ጠይም ቴክ እና ሚድያ

ጠይም ቴክ እና ሚድያ

Share

ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ዜና እና መረጃ ምንጭ ?

Photos from ጠይም ቴክ እና ሚድያ's post 12/07/2022

የጀምስ ዌብ ቴሌስኮፕ አስገራሚ የሆኑ የመጀመሪያ ምስሎችን መላክ ጀምሯል።

02/07/2022

ባሳለፍነው ማክሰኞ አሽከካሪ አልባዎቹ የክሩዝ ሮቦታክሲዎች በአንዴ መስራት በማቆማቸው የሳንፍራንሲስኮ ጎዳናዎችን ለሰአታት ዘግተው ቆይተዋል።
======================
ማክሰኞ ምሽት የሳንፍራንሲስኮ ጎዳና ምን እንደሆኑ እንኳን ሳይታወቅ ድንገት በቆሙ የክሩዝ ኩባንያ አሽከካሪ አልባ መኪናዎች ተዘግቶ ነበር። የኩባንያው ሰራተኞች መጥተው በእጅ እየነዱ እስከሚወስዷቸው ድረስ ለጥቂት ሰአታት ጎዳናውን ዘግተው ቆይተዋል። ይህ ደግሞ አሽከርካሪ አልባ መኪኖች በገሃዱ አለም ሲተገበሩ አሁንም ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ነው።
በጄኔራል ሞተርስ እና በሆንዳ የሚደገፈው ክሩዝ ከየካቲት ወር ጀምሮ ቴክኖሎጅውን በሳን ፍራንሲስኮ ሲሞክር የቆየ ቢሆንም የንግድ ሮቦታክሲ አገልግሎትን ባለፈው ሳምንት ነው ጀመረ። መኪናዎቹ ምንም አይነት የአደጋ ግዜ አሽከርካሪ በዉስጣቸው የሌለ ሲሆን፣ በውስን ሁኔታዎች ብቻ እንዲሰሩ ተደርጓል። ይህም የአየር ሁኔታው ምቹ በሆነበት እና ትራፊኩ ቀለል በሚልበት ከምሽቱ 4 ሰዐት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዐት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የታሰበ ሲሆን በተጨማሪም በሰዐት ከ30ማይል ባልበለጠ ፍጥነት የሚሽከርከሩ ይሆናል።
የክሩዝ ቃል አቀባይ ለTechCrunch በሰጡት መግለጫ፣ ክስተቱን አምነዋል፣ ነገር ግን ለምን እንደተከሰተ እና ችግሩ ለወደፊቱ እንደገና ሊከሰት እንደሚችል ምንም ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። “በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አንዳንድ ተሽከርካሪዎቻችን አንድ ላይ እንዲሰባሰቡ ያደረገ ችግር አጋጥሞናል።” ብለዋል ቃል አቀባዩ፣ አከል አድርገውም “መፍትሄ ያገኘ እና ምንም አይነት ተሳፋሪ ላይ ተጽኖ ባይደርስም፣ ለተጉላላ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን።” ብለዋል።
የክሩዝ አሽከርካሪ አልባ መኪኖችን አስመልክቶ የመጀመሪያው ጥፋት አይደለም፣ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ የትራፊክ ፖሊስ የክሩዝ ሮቦታክሲን ለማስቆም ሞክሯል ምክኒያቱ ደግሞ በለሊት የፊት ለፊት መብራት ሳያበሩ በመሄድ ነው። በኋላም እንደተናገሩት፣ “ክስተቱ በሰው ስህተት የመጣ ነው።” ብለዋል። “የኛ መኪኖች እንደታሰበው ለትራፊክ ፖሊሱ ምቹ የሆነ ቦታን ፈልገው ዳር ይዘው በመቆም ምላሽ ሰጥተዋል።” ብሏል ድርጅቱ። ነገር ኝ ትራፊክ ፖሊሱ ወደ ክሩዝ መኪናው ቀርቦ በሩን ሊከፍት ሲሞክር አሽከርካሪ አልባ መኪናው እንደገና በመንቀሳቀስ ራቅ ብሎ የ አደጋ ምልክት እያበራ ሊቆም ችሏል። ትራፊኩ ፖሊሱም የክሩዝ ሰዎችን በማውራት ምንም አይነት ክስ ሳይጻፍባቸው በነጻ ለቋቸዋል።
========================
ቀን፡ 25/10/2014
&_ሚድያ
: - https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
: - https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
: - https://www.facebook.com/teyimtech

