29/07/2025
Lemma Zemelak
Personal blog
29/07/2025
09/05/2025
እንኳን አደረሳችሁ
29/04/2025
11/04/2025
ቀይ ሽንኩርት ለቤት ውስጥ ሕክምና ወደር ያልተገኘለት መድኃኒት☞14 ነጥቦች
1. ከጉንፋን ለመላቀቅ፡- ግማሽ ፍንካች በቀጭኑ የተከተፈ ሽንኩርት ላይ በመሃል በመሀሉ አስነተኛ ስኳር ነስንሰው በመሸፈን ለሰዓት ያህል ሸፍኖ በማስቀመጥ በቀን ሁለቴ ቢመገቡ ጉንፋንን በቶሎ ይሰናበታሉ፡፡
2. የፀጉር መነቀልን ለመከላከል፡- የተወሰነ ሽንኩርት ውሃ ውስጥ ጨምረው ያፍሉትና ከሻምፖ በፊት ደጋግመው ይታጠቡበት ውጤቱን በፍጥነት ያዩታል፡፡
3. የሕፃን ሆድ ቁርጥ ለማስታገስ፡- ህፃናት በሆድ ቁርጠት ሲቸገሩ አንድ ፍንካች ሽንኩር በውሃ አፍልታችሁ በየሰዓቱ በትሰጧቸው ከስቃያቸው ፋታ ያገኛሉ፡፡
4. የነፍሳት ንክሻ ሕመምንና እብጠትን ለመቀነስ፡- በቀጭኑ የተከተፈ ሽንኩርት ሕመም በሚሰማውና በአበጠው ቦታ ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ሸፍኖ መያዝ፡፡
5. ለጆሮ ኢንፌክሽን፡- በስሱ የተሸነሸነ ሽንኩርት በአነስተኛ ጨርቅ ተቋጥሮ ሕመሙ እስኪጠፋ ድረስ በታመመው ጆሮ ላይ መወተፍ ትልቅ መፍትሔ ይሆናል፡፡
6. ደም ለማቆም፡- ድንገት ጣቶን የሆነ ነገር ቢቆርጦት ወይም ቢወጋዎት የሽንኩርት ልጣጭ ቢጠመጥሙበት ወይም በስሱ የተከተፈ ሽንኩርት ቢይዙበት በፍጥነት ደሞ ከመፍሰስ እንዲቆም ያደርጋል፡፡
7. የአካባቢዎን አየር ያጸዳል፡- ተልጦ የተከተፈ ሽንኩርት በቤት ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ቢያስቀምጡ ባክቴሪያና ቫይረሶችን በመምጠጥ ቤቶን ያፀዳል፡፡
8. በፀሐይ ወይም በእሳት የተቃጠለን ቆዳን ያክማል፡-በአነስተኛ የተላጠ ሽንኩርት በፀሐይ ወይም በእሳት የተቃጠለን ቆዳ ቢያሹት ከኢንፌክሽን ይጠብቆታል፡፡ ይህም ቆዳዎ እንዲያገግም ከማድረጉ ባሻገር እንዳይቀላ ያደርገዋል፡፡
9. ትኩሳትን ያስወግዳል፡፡ የተላጠና በቀጭኑ የተከተፈ ሽንኩርት ከኮኮናት ዘይት ጋር አድርገው የውስጠኛው እግሮን ካሹት በኃላ ሽንኩርቱን እዚያው በመተው በላስቲክ ጠቅልለው ካልሲ አድርገው ቢተኙ ትኩሳቱ ለሊቱን ጠፍቶ ያድራል፡፡
10. ከአፍንጫ የሚወጣ ደምን ለማቆም፡- የሚደማ አፍንጫን ለማቆም የተከተፈ ሽንኩርት በሚደማው አፍንጫ ውስጥ ለተወሰነ ደቂቃ ቢያስገቡ ደሙ ይቆማል፡፡
11. የእንቅልፍ ማጣት ችግርን ያቃልላል፡- ከመተኛትዎ በፊት በትላልቁ የተከተፈ ሽንኩርት በጨርቅ አስረው ወይም እንዲሁ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሽታውን ቢምጉት ከዚያን እንቅልፎን በቀላሉ ያመጣዋል፡፡
12. የወባ ትንኝን ከቤቶ ያባርራል፡- የተላጠውን ሽንኩርት በሚተኙበት ቦታ ላይ በሳህን አድርገው ያኑሩት ወይም የተከተፈ ሽንኩረቱን የሚጋለጠውን የሰውነቶን ክፍል ይሹበት የወባ ትንኟ ከቤቶ ወጥታ ትሄዳለች፡፡
13. የጉሮሮ ሕመምን ያስውግዳል፡፡ የተፈጨ ሽንኩርት ውሃውን አነስተኛ ማር ጨምረውበት በተደጋጋሚ ቢወስዱ የጉሮሮ ቁስልን ይፈውሳል፡፡
14. በቆዳዎ ላይ የሚገኝ ጥቁር ነጥቦችን ያስወግዳል፡- ከዕድሜ መግፋትና በሌሎች ምክንያት በቆዳዎ ላይ የሚወጡ ጥቁር ነጥቦችን በቀን ሁለት ጊዜ በተከተፈ ሽንኩርት ያለማሳለስ ቢያሹት ውጤቱን በፍጥነት ያገኙታል፡:
©Dr.Alle
እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ይተባበሩ!
11/04/2025
ጊዜ.......
19/01/2025
ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.