አዲሱ መንገሻ በየነ

አዲሱ መንገሻ በየነ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አዲሱ መንገሻ በየነ, Addis Ababa.

02/02/2026
20/01/2026

በቅርብ ቀን ተስፋዬ እስከዚያ

05/01/2026

"ዳርዊን ስነ-ፍጥረትን ሲያጠና ከአንድ እውነት ጋር ተጋፈጠ። የጠፉ እና ከዚህ ዓለም በቁጥር የቀነሱ ወይም ድራሻቸው የሌሉ ፍጥረታትን ሲያይ አንድ መለያቸው መመሳሰል (adaptation) ማድረግ አለመቻላቸው ነበር። ጠንካራው አልነበረም የሕይወትን መከራ ማለፍ የቻለው። ፈጣኑ እንስሳ አልነበረም ሳይጠፋ የቀረው። አዳብት (adapt) ማድረግ የቻለው ብቻ ነበር የዘለቀው። የተፈጥሮን ኃይለኛ ማዕበል የተሻገሩት ነፍሳት ብቸኛ ባህሪያቸው በፍጥነት ራሳቸውን ከአካባቢያቸው ጋር ማመሳሰል እና መለወጥ መቻላቸው ነበር። እንጂ ጠንካሮችም ሆነ ፈጣኖቹም አልነበሩም።"

01/01/2026

㊙️መ ቅ ድ ም ።
►►►►►►►►
«ሀገር ያለ ሰው ምድረ በዳ ሆና ትኖር ይሆናል ። ሰው ግን ያለ ሀገር ሊኖር አይችልም ።ሀገር ምን እንደሆነች ሁላችንም እናውቅአለን ነገር ግን ሀገር የምትኖርበትን ዘዴ ገና አጥርተን
ያወቅነው አይመስለኝም። ስለእዚህም የአንድ ሀገር ሰዎች መሆናችንን እንድናውቀውና ለአንድነታችን መጠጊያ የሆነችውን እናታችንን ኢትዮጵያን ለማገልገለ ለማኖርና ለኑሮአችንም ለመሥራት የምንችለው በአንድ መንፈስ ስንሰለፍና በንጹሕ ሕሊና ፀንተን ስንተባበር ብቻ ስለሆነ ወደ እዚህም በቅንነት እንድንራመድ ስለሚአሻ የየአንድ አንዳችን
መንፈስ ከደካማነት ወደ ጽኑነት መለወጥ አለበት ። መተዛዘንን፤ መተሳሰብን፤ ጠንካራ መንፈስን ፤ቅን ባሕርይን ፍቅርን እርስ በእርሳችን መተዋወቅንና አለመናናቅን ማወቅ ይገባናል ። ይህም በመሀከላችን ከሌለ ምንም ሊኖር አይችልም ። ወደ መጥፎ መንፈስ የሚመራ ሁሉ መጥፎ ነገሮችን እያራባ ሌላውን ሁሉ ከትቦ እንዳይጐዳ ያሠጋልና በኑሮ ውስጥ ምን ምን እንዳሉ ተረድቶ ከአሁኑ መገታት
ያስፈልግ ይመስለኛል፤በአጭሩ ከገለጥኩ በኋላ አስፋፍቶ ማተቱን የሚመለከተው የአንባቢዎች አእምሮ እንደሚሆን
በማመን እተወውአለሁ ።ለመልካም ሥራ ይውል እንደሆነ በማለት ተስፋ ይህን ትንሽ መጽሐፍ ለውድ ሀገሬ ሰዎች
አበረክታለሁ ።»-ሌ/ጀነራል አብይ አበበ