26/06/2022

ነገ ናሳ የሚያስወነጭፋትን ትልቅ ተልዕኮን የያዘችውን ጥንጥ ሳተላይት፣ የማስወንጨፍ ሂደቱን በቀጥታ መከታተል ይችላሉ። ይህች CAPSTOLE (Cislunar Autonomous Positioning System Technology Operations and Navigation Experiment) ኪዩብሳት (CubeSat) ከዚህ በፊት በጨረቃ ዙርያ ባልተሞከረ ምህዋር ላይ በማስገባት እና ሙከራ በማድረግ ለወደፊት ናሳ ይሄን ምህዋር እንዲጠቀም ለዋና ሳተላይቶች ለመጠቀም እንዲያስችለው ነው ይሄን ተልዕኮ ሚያደርገው።
ሳተላይቷ የምትወነጨፈው መቀመጫውን ኒውዚላንድ ባደረገው ሮኬት ላብ (Rocket Lab) በተሰኘው ትናንሽ ሮኬቶችን በሚያመርት ድርጅት ነው። አላማው ኪዩብ ሳቷን ቀድሞ በተወሰነላት a near rectilinear halo orbit ተብሎ በሚጠራው በጨረቃ አቅራቢያ ባለው ምህዋር ላይ ማስገባት ነው። ይህ ምህዋር ሳተላይቷን አንዳንዴ ወደ ጨረቃ የሚያቀርብ አንዳንዴ ደግሞ ከጨረቃ የሚያርቃት ውስብስብ ምህዋር ነው። ይህ ምህዋር ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ አልዋለም ነበር ስለዚህ CAPSTONE ሳተላይት እየተላከ ያለው እሱን ለመፈተሽ እና በንድፈ ሀሳብ እንደሰራው በተግባር የሚሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።
የማስወንጨፍ ሂደቱን ተከትሎ፣ ሮኬቱ ሳተላይቷን ከ6 ቀን በኋላ ይለቃታል። ከዚያም ሳተላይቷ የታቀደላት ምህዋር ላይ ለመድረስ 4 ወራትን ትጓዛለች። በዚህም ምህዋር ከገባች በኋላ ለ6 ወራት መረጃን እየሰበሰበች በዚህ ምህዋር ላይ እንደምትቆይ ይታሰባል። ምህዋሩን ከመሞከር በተጨማሪም፣ ለወደፊት የጨረቃ ተልዕኮዎች ሊያገለግሉ የሚችሉ እንደ ከምድር ጋር ግንኙነት (communications with Earth)፣ እና (spacecraft-to-spacecraft navigation system) አይነት ቴክኖሎጂዎችን የመሞከር ተልኮም ትይዛለች።
የማስወንጨፍ መርሃግብሩ ነገ ሰኞ ሰኔ 20 በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ልክ ከቀኑ በ7 ሰዐት የሚጀምር ሲሆን፣ በናሳ ኦፊሴላዊ የዩትዩብ ገጽ በቀጥታ ይተላለፋል። የቀጥታ ስርጭቱን ማስፈንጠርያ ለጠይም ቴክ ተከታዮች ከስር አስቀምጠንላቹሃል። ከተወነጨፈችም በኋላ የ CAPSTOLEን ሂደት በ NASA’s Eyes website መከታተል ይችላሉ።

https://www.youtube.com/watch?v=JGx400xCDVY

=======================================
ቀን፡ 19/10/2014
&_ሚድያ
: - https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
: - https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
: - https://www.facebook.com/teyimtech

