጃ፣ ለዚህ ትልቁ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በስፋት ወርቅ መግዛቱ ነው። ንግድ ባንክ በወርቅ አምራች አካባቢዎች ሰፊ ተደራሽነት ስላለው፣ ብሔራዊ ባንክ ለወርቅ ግዢ የሚያወጣው ገንዘብ በቀጥታ የሚያርፈው እዚሁ ንግድ ባንክ ውስጥ ነው።

በአጭሩ፤ የባንኩ ቁጥሮች በወረቀት ላይ ሲታዩ እጅግ በጣም ያምራሉ፤ እውነታው ግን ከባንኩ መደበኛ የባንክ ስራ ጥንካሬ ይልቅ የመንግስት ትልቅ እገዛ እና የወርቅ ግብይት ያመጣቸው ናቸው።

ዝርዝር የፋይናንስ ትንታኔውን በሰፊው ለማንበብ
የ shega ን ድህረገጽ ይጎብኙ

Address

Addis Ababa
611-0011

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Banking Information -EBI- የኢትዮጵያ የባንክ መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share