ፍቅረ ዘማሪያም - Fikre Zemariyam

ፍቅረ ዘማሪያም - Fikre Zemariyam

Share

Lifelong Educator , Christian , husband , father, teacher & St George FC Supporter.

16/06/2026

ከወንድሜ አብይ ጎን እቆማለሁ! ጀነራሉ

የኢትዮጵያ ዩቁርጥ ቀን ወዳጅ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ልጅ የዩገንዳ ዋና ጦር አዛዥ ጀነራል ሙኡዚ
" በትግራይ ሌላ ጦርነት እንዳይነሳ እለምናለሁ፣ የትግራይ ህዝብ በጣም እወዳቸዋለሁ ግን ጦርነት ሰልችቶናል። ጦርነት ከተነሳ ግን ወንድሜ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድን እደግፋለሁ። ከኢትዮጵያ ጎን ነኝ። "

16/06/2026

ሴኔጋሎች እንደ ጀግና እየተጫወቱ ነው👏

16/06/2026

የኢትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!!
___

1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡

4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
፫= የጡረታ መለያ ቁጥር
፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡

16/06/2026

A woman applied dark makeup during a live assembly and asked, “Am I Black now❓” before making the point: “If makeup cannot change race, then surgery cannot change gender.” The bold statement has gone viral and sparked intense debate.

16/06/2026

ሰበር ዜና

አሜሪካ ከኒውዚላንድ ጨዋታ በኋላ የኢራናዊውን አጥቂ ቪዛ ሰረዘች።

ኢራናዊ ተጨዋች መህዲ ቶራቢ ለቡድን አጋሮቹ ከተሰጠው ብዙ ጊዜ የሚያገለግል multiple- entry ቪዛ በተለየ በስህተት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል single-entry ተሰጥቶት ነበር።

ቪዛው ኢራን ከኒውዚላንድ ካደረገችው ጨዋታ በኋላ አገልግሎቱ አልቋል። ቶራቢ ከቀሪው የቡድን አባላት ጋር ከሎስ አንጀለስ በቲዋና ሜክሲኮ ወደሚገኘው የኢራን ጊዜያዊ የልምምድ ካምፕ አስቸኳይ ለመብረር ተገድዷል።

በአሁኑ ወቅት ኢራን ከቤልጂየም እና ከግብፅ ጋር ለምታደርጋቸው ቀጣይ የምድብ ጨዋታዎች ወደ አሜሪካ ተመልሶ እንዳይገባ በሕግ ተከልክሏል።

የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቶራቢ መመለስ እንዲችል ሌላ የብዙ ጊዜ ቪዛ ለማስፈቀድ ከአሜሪካ ባለስልጣናት እና ከፊፋ ጋር አስቸኳይ ይግባኝ ጠይቋል።

16/06/2026

የዶላር አማካይ ዋጋ 158.00 ብር ደረሰ፤ ከባለፈው ጋር ሲነፃፀር በ98 ሳንቲም ዝቅ ብሏል። በዚህም ዶላር እየቀነሰ መጥቷል።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 100 ሚሊዮን ዶላር አቀረበ

ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) ዛሬ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ቁጥር 23 ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ (Foreign Exchange Auction No. 23) የአንድ የአሜሪካ ዶላር የክብደት አማካይ ዋጋ 158.00 ብር መድረሱን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ይፋ ባደረገው ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ በዛሬው ዕለት በቀረበው የውጭ ምንዛሬ ላይ ከፍተኛ የፍላጎት መጠን ተመዝግቧል። ብሔራዊ ባንኩ ለዚህ ጨረታ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ቢሆንም፣ ከባንኮች በኩል የቀረበው አጠቃላይ የፍላጎት (የመጫረቻ) መጠን ግን ከእጥፍ በላይ በመሆን 236.30 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።

በጨረታው ላይ በአጠቃላይ 16 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 8ቱ ባንኮች ጨረታውን አሸንፈው የቀረበውን የውጭ ምንዛሬ መጋራት ችለዋል።

የዛሬው የጨረታ ዝርዝር ውጤት፦

1. ለጨረታ የቀረበው መጠን 100 ሚሊዮን USD

2. የቀረበው አጠቃላይ የፍላጎት መጠን 236.30 ሚሊዮን USD

3. የማሸነፊያ የክብደት አማካይ ዋጋ 158.0000 ብር/USD

4. የመቁረጫ ዋጋን157.9999 ብር/USD

5. ከፍተኛው የቀረበ ዋጋ 158.0000 ብር/USD

6. ዝቅተኛው የቀረበ ዋጋ 157.9900 ብር/USD

7. የተሳታፊ ባንኮች ብዛት:16 ባንኮች

8. ያሸነፉ ባንኮች ብዛት:8 ባንኮች

የዛሬው የጨረታ ውጤት የዶላር ዋጋ ካለፈው ጨረታ አንጻር መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱንና በባንኮች ዘንድ ያለው የዶላር ፍላጎት አሁንም በከፍተኛ ደረጃ መቀጠሉን አመላካች ሆኗል።