16/06/2022

የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች የተቆረጡ ሰዎች በአይምሯቸው ብቻ ሚያዟቸው የሮቦት ክንድ ሰርተዋል።
================================
የምርምር ቡድኑ የአይምሮ ንባብን (mind-reading) በሰውሰራሽ ልህቀት (Artificial Intelligence(AI)) እና እሌክትሮኒክስ እውን አድርጎታል። ተመራማሪዎቹ ያበለጸጉት ሰው ሰራሽ የሮቦት ክንድ፣ በተቆረጡ ሰዎች ላይ ከተገጠመ በኋላ ጡንቻቸውን ሳይጠቀሙ በጭንቅላታቸው በማሰብ ብቻ ማንቀሳቀስ የሚችሉት አይነት ነው።
አሁን ገበያ ላይ ያሉት ሰው ሰራሽ አካላት (እግር ወይም ክንድ) መልዕክት ከትከሻ ወይም ክንድ በሚወስዱ ገመዶች (ኬብሎች) የተሰሩ ሲሆን፣ በጣም ዘመናዊ የሚባሉት ደግሞ ደህና ከሆነው የታካሚ አካል ዉስጥ ስውር የቱንቻ እንቅስቃሴዎችን የሚያነቡ ሴንሰሮች የተገጠሙላቸው ናቸው። ነገር ግን፣ ሁለቱም አማራጮች አስቸጋሪ፣ ለመረዳት የማይቻሉ እና የተቆረጡ ሰዎች (ታካሚዎች) ሰውሰራሽ አካላቱ እንዴት ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ለማወቅ ወራት ልምምድ ሊወስዱ ይችላሉ።
በዩኒቨርሲቲው የባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ተመራማሪዎች ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር በሰው ክንድ ውስጥ ካለው የፔሪፈራል ነርቭ ጋር የሚጣበቅ እና ሊተከል የሚችል ትንሽ መሣሪያ ፈጥረዋል። ከAI ኮምፑተር እና የሮቦት ክንድ (Robotic Arm) ጋር አንድ ላይ በመሆን፣ መሳሪያው የአእምሯችንን ሲግናል (Brain Signal) ይተረጉማል። ይህም ታካሚው በማሰብ ብእንደቻ እንቅስቃሴዎችን እንዲቆጣጠር ያስችለዋል።
በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ መንታ ከተሞች ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ፒ.ኤች.ዲ. ተመራቂው እና የድህረ ዶክትሬት ድግሪ ተመራማሪው ጁልስ አንህ ቷን ንጉዬን እንደሚለው “ገበያ ላይ ካሉት ከየትኛውም ሰው ሰራሽ አካል በላይ ለመረዳት ቀላል የሆነ ሲስተም ነው። ሌሎቹ ገበያ ባሉት ሰራሽ አካላት፣ ታካሚዎቹ ጣታቸውን ማንቀሳቀስ ቢፈልጉ፣ ክንዳቸው ላይ ያሉትን ጡንቻዎች አክቲቬት ለማድረግ ይሞክራሉ እንጂ ጣታቸውን ለማንቀሳቀስ ሲጀመርም አያስቡም ምክኒያቱም መሳሪያው የሚያነበው ጡንቻቸው ላይ ያለውን መልክት ስለሆነ። ያ ደግሞ ታካሚው ብዙ ልምምድ እና መማር አለበት። በኛ ቴክኖሎጂ ቀጥታ ሲግናሎችን ከአዕምሮ ስለምንወስድ፣ የታካሚውን ፍላጎት በቀላሉ ይረዳል። ታካሚው ጣቱን ማንቀሳቀስ ከፈለገ ማድረግ ያለበት ማሰብ ብቻ ነው።”

