አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ

አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ

Share

ኢትዮጵያ

27/01/2025
17/06/2024

አስተማማኝ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ ለህዝባችን ተጠቃሚነት ተናጠላዊ ፍላጎቶቻችንን መስዋዕት እናድርግ !

በህብረት በቆምንበት ጊዜ ድል አስመዝግበን ታሪክ ሰርተናል። ከተናጠል ፍላጎቶቻችን ይልቅ ለብሔራዊ ክብራችን ቅድሚያ በሰጠንበት የታሪክ ምዕራፍ ሁሉ የአሸናፊነት ደማቅ ታሪክ ተጎናፅፈናል።

በዓለም አቀም ደረጃ የሚጠቀሱ ታላላቅ ስልጣኔዎች የነበሩን ፣ የዴሞክራሲ ስርዓት ከመስፋቱ በፊት አገር በቀል ስርዓትን የገነባን ፣ ተቻችሎ እና ተከባብሮ በመኖር አብነት የሆነን ፣ በየጊዜው የገጠሙንን ተግዳሮቶች በጋራ የመከትን እያልን ስለ ገናና ታሪካችን ብዙ መጠቃቀስ ብንችልም ታላቅ ነበርን ማለት ታላቅ አያደርግም ፤ ታላቅ ሆኖ መገኘት እንጂ።

ኢትዮጵያ በየዘመኑ የታሪክ ስብራቶቿን ልትጠግንባቸው የሚችሉትን መልካም አጋጣሚዎች አባክናለች። እንደ አለመታደል ሆኖ አንድነቷን እንደ ብረት ሊያጠናክርላት የሚገባው በደምና በአጥንት መስዋዕትነት የተገኘው የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ኩራት የሆነው የአድዋ ድል አከባበር ጭምር የመሰባሰቢያ ሳይሆን የመለያያና የመገፋፊያ ምንጭ ሆኖ መቆየቱ አግራሞትን ያጭራል።

ምስጋና ለባለ ራዕይ መሪዎቻችን ይሁንና አሁን ላይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር የጥል ግድግዳ የሚፈጥርበት ምዕራፍ ተዘግቶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአብሮነትና በፍቅር የሚያከብርበት ብቻም ሳይሆን ድሉ ዓመቱን ሙሉ የሚዘከርበት ፣ ጥበብንና ቅርስን አጣምሮ የያዘው ፣ ከእኛ ትውልድ የታሪክ አሻራዎች ውስጥ ጎልቶ ሲጠቀስ የሚኖረው የአድዋ ድል መታሰቢያ ለከተማችንም መለያ ዓርማ ሆኗል::

በመሰባሰባችን የተገኘው ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነውን የአድዋ ድልን በአድዋ ድል መታሰቢያ ተሰባስበን በድምቀት ማክበር ብቻም ሳይሆን በችግር ጊዜ ጭምር የህብረታችን ሚስጢር ተናጠላዊ ፍላጎትን ለአገራዊ ድል በማስገዛት መሆኑ በጥናትና ምርምር እየዳበረ ለትውልድ መማሪያ ዕውቀት እንደሚገበይበትም ይጠበቃል።

የለውጡ መንግስት የህዝባችንን ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት ባረጋገጠ መልኩ ነፃ ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ አገር የመምራት ሀላፊነት ስለተሰጠው የነበሩትን ውስብሰብ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እያቃለለ እንደ አገር የነበሩብንን ስብራቶች ለመጠገን ጥልቅ ሪፎርሞችን እያከናወነ ይገኛል።

ከሪፎርም ስራዎቻችን መካከልም ነፃ እና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተቋማትን ለመፍጠር የተደረገው አበረታች ጥረት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው::

ፓርቲያችን የዴሞክራሲ ስርዓትን በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት እና የፖለቲካ ባህላችን ወደ ትብብር እና ፉክክር ለማምጣት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የወሰዳቸው እርምጃዎች ምንጫቸው የአገራችንን ውስብስብ ችግሮች በጥልቀት ከመረዳት እና አሻግሮ ከማየት ብቃት ነው።

ነፃ እና ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ ተቋቁሞ በአገራችን ታሪክ ሲወሳ የሚኖር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መደረጉ ስልጣን በህዝብ ድምፅ እንጅ በሀይል የሚገኝበት የታሪክ ምዕራፍ መዘጋቱን የሚያመላክት የዛሬው ብቻም ሳይሆን የነገውም ትውልድ ብስራት ነው።

ሀገረ መንግስት ግንባታው የዕድሜውን ያህል እንዳይራመድ ተግዳሮት የነበሩ መግባባት ላይ ያልደረስንባቸውን አገራዊ ጉዳዮች በምክክር እና በውይይት ለመፍታትም ከማንኛውም አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።