18/11/2025

ባለ ራእይ መሪ በሚከተሉት ባሕርያት ሊገለጽ ይችላል::
 ያልኩት ካልሆነ ብሎ ክችች አይልም:: ከየትም ይምጣ ከየት የሚጠቅም ሃሳብ እስካለ ድረስ ሁሉንም በክፍት አእምሮና በቀና ልቦና የመቀበል ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የማስተናገድ ዓቅምም አለው:: በእኔ መቃብር ካልሆነ ሃሳቤ አይቀየርም አይልም:: የሚሠራ ከሆነ ይሞከራል፤ እንደማይሠራ ሲረጋጋጥ ይቋረጣል::
 ፈጥኖ አይፈርጅም:: ጥሩ ሃሳብን ያለጊዜውም አያጨናግፍም:: ለሁሉም በቂ እድልና ጊዜ ይሰጣል እንጂ::
 ውዳቂ የተባለውን ሃሳብ ውዳቂ ብሎ አይተወውም:: ከወደቀበት አንስቶ ከሌላ ውዳቂ ጋር አዳቅሎ ውበት ይዘራበታል እንጂ::
 ከአሉባልታና ግምት ይልቅ መረጃን እና እውነታን ያስቀድማል:: ጥልቁን ይመረምራል እንጂ ከላይ የሚያየውን ብቻ የሚያምን አይደለም::
 ችግር የመተንተን፤ የተበታተነውን የማገናኘት እና የማዋሓድ ችሎታው የላቀ ነው:: ምናባዊውን ከእውነታው ያገናኛል፤ የሚዛመዱበትንም መንገድ ይፈልጋል::
 ያልተሞከረ ሃሳብ፤ ያልተፈሸ አማራጭ፤ ሁሌም አዲስ መንገድና አዲስ መላ ከመፈለግ አያርፍም::
 የማይቻል የሚባል ነገርን ለምን ሊሆን አይችልም ብሎ ይጠይቃል እንጂ እንደ ብዙኋኑ በቀላሉ አሜን ብሎ አይቀበልም:: ብዙኋኑ የተስማሙበትን ነገር ብዙኋኑ ከተስማሙበትማ ምን ይደረጋል እኔ ባላምንበትም ከብዙኋኑ ሃሳብ እንዴት እወጣለሁ? የሚል ባለ ራእይ መሪ 29 አይደለም:: ሁሉንም ነገር የማወቅ ጉጉት አለው:: እውነቱ ላይ ሳይደርስ ተስፋ ቆርጦም አይተወውም:: መላምትን ሞገቶ እውነቱ ላይ ይደርሳል እንጂ::
 ችግር ሲከሰት በችግሩ ከመረበሽ ይልቅ ችግሩን በችግሩ መካከል ያሉ እድሎችን ያፈላልጋል:: ችግርንም ለመልካም እድልነት ተጠቅሞ የተሻለ ነገን ይፈጥራል:: በአስቸጋሪ ሁኔታ አሉታዊውን ሳይሆን አዎንታዊውን አጉልቶ የሚያይ ተስፋ ቆራጭ ሳይሆን ተስፈኛ ነው:: 1.3 የተስተካከለ ዕይታ “እንዲህ አልመሰለንም ነበር፤ አጭበርብረውናል፤ ባለ ራእይ መሪ
ትእዛዙ ካሣ

06/08/2025

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

አቤቱ ደውይ ነኝና ፈውሰኝ (መዝ ፮፥፪)
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በርዕሰ ገዳማት ወ አድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የእናቶችና የአባቶች አንድነት ገዳም የ፬ ቱ ጉባያተ መጻህፍት ምስክር ጉባኤ ቤት በባህር ዳር ከተማ በአይነቱ ልዩ የሆነ ጠቅላላ ሆስፒታል ለመገንባት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ 400 ሚሊዮን ብር በመጀመሪያ ዙር ለመሰብሰብ ታቅዶ የገቢ ማሰባሰብ ስራው ተጀምሯል ፡፡ እርስዎም ለሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት እውን መሆን በሚከተሉት የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች የበኩልዎን ድጋፍ እንዲያደርጉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡

በሒሳብ ስም ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የአራቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት

የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000680619488 / TANA KIRKOS GEDAM 4TU G/METSAHFT

ዳሽን ባንክ፡5020827358011

አቢሲኒያ ባንክ፡ 219553568

ዓባይ ባንክ፡ 2011111181981013

አሐዱ ባንክ፡ 0068829811701

የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ (መጽሐፈ ነህምያ 2:20)

ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር
+251 982 333 444
+251 983 333 444
+251 984 333 444

በመደወል ያግኙን!

04/08/2025

"የአርቆ አሳቢነት ክህሎትን ማሳደግ
1 በጥልቀት ማሰብና ማሰላሰል
2 ልማድን መሞገት
3 ዘመኑን መዋጀት
4 ባይሆንስ ማለት መቻል
ይሆናልን እንደወረደ ከመቀበል ይልቅ እንዴት? ለምን? ብሎ መጠዬቅና መመርመር መቻል (question assumptions) የአርቆ አሳቢነን ክህሎት ያሳድጋል:: “መጠዬቅ ያደርጋል ሊቅ”
5 ነገሮችን ማገናኘት : አንድን ጉዳይ ስንመረምር ጉዳዩ ጠቃሚ ነገር አለው ወይ? የትኛው ነው ጠቃሚው ነገር? የትኛውስ ጠቃሚ አይደለም? ጠቃሚው ነገር አስፈላጊነቱ ምን ያህል ነው? እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ምን ሊደረግ ባለ ራእይ መሪ 46 ይችላል? ምን አማራጮች ይኖራሉ? የሚሉትን ሁሉ መጠዬቅ መቻል ነገሮችን የማገናኘት ጡንቻን ያደረጃል::
6 ቀልብን መሰብሰብ
ቀልብን መሰብሰብ (mindfulness) ከትዝታ ወይም ስለ ነገ ከመጨነቅ ይልቅ ዛሬን ማሰብ መቻል ነው::
7 ማያ መነጽሩን መቀዬር: አንድን ችግር ለመፍታት የተለዬ አዲስ ዕይታ ያስፈልጋል እንኳን ጭንቅላት ቤት እንኳ ባዶ ሲሆን ያረጃልና ማሰብ፤ ማሰላሰልም የተሻለ ዕይታን ይፈጥራል:: አርቆ አሳቢነትም በእነዚህ ሁሉ ይገኛል::"