==============
ቀን፡ 09/10/2014
&_ሚድያ
: - https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
: - https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
: - https://www.facebook.com/teyimtech

10/06/2022

ቴሌግራም የማህበራዊ ሚድያ ለአንዳንድ አገልግሎቶች ተጠቃሚዎችን ማስከፈል ሊጀምር ነው።
==================================
የ ቴሌግራም ባለቤት ፓቬል ዱሮቭ ዛሬ እንደገለጸው ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ የፕሪሚየም ሰብስክሪፕሽን ( ከፋይ ተጠቃሚ) አገልግሎትን እንደሚጀምር የገለጸ ሲሆን አሁን በነጻ የሚገልገሉ ሰዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሌሌው ነው ብሏል።
በዚህ የክፍያ ስርዓት ውስጥ የማይከፍሉ ተጠቃሚዎች አንዳንድ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደማይችሉ ተነግሯል ነገር ግን ከፋዮች አዳዲስ አገልግሎቶችን ማገኘት የሚችሉ ሲሆን ለምሳሌ መጠናቸው ትላልቅ የሆኑ ፋይሎችን ምስሎችን እና ስቲከሮችን መላላክ ይችላሉ ተብሏል።
ዱሮቭ እንደተናገርው ይህ አገልግሎት የሚጀመረው በነጻ የሚገለገሉት ሰዎች ከሚያገኟችው ነባር አገልግሎቶች ባለፈ ተጨማሪ አገልግሎትን መስጠት እንዲቻል ነው ያለ ሲሆን " የክፍያ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ፍጥነት እና ፊዩቸሮችን ማግኘት ይቸላሉ "ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ዱሮቭ ቴሌግራም የ ማስታወቅያ አገልግሎትንም እንደሚጀምር የገለጸ ሲሆን " ቴሌግራም ፈንድ ማግኘት ያለበት ከ ተጠቃሚዎች እንጂ ከማስታወቅያ ገቢ እንደማይሆን ተስፋ አለኝ ብሏል።

03/09/2014
&_ሚድያ
:- https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
:- https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
:- https://www.facebook.com/teyimtech
:- https://vm.tiktok.com/ZMLL2d2v8/

06/06/2022

በሀገራችን እጅግ ትኩረት እያገኘ የመጣውን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት አስመልክቶ ከብራዊ ባንክ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ስለክሪፕቶ ከረንሲ ምንነት ለመረዳት ይህንን አድራሻ ይጎብኙ። https://www.facebook.com/103810378837077/posts/146468264571288/?app=fbl

06/06/2022

ቶዮታ ለመኖርያ ቤት የሚያገለግል የሃይል ማጠራቀምያ ባትሪን አስተዋውቋል።
==========================
ቶዮታ ሞተር ኮርፖሬሽን ያመረተውን ይህ ለመኖርያ ቤት የሚያገለግል ባትሪ አነስተኛ ዋጋ የሚያወጣ ሲሆን ከፍተኛ ግልጋሎት የሚሰጥ ነው ሲል ገልጾታል።
ይህ የባትሪ ዲዛይን ከኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ጋር ተመሳሳይ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ሲሆን ጃፓን ውስጥ በፈረንጆቹ ኦገስት ወር ላይ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
ይህ ባትሪ 5.5 ኪሎ ዋት ሃወር አቅም ያለው ሲሆን መኖርያ ቤትን በአዘቦት ጊዜም ሆነ በተፈጥሮ አደጋም ቢደርስ እንኳን ሃይል መስጠቱን አያቋርጥም።
በተጨማሪም ይህን ባትሪ ከጸሃይ ሃይል መሰብሰብያ ጋር በማገናኘት በቀንም ሆነ በማታ ሃይል ለማገኘት የሚያስችል ሲሆን 100 ቮልት ኤሲ ሃይል የሚሰጥ መሆኑ ተዘግቧል።

29/09/2014
&_ሚድያ
:- https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
:- https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
:- https://www.facebook.com/teyimtech
:- https://vm.tiktok.com/ZMLL2d2v8/

