01/06/2020
በቀን 22/9/2012 ዓ.ም የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጵ/ቤት በ2012 ዓ.ም በ9ኝ ወሩ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላላቸው የትምህርት ባለሙያወች እና የትምህርት ቤት አመራሮች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ ::
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arada sub-city w8 education office, Education, Gibi gebrele, Addis Ababa.
01/06/2020
በቀን 22/9/2012 ዓ.ም የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጵ/ቤት በ2012 ዓ.ም በ9ኝ ወሩ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላላቸው የትምህርት ባለሙያወች እና የትምህርት ቤት አመራሮች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ ::
28/05/2020
በቀን19/9/2012 ዓ.ም የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጵህፈት ቤት የመስከረም አፀደ ህፃናትና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከኬጅ እስከ 8 ኛ ክፍል ላሉ 613 ተማሪዎች ትምህርት በቤታቸው እየተሰጠ ያለውን ስራ ለማጠናከር ወርክ ሽት ;ለንፅህና መጠበቂያ የሚውል 3300 የንፅህና መጠበቂያ የሚውል የገላ ሳሙና ;እንዲሁም ለ100 ሴት ተማሪዎች ለንፅህና መጠበቂያ የሚውል ቅባት;ሞደስ እና ሳሙና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ለተማሪ ወላጆች አሰራጨ :: የት/ቤቱ ምክትል ር/መር አቶ ጣእመ ካሳይ ለዚህ መልካም ተግባር ላይ የተሰማሩትን የትቤቱን መምህራንና :አመራር እና ድጋፋ ሰጭ ሰራተኞችን እንዲሁም ለስራው አጋዥ የነበሩትን የወረዳ 08 ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊን እና ባለሙያወችን አመሰግነው ተማሪዎች በቤታቸው ሁነው ሳይዘናጉ ጤናቸውን በመጠበቅ ትምህርታቸውንም በቤታቸው ሁነው በአግባቡ መከታተል አለባችሁ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል :: በተጨማሪም የወረዳ 08 ትምህርት ጵ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ውብአንተ ገደፌ ፡ - በዚህ ፈታኝ ወቅት ላይ ሀላፊነታቸውን በብቃት እየተወጡ ያሉ የትምህርትቤቶቻችን አመራሮች; መምህራኖች ;ድጋፋ ሰጭ ሰራተኞች እና የትምህርት ባለሙያዎችን እንዲሁም የትምህርት ስራውን እያገዙ ያሉ የወረዳ 08 አስተዳደር አመራሮችን ከልብ በማመስገን የት/ቤቱ ማህበረሰብ እራሱን ከኮሮና ወረርሽኝ መጠበቅ እንዳለበት እና ወገኑንም ከወረርሽኙ ለመጠበቅ እና ለማገዝ እያደረጉ ያሉትን መልካም ስራ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል ::
13/05/2020
በቀን 05/09/2012 ዓም የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት መስከረም አፀደ ህፃናትና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኮሮና ባይረሰ ወረርሽኝ ምክንያት ተጎጅ ለሆኑ የወረዳው ነዋሪዋች እና አቅመ ደካሞች ለንፅህና መጠበቂያ የሚሆን 1000 ሽህ የገላ ሳሙናና ለምግብነት የሚውል የ5000 ሽህ ብር ዱቄት ድጋፍ አደረጉ !!
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት መስከረም አፀደ ህፃናትና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኮሮና ባይረሰ ወረርሽኝ ምክንያት ተጎጅ ለሆኑ የወረዳው ነዋሪዋች እና አቅመ ደካሞች ለንፅህና መጠበቂያ የሚሆን 1000 ሽህ የገላ ሳሙናና ለምግብነት የሚውል የ5000 ሽህ ብር ዱቄት ድጋፍ አደረጉ !!
የትምህርት ተቋሞቻችን የችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ መሳሪያዎች ናቸው የምንለው በምክንያትነት ነው !! ነገሩ እንዲህ ነው የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጵ/ቤት የመሰከረም 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰባችን ከcovd -19 ወረርሽኝ ለመጠበቅ እና ለመከላከል ከወረዳ አስተዳደሩ ጎን መሰለፍቸውን በተግባር አረጋገጡልን 1.መስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 150 ሺህ ብር የሚገመት 10 ሺህ የንጽህና መጠበቂያ ሳሙና እና ለአቅመ ደካሞች እና ለአረጋውያን ለምግብ አገልግሎት የሚውል የ10 ሽህ ብር መኮረኒ 2 .መስከረም 2ኛ ጀረጃ ት/ቤት ለአረጋውያንና ለአቅመደካሞች ለምግብ አገልግሎት የሚውል የ10 ሽህ ብር መኮረኒ እና እሩዝ በቀን 30/07/2013 ለኸረዳ አስተዳደሩ ገቢ ገቢ አድርገዋል
01/01/2020
10/11/2019
