17/04/2026
ሰበር : - 27.1 ሚሊዮን እይታዎች በአንድ ቀን!
ቴዲ አፍሮ በዓለም የምርጥ 20ዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙን በወርቅ ቀለሙ ጻፈ:
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከ9 ዓመታት ቆይታ በኋላ፣ 18 ሙዚቃዎችን ያካተተ “ኢትዮሪካ” የተሰኘ ስድስተኛ አልበሙን ትላንት በዚሁ ሰዓት በይፋ ለቋል።
አልበሙ ከተለቀቀበት ቅጽበት ጀምሮ ከፌስቡክ እስከ ቲክቶክ፣ ከዩቲዩብ እስከ X (ትዊተር) ዋነኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል።
በሀገራችን የኪነ-ጥበብ ስኬቶችን በዝርዝር መዝግቦ ይፋ የሚያደርግ ተቋም ባይኖርም፣ በግል ጥረት ጎግልን (Google) በመጠቀም በተደረገ ፍተሻ ቴዲ አፍሮ የሚከተሉትን ታሪካዊ ስኬቶች አስመዝግቧል፡
1. የአፍሪካ አዲስ ሪከርድ
ቴዲ አፍሮ በአንድ የአፍሪካዊ ድምፃዊ ታሪክ ውስጥ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ቀደም ሲል የነበረውን የ22 ሚሊዮን እይታ ሪከርድ በመስበር፣ በድምሩ 27.1 ሚሊዮን እይታዎችን በማግኘት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆኗል።
2. የሰብስክራይበር (Subscriber) እድገት
የድምፃዊው የዩቲዩብ ቻናል በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ አዳዲስ ተከታዮችን በማፍራት 1.84 ሚሊዮን ደርሷል። ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛ እድገት በአፍሪካ ታይቶ የማይታወቅ ነው።
3. "ዳስ ጣል" እና ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ
በአልበሙ ውስጥ የሚገኘው "ዳስ ጣል" የተሰኘው ሙዚቃ ብቻውን ከ4 ሚሊዮን በላይ እይታዎችን በማግኘት፣ በዩቲዩብ ታሪክ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ከሳቡ ጥቂት ቪዲዮዎች ተርታ ተሰልፏል።
4. ከምርጥ 20ዎቹ ተርታ
የዓለምን የ24 ሰዓት የሪከርድ ዝርዝር ስንመለከት (ለምሳሌ የቢቲኤስ "Butter" 113 ሚሊዮን)፣ ቴዲ አፍሮ በ27.1 ሚሊዮን እይታው በዓለም ደረጃ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ እይታ ካገኙ ምርጥ 20 አርቲስቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል።
ይህም አልበሙን ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ውጭ ተሰርተው እንዲህ ያለ ከፍተኛ እይታ ካገኙ ጥቂት የሙዚቃ ስራዎች ቀዳሚ ያደርገዋል።
* ዳስ ጣል፦ 4.2 ሚሊዮን በላይ
• ጀምበር፦ 2.8 ሚሊዮን በላይ
• መሬማ፦ 2 ሚሊዮን በላይ
• ጽዮን ሙሽራዬ፦ 1.8 ሚሊዮን በላይ
• ስምምነን፦ 1.6 ሚሊዮን በላይ
• ኢትዮሪካ፦ 1.4 ሚሊዮን
• መርከብ፦ 1.4 ሚሊዮን በላይ
• ስማ ራሴ፦ 1.4 ሚሊዮን በላይ
• ሺ ቢባል፦ 1.3 ሚሊዮን በላይ
• ብልጭታ፦ 1.3 ሚሊዮን በላይ
• የአዞ ዕንባ፦ 1.3 ሚሊዮን በላይ
• ዝ ፀዳል፦ 1.3 ሚሊዮን በላይ
• ሳምነው፦ 1.2 ሚሊዮን በላይ
• ታንታጎ፦ 1.1 ሚሊዮን በላይ
• በመስኮቱ፦ 1.1 ሚሊዮን በላይ
• ታየኝ፦ 1 ሚሊዮን በላይ
• ተወዳጅ፦ 932 ሺህ በላይ
• የማዕረግ ጥግ፦ 861 ሺህ በላይ
ማጠቃለያ
ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲህ በአንድ ድምፅና በአድናቆት የቆሙበት አጋጣሚ አይቼ አላውቅም። የፌስቡክ ግድግዳዎች በሙሉ በኢትዮጵያዊነት ፍቅርና በቴዲ አድናቆት ተሞልተዋል።
ማሳሰቢያ፦ ይህ መረጃ ጎግልን እና የዩቲዩብ መረጃዎችን በመጠቀም በግል ጥረት የተዘጋጀ ነው።
Via ታዴ የማመይ ልጅ
ጉርሻ page
🌴🌴🌴