02/06/2022

ጃፓን ተመራማሪዎች ክብርወሰን የሆነ ፈጣን መረጃ ማስተላለፍያ ሰርተዋል።
=============================
አሁን ባለንበት ዘመን እንደ 5G የመሳሰሉ ፈጣን መረጃ ማስተላለፍያ ቴክኖሎጂዎች በኖሩንም የፋይበር ኦፕቲክስ ኬብል አሁንም ድረስ የኢንትርኔት ማስተላለፍያ መንገድ እንደሆነ ይታወቃል ። ታድያ የጃፓን ተመራማሪዎች የሰሩት በነባሩ በፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ የሚሰራ ፈጣን መርጃ ማስተላለፍያ ዘዴ ከቤተ ሙከራ ባለፈ አሁን ባሉት የኢንተርኔት ማስተላለፍያ ገመዶች ላይ መተግበር የሚችል ነው።
የጃፓኑ ብሄራዊ መረጃ እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (NICT) ተመራማሪዎች በሰኮንድ 1.02 ቴትራ ባይት መረጃን 51.7 ኪ.ሜ ርዝማኔ ባለው የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ ማስተላልፍ ችለዋል ይህም ማለት በስኮንድ 127500 ጊጋ ባይት መረጃ መላክ ያስችላል ማለት ነው።
ባሳልፍነው የፈረንጆቹ 2020 ዲሴምበር ወር ላይ እነዚህ የ NICT ተመራማሪዎች 1ፔትራ ባይት መረጃን በሰኮን መላክ ችለው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከአመት በኋላ ደግሞ ክብረወሰን የሆነውን ይህን በሰኮንድ 1.02 ቴትራ ባይት መረጃን መላክ ቸለዋል።

16/09/2014
&_ሚድያ
:- https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
:- https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
:- https://www.facebook.com/teyimtech
:- https://vm.tiktok.com/ZMLL2d2v8/