በቀን 28/02/2012 ዓ.ም የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ልዩ እና ደማቅ የትምህርት ጉባኤ አካሄደ ::በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጵህፈት ቤት ስር የሚገኙ የመንግሥት እና የቤተክህነት 1ኛ ና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት አመራሮች ፣መምህራን ፣ተማሪዎች ፣የተማሪ ወላጆች ፣የወረዳው ነዋሪዎች ፣የነየትምህርት ቤትና የወረዳው የወተመህ አባላት ፣የወረዳዉ የሴክተር መስሪያቤቶች አመራሮች ና ባለሙያዎች በጉባኤው ላይ መሳተፋቸውን አና በጉባኤው በ2011ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን የትምህርት ባለድርሻ አካላትን እውቅና የሚሰጥበት ፣ለ2012ዓ.ም የጽሕፈት ቤቱ፡እቅድ ላይም ጉባኤተኛው የጋራ መግባባት የሚደረስበት ፤ለእቅድ ስኬቱ በጋራ የሚሰራበትመሆኑን ፣መንግስትም ከምንግዜውም በላይ ለትምህርት ሴክተሩ ልዪ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን የወረዳው ዋና ስራአስፈፃሚ የሆኑት አቶ አቢዮት ጅፋራ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል ::የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንዳፍራሽ ለገሰ የጽሕፈት ቤቱን የ2011ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም ከተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር ጋር በማያያዝ ገላጭ በሆነ መልኩ በማቅረብ ጽህፈት ቤቱ በ2012ዓ.ም ሊሰራባቸው ያቀዳቸውን እቅድ በዝርዝር አቅርበዋል ::የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ውብአንተ ገደፌ ውይይቱን የመሩት ሲሆን ጉባኤተኞቹ ለአነሱአቸው ጥያቄዎች ጥያቄዎች ም አቶ ዉብአንተ መልስ ሰጥተው ጉባኤተኛው ያለምንም ልዩነት መግባባት ላይ ተደርሶበታል :: የወረዳ 08 አስተዳደር የድርጅት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሀላፊ እና የትምህርት ደጋፊ የሆኑት አቶ ሶፎንያስ ቦጋለ ፣የወረዳዉ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊየሆኑት አቶ ውብአንተ ገደፌ ፣የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት የወተመህ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ምስጉን በ2011ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው የትምህርት ተቋማት እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት እውቅና እና ሽልማት ሰጥተዋል ::በበ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከምንግዜውም በላይ የተማሪዎች ን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ያታቀዱ እቅዶችን በአግባቡ እንዲተገበሩ ለትምህርት ተቋሞቻችን ተከታታይ የሆነ ፤ከችግር የሚያወጣ እና ችግር ፈች የሆነ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ሞደል የትምህርት ተቋማትን መፋጠር ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ፣ውጤታማ የሆኑ የትምህርት ተቋማትን እናየትምህርት ባለድርሻ አካላትን እውቅና የመስጠት እና የማበረታታት ስርአቱን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትምህርት ጵህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ውብአንተ ገደፌ በመዝጊያ ንግግራቸው ገልጸዋል ::በተጨማሪም ትምህርት ጽህፈት ቤቱ በ2011ዓ.ም ለነበሩት የተሻለ አፈጳጸሞችበየደረጃው ያለው የትምህርት ባለድርሻ አካላት የነበረው አስተዋጽኦ ከፍተኛም እንደነበር በመግለጽ ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት በተለይም የትምህርት ሴክተሩ ቁልፍ ተግባር የሆነውን ሁለንተናዊ ስብእናቸው የተሟላ ትውልድ የማፍራት ተግባራችን አንግበን በየደረጃው ያለን የትምህርት ባለድርሻ አካላት አንድ በመሆን ሳንገፋፋ የየድርሻችንን በመውሰድ እና በመተግበር ጉልህ ሚና እንደሚጠበቅ በማሳሰብ እና ጉብአይተኛዉን በማመስገን የእለቱ የትምህርት ጉባኤ ተጠናቅቆአል ::
08/11/2019
በቀን 28/2/2012 ዓ.ም የአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ጉባኤ አካሄደ
26/10/2019
በቀን 15/2/2012 ዓ.ም የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የመሰከረም አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ ለማስቀጠል ፣የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር በማሻል ከተማሪ ወላጆች ጋር ምክክር ተጀመረ
21/10/2019
የአራዳ ክ/ከ ወረዳ 08 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የመስከረም አፀደህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ በቀን 10/2/2012 ዓ.ም በይፋ ተጀመረ ::
የአራዳ ክ/ከ ወረዳ 08 አስተዳደር ትም/ት ጽ/ቤት የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 6 የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የትምህርት ሰራውን እየሰራ መሆኑን የወረዳ 08 ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ውብአንተ ገደፌ ገልፀው ፦
የትኩረት አቅጣጫዎቻቸውም 1.የትምህርት ጥራት አሀድ ማጠናከር 2.የትምህርት ሽፋን ፣ተደራሽነትና ፍትሀዊነት ን ማሳደግ 3.የትምህርት ውስጣዊ ብቃት ማሻሻል 4.የትምህርት ጥራትን ማሻሻል 5.የተቋማትና የሰው ሀይል አቅም ግንባታ 6.የትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰራር ስርአትን ማሻሻል መሆናቸውን ገልፀው እነዚህ ን የትኩረት አቅጣጫዎች ብቃት ለመተግበር እና ለመወጣት በየጀረጃው ያሉ የትምህረት ባለድርሻ አካላትን ያላሰለሰ ጥረት የሚጠየቅ መሆኑን ገልፀዋል :: -በአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በተጠናከረ ሁኔታ በመተግበር የትምህርት ጥራት የተረጋገጠበት ና በልማት ፣በዲሞክራሲ ፣በመልካም አስተዳደር ግንባታ ሚና በመጫወት ሀገራችንን መጀመሪያ ደረጃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ዜጎችን ለማፍራት በጋራ እንስራ ብለዋል ::