Via NBE

16/06/2026

ከፍተኛ ግብር እና ዝቅተኛ ገቢ የተማረውን የሰው ኃይል ሀገር ጥሎ እንዲሰደድ ወይም ከመንግስት መዋቅር እንዲወጣ እያደረገው በመሆኑ ይህንን ማሻሻያ ማድረግ የሀገርን ዕውቀት በሀገር ውስጥ ለማስቀረት ይረዳል

16/06/2026

ሊቀጣ ነው !

ፊፋ ኢራናዊው ተጫዋች መሐመድ ሞሄቢን ሊቀጣው መሆኑ ታወቀ።

ኢራን ከኒውዚላንድ ጋር ባደረጉት የምድብ ጨዋታ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ያሳየው ''ሽጉጥ መተኮስ'' የሚመስል የ ደስታ አገላለፅ ምክኒያት መሆኑም ታውቋል።

ከፊፋ የወጣ ይፋዊ መግለጫ እንዳመለከተው የደስታ አገላለፁ ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለውና ተገቢ ያልሆነ ባህሪ ሆኖ የተገኘ ሲሆን የፊፋ የዲስፕሊን ደንቦች የጣሰ ነው ተብሏል።

የኢራን ብሄራዊ ቡድን ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር ባላት ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ብሄራዊ ቡድኗ የጨዋታ ዕለት ብቻ በአሜሪካ ቆይቶ ዋና መቀመጫውን ሜክሲኮ ለማድረግ መገደዱ የሚታወስ ነው።

ኢራን የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከኒውዝላንድ ጋር 2 አቻ በማጠናቀቅ 1 ነጥብ አሳክታለች።

Photos from ፍቅረ ዘማሪያም - Fikre Zemariyam's post 16/06/2026

"ሕወሓትን የተቃወሙት የ76 አመት አዛውንት ታሰሩ"

በትግራይ ክልል የእንደርታ ተወላጅ የሆኑት የ76 ዓመቷ ነባር ታጋይ አኸዛ ሕሉፍ፣ በክልሉ ስላለው የፍትህ እጦት፣ የመልካም አስተዳደር እክል እና የፖለቲካ ብልሽት አስመልክተው ከሶስት ቀናት በፊት የሰጡት ቃለመጠይቅ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ በህወሓት ታጣቂዎች ታግተው መታሰራቸው ተሰማ።

የወረዳ 70 እንደርታ የፈለግማያት ጣቢያ ነዋሪ የሆኑትን ይህችን ጀግና እናት ለምን ተነፈስሽ? ለምንስ ተናገርሽ?'' በሚል ዛሬ መታሰራቸውን ተረጋግጧል። እንደ መረጃዎች ገለጻ ለእስራታቸው ዋነኛ ምክንያት የሆነው ''ለምን ልጆች ወደ ጦርነት ይገባሉ?'' በማለት ሰላማዊ ጥሪ ማቅረባቸውና እንደሌሎቹ የጦርነት ነጋሪት ለመጎሰም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ሲሆን፣ የቀድሞው ህወሓት እስከ እድሜ ልክ የሚያስቀጣ አፋኝ ህግ ማውጣቱ በሚታወስበት በዚህ ወቅት የ76 ዓመት አዛውንት እና ነባር ተጋዳሊትን ለአመለካከታቸው ሲል ማሰሩ ከፍተኛ ቁጣንና ትዝብትን እየቀሰቀሰ ይገኛል።

እስካሁንም እናት አኸዛ ሕሉፍ በታጣቂዎች ተወስደው የት ቦታ እንደታሰሩና አሁን ያሉበት ሁኔታ በትክክል አለመታወቁ ተገልጿል።

16/06/2026

''የሰላም አማራጭን ችላ ብሎ ወደ ውጊያ ከገባ፣ አየር ኃይላችን ጠላትን እስከወዳኛው ይሸኛል''ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ''

ጠላት የሰላም አማራጭን ችላ ብሎ ወደ ውጊያ ከገባ፣ አየር ኃይላችን የጠላትን ህልውና እስከወዲያኛው የሚያከስም አስተማማኝ መቺ ኃይል መሆኑን በተግባር ያረጋግጣል ሲሉ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተደምጠዋል።

ሀሳብዎን ያካፍሉን!

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Addis Ababa
Addis Ababa