ብሩህ ትውልድ Biruh Tiwilid

ብሩህ ትውልድ Biruh Tiwilid

Share

we make our habits first then they make our destiny!!

04/03/2021

Coming soon!!

Google Forms - create and analyze surveys, for free. 15/01/2021

ብሪቲሽ ካውንስል ክሪኤቲቭ ፊውቸርስ 2.0 አዘጋጅቷል።

ከሌሎች የጥበብ ባለሙያዎች ጋር ትብብር የሚጥይቅ የጥበብ ንድፈ ሃሳብ አለዎት?
ካለዎት፤ እባክዎን ማንበብ ይቀጥሉ!

ክሪኤቲቭ ፊዩቸርስ በመጪው የካቲት ለአንድ ወር የሚቆይ የስነጥበብ ፈጠራ ወር በሚል የተሰየመ ፕሮግራም በከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል ተዘጋጅቷል፡፡ ሀሳቡ ቀላል ነው፤ በዚህ ዝግጅት ተሳታፊዎች በቂ ቦታ እና መሳሪያ ቀርቦላቸው በንድፍ ሀሳብ ደረጃ ያለ የጥበብ ሀሳባቸውን እውን ያደርጉበታል።

ስለ ክሪኤቲቭ ፊዩቸርስ 2.0 የበለጠ መረጃ ከፈለጉ ይህንን ድረ ገጽ ይጎብኙ፡ www.cutt.ly/HjuyVSG

አስፈላጊውን መረጃ ካነበቡ በኋላ እባክዎን ይህንን ቅጽ በመሙላት እስከ ረቡዕ ጥር 12 ቀን 2013ዓ.ም. ያመልክቱ። በአካል ለማመልከት ከፈለጉ በብሪቲሽ ካውንስል ወይም በከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል በመገኘት ማመልከቻዎን ገቢ ያድርጉ።

የተመረጡትን ንድፈ ሀሳቦች ለማበልጸግ የሚችሉት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሆነ በማወቅ በዚሁ ጊዜ ሊጠናቀቅ የሚችል፤ በአንድ ቦታ ሊሰራ የሚችል ምጥን ያለ ሀሳብ መሆኑን ያረጋግጡ። ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ የሚያስፈልጓቸውን መሳሪያዎች ሲዘረዝሩ በሀገር ውስጥ የሚገኙ መሳሪያዎች መሆናቸውን ያረጋግጡ።

ቀድመው ያመለከቱ ተወዳዳሪዎች የተሻለ የመመረጥ ዕድል ስላላቸው ቀደም ብለው ያመልክቱ። መልካም ዕድል!

Google Forms - create and analyze surveys, for free. Create a new survey on your own or with others at the same time. Choose from a variety of survey types and analyze results in Google Forms. Free from Google.

Naomi Girma Voted 2020 U.S. Soccer Young Female Player of the Year 24/12/2020

ታዳጊዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ተሰጦአቸውን እንዲያዳብሩ መርዳት የወደፊት ህልማቸውን በጊዜ እነዲጀምሩት ጥርጊውን ማመቻቸት ነው ….. እንኳን ደስ አለሽ ናኦሜ ግርማ …….. ታዳጊ ወጣቶችን በበጎ ልማዶች ባነጽናቸው ቁጥር ነጋቸው ብሩህ እንዲሆን ውለታ አየዋልን እንደሆነ እንወቅ፡፡ …… ብሩህ ትውልድ…….

Naomi Girma Voted 2020 U.S. Soccer Young Female Player of the Year Under-20 USWNT Captain and Stanford Star Helped Lead USA to Since-Cancelled FIFA U-20 World Cup

19/12/2020

********************** እኔ ማን ነኝ?***********************

የሁልግዜ ጓደኛህ ነኝ ፡፡ በጣም ጠቃሚ ረዳት ወይንም በጣም ጎጂ ልሆን እችላለሁ፡፡ ወደ ፈለከው ስኬት መድረሻ መንገድ ነኝ ወይንም ውድቀትህን ላፋጥን እችላለሁ፡፡ ሁሌም ግን ባንተ ትእዛዝ ስር ነኝ፡፡ ሁሉንም ነገር ጀምረህ አሳየኝ እንጂ በፍጥነትና በትክክለኛው መንገድ እፈፅመዋለሁ፡፡
በቀላሉ ልጠመዘዝ ስለምችል ጠንከር አድረጎ መያዝ ያስፈልገኛል፡፡ አንድ ነገር እንዴት እንደሚደረግ ካሳየኸኝ በፍጥነት መማርና እንዳሳየኸኝ ማድረግ እችላለሁ፡፡ የስኬታማና ታላላቅ ሰዎች ጥንካሬ ስሆን የተሸናፊና ደካሞች ደግሞ የውድቀታቸው ምክንያት ነኝ፡፡
ማሽን አይደለሁም ግን እንደማሽን ያለእረፍት እሰራለሁ ወይንም እንደሰው በማሰብ አከናውናለሁ፡፡ ተጠቅመህ ልታተርፍብኝ ትችላለህ ወይንም አራክሰህ ልትከስርብኝ ትችላለህ … ለኔ ጉዳዬ አይደለም፡፡
በርትተህ አሰልጥነኝና ተጠቀምብኝ ይህችን ምድር በእግርህ ስር ጥዬ አስገዛልካለሁ፡፡ ቸል ብለህ ከተውከኝ መጥፊያክ እሆናለሁ፡፡
እኔ ማነ ነኝ?