Photos from ጠይም ቴክ እና ሚድያ's post 01/06/2022

የግንቦት ወር ታላላቅ ፈጠራዎች
=================================
በእያንዳንዱ ወር መቼስ የሰው ልጅ ያበረከታቸው የቴክኖሎጂም ይሁን ሌሎች ፈጠራዎች በታሪክ መዝገብ ላይ አይጠፉም። ያለፈውን ወር ፈጠራዎች መራርጠን በቻናላችን ላይ መለጠፋችን ይታወሳል። የዚህን ወር ፈጠራዎች ደግሞ መራርጠን እንደሚከተለው አቀረብንላቹ። የተጠቀሱት ቀኖች በሙሉ እንደአውሮፓውያን የዘመን ቀመር አቆጣጠር መሆኑን ልብ ይሏል።
1. ግንቦት 1፣ 1888 ስመ ጥሩ የቴክኖሎጂ ተመራማሪ ኒኮላ ቴስላ በኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ “Electric Power Transmission” ፈጠራው የባለቤትነት መብት የተሰጠው ልክ በዚህ ቀን ነበር።
2. ግንቦት 3፣ 1831 ጂም ማኒንግ ለሰራው የሳር ማጨጂያ ማሽን የባለቤትነት መብት የተሰጠው ቀን ነው። ይህ ማሽን ግን ለመጀመሪያ ግዜ የተሰራው እና ባለቤትነት መብቱንም ያገኘው፣ ኤድዊን ቢርድ በዲንግ ነው።
3. ግንቦት 4፣ 1943፣ ኢጎር ሲኮርስኪ በሰራው የሄሊኮፕተር መቆጣጠሪያ (Helicopter control) የባለቤትነት መብት አግኝቷል። ሲኮርስኪ ቋሚ ክንፍ ያላቸው (Fixed-Wing) እና ባለብዙ ሞተር (Multi-Engined) አውሮፕላኖች፣ ውቅያኖስን እንደጀልባ ማቋረጥ የሚችሉ እና እንዲሁም መብረር የሚችሉ (Flying Boats) ጀልባዎች እና ሄሊኮፕተሮች ፈጠራውም በደንብ ይታወቃል።
4. በግንቦት 10፣ 1752 ቤንጃሚን ፍራንክሊን መብረቅ እሌክትሪሲቲ መሆኑን የሚያረጋግጥበት የመጀመሪያውን የመብረቅ መከላከያ “Lightning rod” የሞከረበት ቀን ነው። ፍራንክሊን እንደምናውቀው የመብረቅ መከላከያ (lightning rod)፣ በወቅቱ ከነበረው የተለየ የእሳት መሞቂያ (iron furnance stove)፣ ለአይን ችግር ለነበረባቸው መፍትሄ የሆነው መነጽር (bifocal glasses) እና ኦዶሜትር “Odometer” (በማንኛውም ተሽከርካሪ ዳሽቦርድ ላይ የምናገኘው፣ መኪናው ምን ያህል ርቀት እንደሄደ የሚያሳይ መሳሪያ) ፈጠራ ባለቤትም ነበር።
5. ግንቦት 15፣ 1718 የለንደኑ ጠበቃ ጄምስ ፐክል፣ የመጀመሪያውን አውቶማቲክ የቶር መሳሪያ “Machine Gun” ፈጠረ።
6. ግንቦት 19፣ 1896 የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ማቅለጫ “Electric Furnance” በኤድዋርድ አቼሰን ተሰራ። ይህ ማቅለጫ እጅግ በጣም ጠንካራ (Hard) የሆነውን “Carborundum” ለማቅለጥ አገልግሎት ይውላል።
7. ግንቦት 25፣ 1948 አንድሪው ሞየር ፔንሲሊን በብዛት በማምረት ሂደት የፈጠራ መብት ባለቤት ሆኗል።
8. ግንቦት 27፣ 1796 የመጀመሪያው ፒያኖ በጄምስ ማክሊን ተሰራ።
==============
ቀን፡ 24/09/2014
&_ሚድያ
: - https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
: - https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
: - https://www.facebook.com/teyimtech

30/05/2022

ቮልስ ዋገን ኩባንያ በ 2025 በኤሌክትሪክ መኪና ሽያጭ ከቴስላ ለመብለጥ እንደሚሰራ አስታውቋል።
=====================================
ቮልስ ዋገን ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና ሽያጭ ገበያ እየተሳካለት የመጣ ይመስላል። ኩባንያው ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2021ዓ.ም ብቻ ቁጥራቸው 452,900 የሚደርሱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እና 310,000 የሚያህሉ ሃይብሪድ መኪኖችን በአለም ዙርያ መሸጥ ችሏል።
የኩባንያው አለቃ ሀርበርት ዳይስ የአለማችን የኤሌክትሪክ መኪና ሽያጭ እየመራ ከሚገኘው ከቴስላ ኩባንያ በፈረንጆቹ 2025 ላይ መሪነቱን ለመረከብ ማቀዱን ተናግረዋል።
" ቴስላ ኩባንያ በኤሌክትሪክ መኪና ሽያጭ ቁጥር አንድ ነው" ያሉት ዳይስ "ቮልስ ዋገንም እግር በግር እየተከታተለ በ 2025 ላይ በኤሌክትሪክ መኪና ገበያ ላይ ቀዳሚ ይሆናል " ብለዋል ።

18/09/2014
&_ሚድያ
:- https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
:- https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
:- https://www.facebook.com/teyimtech
:- https://vm.tiktok.com/ZMLL2d2v8/