ሳንግባባቸው ያደርን ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች ሳያንሱን ለሰላም እንምከር ፣ ለልማት እንተባበር ፣ ዴሞክራሲን እናዳብር ስንል ተቃራኒውን የሚያስቡ እና የሚተገብሩ ፅንፈኛ አካላት የሀሳብ ድርቀታቸውን ለመሸፋፈን ጥረት ቢያደርጉም ህዝባችን

16/06/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል አድሐ( አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

ዒድ አል አድሃ፣አረፋ ሙስሊሞች በታላቅ ክብር እና ፍቅር የሚያከብሩት፣ መሥዋዕትነትን የሚዘክር በዓል ነው፡፡

በዓሉ ከአምስቱ የእስልምና መሠረቶች መካከል አንዱ የሆነውና ማንኛውም ሙስሊም የገንዘብና የጉልበት ዐቅሙ እስከፈቀደ ድረስ በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንዴ ወደ መካ በመጓዝ እንዲያከናውነው የሚጠበቅበት የሐጅ ሥርዓት የሚካሄድበትና የሚጠቃለልበት ታላቅ ምዕራፍ ነው፡፡

ኢድ የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር በዓል ነው፡፡
የኢድ አል አዳሃ የአረፋ በዓል የደስታና የመረዳዳት በዓል በመሆኑ የእምነቱ ተከታይ ወንድሞችና እህቶች በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካማ ወገኖቹን በመጠየቅ የተራቡትን በማብላትና የታረዙትን ማልበስ የተለመደ ተግባር በመሆኑ ልንተገብረው ይገባል።

ፈጣሪ የአገራችንን ሠላም እንዲጠብቅልን ሃይማኖታዊ እሴቶቻችንን ማክበርና በየእምነታችን ዱአ ወይም ፀሎት ማድረግ ይጠበቅብናል።

በዓሉ የሠላም፣ የጤና የመተሳሰብና የአንድነት በዓል እንዲሆልን እመኛለሁ!!!

አቶ አብደላ ሀሰን
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ ኀላፊ

15/06/2024

እንኳን ለ2016 የዒድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የኢድ አል አድሃ በዓል የፈተናና የመሥዋዕትነት በዓል ነው፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም በአላህ ትእዛዝ ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት ያዘጋጁበት፤ ጽናታቸው ተፈትኖ ያሸነፉበት በዓል ነው፡፡ ለዚህ ጽናታቸውም ከአላህ ዘንድ ምትክ በግ ያገኙበት በዓል ነው፡፡

ከዚህ በዓል የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ማንኛውም ፈተና በጽናት ካለፉት ዋጋው ከፈተናው በላይ መሆኑን እንማርበታለን፡፡ ልጅን ያህል ነገር እንዲሠዉ መጠየቅ ከባድ ፈተና ነው፡፡ ልጅን ለመሥዋዕትነት ማዘጋጀት ደግሞ ከባድ ጽናት ነው፡፡ ከባድ ፈተና ከባድ ቆራጥነት ይፈልጋል፡፡ ከባድ ቆራጥነት ከባድ ውሳኔን ይጠይቃል፤ ከባድ ውሳኔም ታላቅ ዋጋን ያስገኛል፡፡

ኢትዮጵያን ታላቅና የበለጸገች ሀገር ለማድረግ ስንነሣ ፈተናው ከባድ እንደሚሆን እናምን ነበር፡፡ ሳይፈቱ የተከማቹ ሀገራዊ ችግሮች አሉ፡፡ በዘመናችን የተፈጠሩ አሁናዊ ችግሮችም አሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱን በአንድ ጊዜ መጋፈጥ ይጠይቀን ነበር፡፡ ተራራውን መጋፈጥ ሳይሆን ተራራውን ማንሣት ይጠይቀን ነበር፡፡ ይሄንን ፈተና ለመጋፈጥ ከባባድ ውሳኔዎችን መወሰን ይገባን ነበር፡፡ እንደ ልጅ የምንወዳቸውን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ቡድኖች፣ ወዳጆችና አካሄዶች ለመሠዋት መወሰን ነበረብን፡፡ መወሰን ብቻ ሳይሆን ማድረግም ነበረብን፡፡

ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸው ኢስማኤልን ሳይሆን በምትኩ ከአላህ የተሰጣቸውን በግ ሠዉተዋል፡፡ የእኛ ፈተና ከዚህም የባሰ ነበር፡፡ ሀገራችን ባከማቸቻቸው ዕዳዎችና ስብራቶች የተነሣ፣ ያለን አማራጭ የራሳችንን ነገር መሠዋት ብቻ ነበር፡፡ ሀገራችንን ለማዳን፣ የሕዝባችንን ዘላቂ ጥቅሞች ለማስከበር እና ከዛሬው የተሻለ ነገን ለመፍጠር ስንል፣ ብዙ ነገሮችን ሠዉተናል፡፡