Photos from Ezedin Kamil - ኢዘዲን ካሚል's post 18/12/2020

Congratulations Ezedin Kamil , for your achievements and we see this as a beginning and sure to see you on an international stage. Thumbs up!!

Maryam Tsegaye, Canada, Physics, Winner: 2020 Breakthrough Junior Challenge 07/12/2020

Maryam Tsegaye, a 17-year-old 12 grade student became is the 1st Canadian to win $500,000 Cdn at the international Breakthrough Junior Challenge with her 3-minute video explaining quantum tunnelling 🤯🤯. The prize includes $250,00USD US scholarship for her, a new science lab for her school & cash prize for the teacher who mentored her. The competition asked students from around the world to create a video that explains a scientific principle to the public & about 5,600 students entered the competition. Here is her amazing winner video. https://www.youtube.com/embed/vg2rnjZ19PY

Maryam Tsegaye, Canada, Physics, Winner: 2020 Breakthrough Junior Challenge Learn more at https://breakthroughjuniorchallenge.org. The Breakthrough Junior Challenge is an annual competition for students, ...

The Seven habits 11/05/2020

****** በአሁኑ ሰአት ላለው ችግር ብቸኛው መፍትሄ…*******
ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ከሚፈጠረው ተጽእኖ መሃል ስለወደፊት ተስፋ ማስቆረትና በእቅድና በፕላን እንዳንኖር የመንፈስ አለመረጋጋት ዋነኛው ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት በአገራችን የተከሰተው ስለነገ አይደለም ስለዛሬ እንኳን በአግባቡ እንዳናስብ የመንፈስ ስብራት የሚያደርስ ወረርሽን ላይ ከፍተኛ የሆነ ፖለቲካዊ ቀውስ የሚመስል ብዥታ እየተስተዋለ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ከተለያዩ ወዳጆቼና የንግድ አጋሮቼ ጋር በሚኖረኝ ውይይት ውስጥ ከሚነሱ ነጥቦች ውስጥ በሃገር ውስጥ ስለእድገትና ለውጥ ለማቀድ ተስፋ አስቆረጭ ስሜትን የሚያብጸባርቁ ነጥቦች ይበዙበታል፡፡ የአሁኑ የሚብሰው የታባቱ ከዚህ አገር ወጥቼ ሰው እንደሚሆነው እሆናለው ለማለት እነኳን እንዳይቻል አለምን አከርካሪዋን የሰበራት የኮሮና ወረርሽኝ አሳሳቢና አስጊ መሆኑ ይበልጥ ፍርሃትና ተስፋ መቁረጥን ይጋብዛል፡፡
ስለተፈጠረው ችግርና የንግድ እንቅስቃሴ መዳከም እንዴት ያደርገን ይሆን የሚለው ስጋት ሳያንስ ፖለቲካዊ ሚዛኑ መዛባትና ባለፉት አምስት አመታት ያየነው የመንገዶች መዘጋት የሰዎች በሰበብ አስባቡ መሰደድና ሲከፋም ሞት በዚህ ወቅት አንሰራርቶና ጭራሽ ቀነ ቀጠሮ መያዝም መጀመሩ እንኳን ስለነገ አቅደን እንድንቀሳቀስ ሊያበረታታን ያለንም ነገር ላይ ለመስራትና የተሻለ እድገት እንዳንፈጥር አለመረጋጋትን ይፈጥራል፡፡