02/08/2025

"ትልቁን ስዕል የማዬት ዓቅም ሙሉ እውቀት መኖርንም ይመለከታል::
መሪ የአንድ ክፍል ሓላፊ ከሆነ ከሚመራው ክፍል አለፍ ብሎ ስለ
ድርጅቱ ጠለቅ ያለ እውቀት ያለው መሆኑ እንዲሁም ተቋሙን የሚመራ
ከሆነ ከውጭም ከውስጥም ተቋሙ ያሉትን እድሎችና ተግዳሮቶች፤
ተቀናቃኞቹንና አጋሮቹን ጠንቅቆ ማወቅ መቻልን ይጠይቃልና:: ትልቅ
ስዕል ማዬት ክልል እየመሩ ስለ አገር መጨነቅን፤ ዞን እየመሩ ስለ
ክልል መጨነቅን፤ ቀብሌ እየመሩ ስለ ዞን መጨነቅንም ይጨምራል::
አገር ሲመራም እርስ በርሱ በተሳሰረ ዓለም ቀጠናውን ያስባል፤
አኅጉሩን ያስባል፤ ዓለምን ያስባል::"ባለ ራእይ መሪ 34

24/07/2025

“መሪዎቹ ለስኬታማነታቸው ከጠቀማቸው አራት ነጥቦች
1) ውሳኔ አሰጣጥ (deciding with speed and conviction)
2) ውጤታማነት (Engaging for impact)
3) የለውጥ መሪ (Adapting proactively)
4) ታማኝነት ወይም ቃልና ተግባሩ የተስማማ (delivering reliabliy) ናቸው::
ታማኝነት ወይም ቃል የገባውን የመፈጸም ብቃት መኖር ለመሪዎቹ የስኬት ምንጭነው
ታማኝነት ለመሪነት ቁልፍ ነው
መተማመን የአንድ አገር ትልቅ ሀብት ነው
መተማመን ባለበት መግባባት አለ
መተማመን ባለበት መረዳዳት አለ
መተማመን ባለበት መቻቻል አለ
መተማመን ባለበት ፍቅር አለ
በአንጻሩም መተማመን በሌለበት አብሮ መኖር እንዴት ይቻላል? ማኅበራዊ መስተጋብር፣ መገበያየትም አደጋ ይገጥመዋል:: መተማመን በሌለበት ሰላምስ እንዴት ሊኖር ይችላል? መተማመን ሲጎድል ፍቅር ይቀዘቅዛል፤ ጥላቻ ይጎለብታል:: መተማመን ሲጎድል እውነትና ሐሰቱ እየተደበላለቀ ግራ መጋባት ይበዛል:: በአጠቃላይ ማኅበረሰብ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ነው:: አብሮ ለመኖርም ትልቁ ቁልፍ ጉዳይ መተማመን ነው ማለት ይቻላል:: ጨምሩበት” ከቅን መሪ እትም የተወሰደ

18/07/2025

"ቅንነት ከሰው ጋር ተግባብቶ ለመሥራትም ያስችላል:: ፍትሕንና
ለእውነትን ማድላትንም የሚያገናኛቸው ብዙ ነገር አለ:: ለፍትሕ
መቆም እውነትን መያዝ፣ ለእውነት ማድላትን ይጠይቃልና:: እውነትን
የሚያውቅ ለእውነት የሚያደላና ለእውነት የሚቆም መሪ በቆመለት
መርህ ዋጋ ቢያስከፍለውም እንኳ ለመርህ መቆሙ የሚጠበቅ ነው::
አገልጋይነትም የቅንነት ውጤት ነው ማለት ይቻላል:: ከቅንነት ፈሪሃ
እግዚአብሔር ይገኛል፤ ፈሪሃ እግዚአብሔርም ቅን ያደርጋል::"

Photos from አዲሱ መንገሻ በየነ's post 07/09/2024

ወንድማችን ይልቃል እንደአሳወቀን በታሪክ እንደሰማነው የሚያውቋቸው ሲመሰክሩ ብዙ ያልተነገረላቸው መለአከ ገነት ጥሩነህ ከመልካም ባህሪያቸው ጀምረው ይተርካሉ በቤተክርስቲያን እውቀት እና ጥበብ ድንቅ ተሰጥኦ እንደነበራቸው ይመሰክራሉ ከሞጣእስከ አዲስ አበባ በበ ታዕካ ነገስት ባዕታለማሪያም ገዳም ቤተክርስቲያንን በግንባር ቀደም በብቃት እንደአገለገሉ የሚያውቋቸው ይናገራሉ መልአከገነት ጥሩነህ ጌታሁን ሞጣ ካፈራቻቸው ሊቃውንት ውስጥ በግንባር ቀደምት የሚጠሩ እንደነበሩ ታላላቅ ወንድሞቻችን ነግረውናል። ስለዚህ የምንችል ሰዎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተን መፅሐፍን ብናስመርቅ ስለእሳቸውም ብናውቅ ለትውልድ የታሪክ ቅብብሎሽ ይጠቅማልና የምትችሉ እንድታገኙ ተጋብዛችኋል ይህን ድንቅ ስራ ለፍሬ ያበቃችሁ ወገኖች ትልቅ ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል በረከታቸው ይደርብን። 🙏🏾🙏🏾🙏🏾

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa