የስኪልማርት አካዳሚ የ2017 ዓም የኬጂ-3 ተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት
Skillmart International College
Skillmart International College is fully Accredited higher education institution located in Ethiopia
05/06/2025
እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉን የሠላም፣ የፍቅርና የደስታ ያድርግልን።
ኢድ ሙባረክ!
ስኪልማርት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
19/04/2025
ለመላው የስኪልማርት ቤተሰቦች፤
እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉን የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ያድርግልን!
https://www.facebook.com/SkillmartInternationalAcademy
https://www.facebook.com/SkillmartInternatinalCollege
https://t.me/skillmartInternationalcollege
https://t.me/SkillmartAcademy
18/01/2025
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!
06/01/2025
መልካም የገና በዓል!
Merry Christmas!
22/12/2024
ስኪልማርት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ባህርዳር ካምፓስ ተማሪዎቹን አስመረቀ!
ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም || 21st December 2024
***
ስኪልማርት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በባህርዳር ካምፓሱ በድህረ-ምረቃ (ማስተርስ) መርሐግብር በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ አናላይሲስና ኢቫልዌሽን (Project Management, Analysis and Evaluation_ PMAE) እንዲሁም በቢዝነስ አስተዳደር (MBA) የትምህርት መስኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን ከ250 በላይ ተማሪዎቹን ኮሌጁ ከተመሠረተ ጊዜ አንስቶ ለ4ኛ ጊዜ እንዲሁም በካምፓሱ ታሪክ ለ2ኛ ጊዜ በባህር ዳር ከተማ፣ በአማራ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓም አስመርቋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የስኪልማርት ትምህርት ልማት አክስዮን ማህበር የቦርድ አመራር፣ የኮሌጁ መምህራንና ሰራተኞች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በመርሐ-ግብሩ ላይ በኮሌጁ የካምፓሱ ዲን የሆኑት አቶ ምኒልክ ግዛቸው፣ የአክስዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ ምንዳ እና የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ከማል ስዒድ ለተመራቂዎች እና ለተመራቂ ቤተሰቦች ባስተላለፉት መልዕክት የዕለቱ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሮ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
የፕሮግራሙ የክብር እንግዶች እና የተቋሙ አመራሮች በዕለቱ የምረቃ ስነስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ምሩቃኑ በየዘርፋቸው ያለውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ክፍተት ከማጥበብ ባሻገር ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ እና በእውቀት በመምራት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ አደራቸውን ገልጸዋል።
Telegram: https://t.me/skillmartInternationalcollege
https://t.me/skillmartbahirdar
Facebook: https://www.facebook.com/
Class of 2024
18/11/2024
ስኪልማርት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በአዲስአበባ መገናኛ አደባባይ ካምፓሱ በድህረ-ምረቃ (ማስተርስ) መርሐግብር በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ አናላይሲስና ኢቫልዌሽን (Project Management, Analysis and Evaluation_ PMAE) እንዲሁም በአካውንቲንግና ፋይናንስ (Accounting and Finance) የትምህርት መስኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን ተማሪዎቹን ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው ማግኖሊያ ሆቴል አዳራሽ ቅዳሜ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓም አስመርቋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የስኪልማርት ትምህርት ልማት አክስዮን ማህበር የቦርድ አመራሮችና አባላት፣ የኮሌጁ መምህራንና ሰራተኞች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ የአክስዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚና የኮሌጁ ዲን የሆኑት አቶ በቀለ ምንዳ እና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ተሰማ ገዳ ለተመራቂዎች እና ለተመራቂ ቤተሰቦች ባስተላለፉት መልዕክት የዕለቱ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል።
በፕሮጀክት አመራርና በተለያየ ደረጃ በባለሙያነት የበርካታ ዓመታት ልምድ ያካበቱት እና በአሁን ሰዓትም የፒ ኤም አይ ኢትዮጵያ ቻፕተር (PMI Ethiopia Chapter) ፕሬዘዳንት እንዲሁም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የሆኑት የዕለቱ የምረቃ የክብር እንግዳ አቶ ተሰማ ባስተላለፉት መልእክት ምሩቃኑ በሰለጠኑበት ዘርፍ ያለውን የሰው ሀይል ክፍተት ከማጥበብ ባሻገር ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ እና በመምራት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
Magnolia https://www.facebook.com/magaddis?mibextid=ZbWKwL
Telegram: https://t.me/skillmartInternationalcollege
Facebook: https://www.facebook.com/
24/09/2024
Bahir Dar Campus
14/09/2024
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የስኪልማርት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ቤተሰቦች፤
እንኳን ለ1499ኛው የታላቁ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ በዓሉን የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ያድርግልን።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |
| Saturday | 09:00 - 12:00 |