ይህንን ችግር ብንተነትነው በድቅድቅ ከመዋጥ የበለጠ ጭል ጭል የሚል ብርሃን እንኳን እንዳናይ ነው የሚያደርገን፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ለማስታወስ እወዳለሁ፡-
ምርጫ 97 እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ
ምርጫ 97 ላይ የነበረው አለመረጋጋትና የህዝቦች በግፍ መጨፍጨፍ የጎዳና ላይ አመጽ ብዙ ሰዎችን ንግዳቸውን አዘግቶ ስራቸውን አስፈትቶ ለስደት የዳረግ የምናስታውሰው ክስተት ነው፡፡ በዚን ወቅት ብዙ ሰዎች ከእቅዳቸው እነዲዘገዩና ተስፋ እንዲቆርጡ ሁኔታው በበቂ መልኩ ይጋብዝ ነበር፡፡ ጥቂት ሰዎች ግን ይህ ግዜ የሚልያፍና የተሻለ ቀን ሲመጣ ከምንም ከመጀመር የቻልነውን እንስራ፣ እናቅድ እንደውም በዚህ መሃል የሚፈጠር ከፍተኛ እድል ስልሚኖር እሱን መመልከት ይቻላል የሚል ቀና አመለካከትን ነበራቸው፡፡ ይህንንም ድህረ 97 የተፈጠሩ ሃብቶች፣ የስራ እድሎች እንዲሁም የቤትና የቦታ ባለንብረቶች ( ሙስናውና መሬት ወረራው እንዳለ ሆኖ) አሁን ላይ ወደኋላ ስንመለከተው በዛን ወቅት ልንሰራው አቅደን ተስፋ ቆርጠን የተውነው ስንት ነገር አለ ብለን እንድንቆጭ ያደርገናል፡፡
ምርጫ 2002 እና መዘዙ
ክምርጫ 2002 በኋላ የአቶ መለስ መሞትን ተከትሎ በተፈጠረው አድማና ብጥብጥ ብዙዎች ተሰደዋል ብዙዎች ህወታቸውን አጥተዋል ኢነቬስተሮች ንብረታቸው ተቃጥሏል ስፍር ቁጥር የሌለው ወጣት ታስሮ እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ይህም ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥና ይህች አገር አበቃላት ልትፈርስ ነው የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ልንገባ ነው የሚል ስጋት ከፍተኛ ነበር፡፡ አሁንም ላወሳ የምወደው በዚህ በሃል በእቅዳቸው የጸኑ እንዲሁም ለውጥ መስዋእት ቢያስፈልገውም ውጤቱ ግን ቢከፋም ቢለማም መርገቡ አይቀርም ያሉ ከለውጡ በኋላ የተፈጠረውን እድል ሲጠቀሙ ተመልክተናል፡፡
አሁንስ
አሁንም ደግሞ እላለሁ ሊነጋ ሲል ይጨልማልና በጨለማው ሳንዘናጋ እራሳችንን ለለውጥና ለሚፈጠረው አዲስ የሆነ እድል እናዘጋጀው እንጂ ተስፋ መቁረጥና ከእቅዳችን ማፈግፈግ ጊዜው ሲያልፍ ቁጭት ነው ትርፉ፡፡ ኮሮና እንደሆን የትም አገር ተከስቶ ጉዳት ፈጥሮ እንደሚልፈው እኛም ጋር ያልፋል፡፡ ፈጣሪ ብርታቱን እና ጽናቱን ሰጥቶን በአቅማችን ሁሉ ማድረግ የምንችለውን ጥንቃቄ አድርግን ጊዜውን ማሳለፍ ተገቢ ነው፡፡ ጎን ለጎን ግን በዚህ ምድር ላይ ባለን ቀሪ ዘመን ሁሉ ማድረግ የምንፈልገውን ነገር የተጠራንበትን አላማ ፈጽመን ለማለፍ እራሳችንነ በእቅድና በተስፋ መሙላት አንዱ ቁልፍ ነው፡፡
በአገራችን ላይ ያንዣበበ የሚመስለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንደደመና ብን ብሎ የሚጠፋ እና ፖለቲኮኞቻችንም ከመቼውም የበለጠ ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ እንደስከዛሬ ህዝቡን ብቻ ሳይሆን እነሱንም ዋጋ እንደሚስከፍላቸው የተረዱትይመስላሉ፡፡ እኛ እንደዜጋ እራሳችንን የተሻለ እድል የምናገኝበትን እቅድ እና ማንነት መገንባት እንጂ መዘናጋትና ጨለማው ሲነጋ ከዜሮ በመጀመር የበለጠ ለሽንፈት መዘጋጀት የለብንም፡፡
የሚሆነው ሁሉ መሆኑ ላይቀር ግዜያችንን በፍርሃትና በስጋት አናባክነው፡፡ ነገ የኔ ነው! ነገ ያንቺ ነው! ነገ ያንተ ነው! ነገ የኛ ነው! ነግን ዛሬ ለማድረግ ውሳኔው የኛ ነው፡፡

The Seven habits You can view and join right away.

08/05/2020

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሰው በኮሮና እና መሰል ችግሮች ሲሞት ሁላችንም ስለመጠንቀቅ ስናወራ አንድ ጥያቄ መጠየቅ ያለብን ይመስለኛል ለምንድን ነው ይህን ግዜ ተሻግረን መኖር ያለብን? የእውነት እስከ ዛሬ በእንደዚህ አይነት ስጋት ውስጥ ሳንኖር የኖርነው ህይወት በምንፈልገው መልኩ ነው ወይስ የማሟያ ኑሮ ነው የምንኖው?
እንደሆነ በሆነ አጋጣሚ መቼ እንደሆነ ባናውቀውም መሞታችን አይቀርም … ይህን ጽሁፍ ካነበብን በኋላ ለጥቂት ደቂቃዎች እስኪ ለምንድነው የምኖረው? የሚለውን እንጠይቅ፡፡

26/03/2020

እውነት የኮሮና ቫይረስ ፈጣሪ እንዲታደገን ከወደድን ይህንን ለማድረግ ቃል/ስእለት እንገባ
ብትወዱኝስ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ብሎናልና እንዳቅማችን ይህንን ቀን ለመውጣት አስቤዛችንን ስንሸምት እንደኛ ማድረግ የማይችሉ ዛሬን እኛ ብናደርግላቸው ነገ ለሌላው ይተርፋሉና ለእለት ጉርሳቸው እንኳን መሆን የማይችሉ አሉና እባካችሁ ከነዚህ ከታች ባሉት አቅማችሁ በቻለው ልባችሁ በፈቀደው ፈጣሪ እንዲራራልን መስዋእታችንነ እናቅርብ
1. የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000327016559
ERCS-COVID-19 Protection Project
2. በሃገር ፍቅር ትያትር ግቢ ውስጥ በአካል የምትለግሱትን በመያዝ
3. ወደ 444 በስልካችን ከታች በተዘረዘረው መሰረት መልእክት በመላክ
ለ1 ብር A
ለ15 ብር B
ለ10 ብር C
ለ25 ብር D
ለ50 ብር E
ለ100 ብር F
ለ300 ብር G
ለ500 ብር H
ለ1000 ብር J
4. አደባባይ ላልወጡ ችግረኛ ጎረቤቶቻችን ከሸመትነው ላይ የቻልነውን በማካፈል
ይህችን ቀን እንወጣት
መስጠት መብት ሳይሆን የሰውነት ግዴታ ነው፡፡
ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ ወዳጆቻችን እንዲለግሱ መልእክቱን እናድርስ

24/03/2020
Join group chat on Telegram 24/03/2020

ወዳጆቼ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችም እንዳየነውና እየሰማነው እንዳለነው የቫይረሱን መተላለፍ ለመቀነስ ያለው ብቸኛ አማራጭ ከማህበራዊ ንክኪ እራስን ማራቅ በመሆኑ አገራችን ከትምህርት ቤት እሰከ መንግስት መስሪያ ቤቶች መዝጋት ደርሳለች፡፡ በቀጣይ የግሉም ንግድ ከምግብ ነክ ሸቀጦችና መድሃኒት ውጪ በጥቂት ቀናት እንደሚዘጋ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ወቅት በጭንቀት የምናመጣው ነገር ስለሌለ አቅም ያለን በቻልነው መጠን የተቸገሩትን በመመገብ፣ የታመሙትን ቶሎ ህክምና እንዲያገኙ ጥንቃቄ የተሞላበት ትብብር እያደረግን፣ ፈጣሪ ይህንን ቀን እንዲያሳልፈን ተግተን በመጸለይ፣ እረሳችንን በእውቀትም ሆነ በስነልቦና ሊያጎለምስን የሚችሉ መጽሃፍትን በማንበብ፣ ክፋትና ጥፋትን ሳይሆን የሰው ልጅ ልቦናው በንጹህነትና በይቅርታ እንዲሞላ የሚያስተምሩ ፊልሞችን በማየት፣ ከሁሉም በበለጠ በዚህ አጋጣሚ ከቤተሰባችን ጋር በበለጠ ቅርበት፣ ቤተሰባዊ ፍቅር እና ትብብር በማጎለበት እንድናሳልፍ እየመከርንና እተመኘን በዚህ ገጽ ተስፋ፣ፍቅርና በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ጽሁችና ቪዲዮዎችን እየተጋራን እና እየተማማርን እንድናሳልፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
like and share or visit our telegram

Join group chat on Telegram

24/03/2020

የአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞች ከቤታቸው እንዲሠሩ የተላለፈው ውሳኔ የጤና፣ ፖሊስ፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ትራንስፖርት፣ መንገድ፣ ኮንስትራክሽን እና ደረቅ ቆሻሻ አገልግሎትን አይመለከትም ተባለ

**********************

ከወሳኝ የሥራ ሂደት ውጪ ያሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ዛሬ መወሰኑ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ውሳኔው የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎትን፣ የትራንስፖርት፣ መንገድ እና ኮንስትራክሽን ዘርፎችን እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ ማንሳት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን አያካትትም ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎች እና የፖሊስ አባላትም የተለመደ ህዝባዊ አገልግሎታቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታውቋል።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address

Kirkis Sub City Besides WFP Bambis
Addis Ababa
REGION14