26/05/2022

JOBY የ አቪዬሽን ኩባንያ የኤሌክትሪክ ታክሲ አገልግሎት ለመጀመር ጫፍ መድረሱን ገለጸ።
====================================
በሰሜን ካሊፎርኒያ መቀመጫውን ያደረገው Joby የኤሌክትሪክ አየር ታክሲ ኩባንያ ከ ፌዴራሉ የአቬሽን አስተዳደር (FAA) የመጀመርያ ስርተፊኬት መቀበሉን አስታውቋል።
ኩባንያው አሁን ያገኘው Part 135 ሰርተፊኬት የFAAን የዲዛይን እና የደህንነት መስፈርቶች በማሟላቱ የተሰጠው ሲሆን ወደፊት ተሳፋሪዎችን ጭኖ የተሟላ የአየር ታክሲ አገልግሎት ለመስጠት ሁለት ተጨማሪ ሰርተፊኬቶች እንደሚቀሩት ታውቋል።
የJoby ኩባንያ የኤሌክትሪክ አውሮፕላኖች 6 ተሽከርካሪ ክንፎች (Rotor) ያላቸው እና ፓይለቱን ጨምሮ 5 ተሳፋሪዎችን መያዝ የሚችሉ ሲሆን አውሮፕላኑ ሲነሳ ማኮብኮብ ሳያስፈልገው ቀጥታ ወደላይ (Vertical takeoff) እንደሄሌኮፕተር የሚነሳ ነው።
ኩባንያው እንዳለው ይህ አወሮፕላን ታክሲ 200 ማይል በሰአት በሆነ ፍጥነት መጓዝ የሚችልና በአንድ ባትሪ ሙሌት እስከ 150 ማይል መጓዝ የሚችል ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም እንደኩባንያው አገላለጽ ይህ ታክሲ አሮፕላን ከነባሮቹ የነዳጅ አውሮፕላኖች በ 100 እጥፍ ያነሰ ድምጽ የሚያወጣ ሲሆን በፈረንጆቹ 2024 ላይ ሙሉ ለሙሉ ስራ እንደሚጀምር ገልጿል ።
ይህ ኩባንያ በፈረንጆቹ 2009 ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከ ቶዮታ ፣ ኢንቴል ጨምሮ የተለያዩ ኩባንያዎች 690 ሚልዮን ዶላር ፈሰስ ተደርጎበታል።

18/09/2014
&_ሚድያ
:- https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
:- https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
:- https://www.facebook.com/teyimtech
:- https://vm.tiktok.com/ZMLL2d2v8/

23/05/2022

ኤሎን መስክ በዚህ አመት ብቻ 69 ቢልዮን ዶላር አጥቷል።
===============================
የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ኤሎን መስክ ከጠቅላላ ሃብቱ በዚህ አመት ብቻ 69 ቢልዮን ዶላይ ያህሉን ማጣቱን የብሉምበርግ ዘገባ አስታወቋል።
መስክ ያጣው ይህ ገንዘብ ትንሽ የማይባልና የአለምን ረሃብ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ከሚያስፈልገው ገንዝብ እጅግ የበለጠ ቢሆንም ነገር ግን ኤሎን መስክን የአለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር ሰው ከሚለው ደረጃው አላወረደውም።
የኤሎን መስክ ያሁኑ ሃብት 200 ቢልዮን ዶላር ሲሆን ይህ ከ አማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ጠቅላላ ሃብት 131 ቢልዮን ዶላር ሃብት በእጅጉ የበለጠ ነው።
መስክ አሁን ለገጠመው የገንዘብ ኪሳራ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም አብዛኛውን ገንዘብ ያከሰረው ቴስላ ኩብንያ ሲሆን ይህ ኩባንያ ከኤሎን መስክ የግል ሃብት ላይ 12.3 ቢልዮን ዶላር እንዲከስር አድርጎታል።

16/09/2014
&_ሚድያ
:- https://www.youtube.com/channel/UC1zDq930ZT9zsdIQeV3Q8dw
:- https://t.me/+FA1Na8uBDicyNWI0
:- https://www.facebook.com/teyimtech
:- https://vm.tiktok.com/ZMLL2d2v8/

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Addis Ababa