10/09/2024
⭐️እንኳን ለ2017 ዓ.ም⭐️
አዲስ ዓመት በሠላም አደረስዎ!⭐️
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።
Here is the institution which students love and parents trust! At our school,success is not a matter of luck;it's a matter of teamwork!
10/09/2024
⭐️እንኳን ለ2017 ዓ.ም⭐️
አዲስ ዓመት በሠላም አደረስዎ!⭐️
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።
23/06/2024
11/09/2023
Dear Glory School Students'/Parents/Guardians:
Happy new academic year 2023/24. I explained that this new school year is a year that creates a better mindset for our children, a year in which they can think and do new things;when children come to school they will meet new friends, learn to socialize, play and pick essential life skills. As long as there is cooperation of parents and the door of the school is open to parents, we are sure to get results. It is with great joy that we announce our full preparation in terms of implementing modern education in this New Year.
Finally, I assure you that this New Year will be a year of working together. More on this; It is my constant prayer to see our children be a blessing to Ethiopia. In Glory School Successes is not about luck but it is the result of teamwork.
Best regards
Shigiger Daniel
Managing Director
ውድ የግሎሪ ት/ቤት ተማሪዎች /ወላጆች/ አሳዳጊዎች
እንኳን በ 2016 ዓ.ም አዲስ የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ::
ይህ አዲሰ የትምህርት ዘመን ለልጆቻችን የተሻለ የአስተሰሰብ ለውጥን የሚፈጥር፣ ስራ ወዳድ፣ ተመራማሪ ብሎም አዳዲስ ነገሮችን ማሰበና መስራት የሚችሉበት ፣ አዳዲስ ጓደኞችን የሚያገኙበት ፣ መግባባትን የሚማሩበት፣ መጫወት እና አስፈላጊ የህይወት ክህሎቶችን የሚያዳብሩበት አመት እንዲሆን በብዙ መልኩ የተዘጋጀን መሆኑን አየገለፅኩኝ ፤ ከእግዚአብሔር እርዳታ ጋር ውጤታማ አመት እንደሚሆን ስናገር ያለምንም ጥርጥር ነው :: የወላጆች አብሮነት እስካለ እና የትምህርት ቤቱ በር ለወላጆች ክፍት ከሆነ ውጤት ማግኘታችን አሙን ነው::
በዚህ አዲስ አመት ዘመናዊ ትምህርትን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ሙሉ ዝግጅት መጨ ረሳችንን ስናበሰር በታላቅ ደስታ ነው::
በመጨረሻም ይህ አዲስ አመት ተባብረን የምንስራበት አመት እንዲሆን ከወዲሁ አደራ እላለሁ። ልጆቻችን የኢትዮጵያ በረከት ሆነው ማየት የዘወትር ፀሎቴ ነው።
በግሎሪ ስኬት እድል ሳይሆን የጋራ ስራ ውጤት ነው።
ከሰላምታ ጋር
ሽግግር ዳንኤል
ማኔጂንግ ዳይሬክተር
14/07/2023
ቃል ሜሞሪ" የማስታወስ ጥበብና ሁለንተናዊ የአዕምሮ ዕድገት ሥልጠና ማዕከል
KAL Memory Art and Mental Development Training Centre
ለውድ ወላጆች
ቃል ሜሞሪ የማስታወስ ጥበብና ሁለንተናዊ የአዕምሮ ዕድገት ማሰልጠኛ ተቋም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ ሙሉ ዕውቅና ያለው ሲሆን፤ ድርጅቱ በዋናነት የማስታወስ ጥበብ፣ የአጠናን ቴክኒኮችን፣ ቁጥሮችን በአዕምሮ ብቻ ከካልኩሌተር ቀድሞ የማስላትና ሐሳብንና ትኩረትን አንድ ቦታ ላይ የማድረግ ጥበብ ትምህርትን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባላቸው መምህራን ለተማሪዎች ክረምትን በግሎሪ ት/ቤት ያሰለጥናል፡፡
ልጆችዎ ይህንን ለከረምት የሚሰጥ ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላ ያዩትን፣ የሰሙትንና ያነበቡትን በቀላሉ ማስታወስ፣ ቁጥሮችን ከካልኩሌተር ቀድሞ በአዕምሮ ማስላት፣ ከፍተኛ የንባብ ፍቅር ባለቤት መሆን፣ ትኩረታቸውን ረዘም ላለ ሰከንድ አንድ ነገር ላይ የማድረግ ብቃት ይኖራቸዋል፡፡ በመጨረሻም ይህንን ስልጠና ከወሰዱ ተማሪዎች ጋር በመወዳደር ለከፍተኛ ሽልማት ዕጩ ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም ልጅዎ ይህንን ስልጠናና ውድድር እንዲሳተፍ ፈቃደኛ ከሆኑ ለስልጠናና ቁሳቁሶች ወጪ የሚሆን 1300 ብር በግሎሪ ት/ቤት የቃል ሜሞሪ ስልጠና አስተባባሪ ከፍለው ደረጃ አንድ የሥልጠና ሞጁል (Level 1 Module) እና ሒሳብን የማስሊያ መሳሪያ (አባከስ) እንዲወስዱ እናሳስባለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ቃል ሜሞሪ የማስታወስ ጥበብ ት/ቤት ስልክ፡ 0929 92 97 92
09/07/2023
Congratulations to all 2022/23 kindergarten graduates!