ችግሮቻችን ቀስ ብለን እንድንሄድ አይፈቅዱልንም፡፡ በጥንቃቄ እንድንሮጥ እንጂ፡፡ የልማት ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ እንደ ሕዝብ ሁላችንም የምንወዳቸውን ነገሮች ሠዉተናል፡፡ ከምንወደው አካባቢ ወደ ሌላ ሄደናል፡፡ ትዝታዎቻችንን ሠዉተናል፡፡ የባንዳውን ጩኸት ችለናል፤ ሀገርን ለመለወጥ ስንል ቤቶቻችንና ሕንጻዎቻችን እንዲፈርሱ ፈቅደናል፡፡ የመብራትና የውኃ መጥፋትን ታገሠናል፤ የመንገድ መዘጋትንና የአካባቢ መፈራረስን ተቀብለናል፡፡ ያለ መሥዋዕትነት የሚያድግ ሕዝብ፣ ያለ መሥዋዕትነት የሚበለጽግ ሀገር የለም፡፡ የኮሪደር ልማቱን በዚህ መልኩ በመሥዋዕትነት ነው የሠራነው፡፡ ፍሬው ግን እጅግ ጣፋጭ መሆኑን አይተናል፡፡

ሰላማችንን ለማስፈን በዚሁ መንገድ ነው መቀጠል ያለብን፡፡ ነፍጥን መጣል፤ ከጫካ መውጣትና የራስን ዋሻ ትቶ ወደ መስኩ መውጣትን ይፈልጋል፡፡ የራስን ኢጎ መሠዋትን ይጠይቃል፡፡ ምቾትንና ፍላጎትን መተዉን ይፈልጋል፡፡ ከመቀበል በላይ መስጠትን ይሻል፡፡ እንደ ኢብራሂም በጣም የምንሳሳለትን ነገር ለመሠዋት መቁረጥ ይፈልጋል፡፡ ሁላችንም ለመሥዋዕትነት ከተዘጋጀን የማይሳካ የሰላም መንገድ የለም፡፡ እንደ ልጅ ያሳደግናቸው ብዙ ልማዶች፣ ጠባዮች፣ አመለካከቶች፣ ርእዮተ ዓለሞችና አካሄዶች አሉን፡፡ እነርሱን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ስንል ለመሠዋት ዝግጁ ከሆንን፣ ውጤቱ ከሰላም በላይ ነው፡፡

ምክክር የሚሳካው የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት በማዋጣት ብቻ አይደለም፡፡ የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት ስላለን ብቻ የሠመረ ውጤት አናገኝም፡፡ ሌላ ወሳኝ ነገር ይፈልጋል፡፡ እርሱም መሥዋዕትነት ነው፡፡ የራስን ፍላጎት ለመሠዋት መቻል አለብን፡፡ ለትልቅ ግብ ሲባል ይቅርብኝ ማለት አለብን፡፡ ከእኔ የተሻለ ሐሳብና ልምድ፣ ዕውቀትና ጥበብ ሊኖር ይችላል ብለን ማመንና መቀበል አለብን፡፡ ለተሻለው ሐሳብ መገዛት አለብን፡፡

Photos from አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 15/06/2024

የውስጠ ፓርቲ ስራዎችን በማጠናከር ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ጠንካራ ፓርቲን እንገነባለን!!

በፌደራል ደረጃ የተዋቀረው በብልጽግና ፓርቲ የኢንሰፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን "በጠንካራ ኢንስፔክሽን ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት" በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በየካ፣ በአቃቂ ቃሊቲና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና በስራቸው ባሉ ስድስት ወረዳዎች ውስጥ ሲያካሄድ የነበረውን ኢስፔክሽንና ሱፐርቪዥን በማጠናቀቅ ግብረ መልስ ተሰጥቷል።

በመድረኩም በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ እና ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣ በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይመር ከበደ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች በተገኙበት ግብረ-መልስ ተሰጥቷል።

ግኝቱን ያቀረቡት የፌዴራል ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን የድጋፍ እና ክትትል ቡድን መሪ ዶ/ር ኤባ ሚጀና በቆይታቸው በፓርቲ መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ የፓርቲ ተግባራት መሰራታቸውን በማረጋገጥ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ ማስቀጠልና በጉድለት የታዩ ተግባራት ደግሞ በቀጣይ እንዲታረሙ አቅጣጫዎችን አስቀመጠዋል።

በጥቅሉ ፓርቲያችን በጀመረው የሀገራዊ የብልጽግና ጉዙ ቀጣይ ጠንካራና የተቀናጀ አሰራርን በመከተል ሀገረ-መንግስት ግንባታን ማሳለጥ ወሳኝ መሆኑንም ተገልጿል።



Photos from አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 15/06/2024

"ያለ ህዝብ ብቁ ተሳትፎ የሚከናወን ስራ ሙሉ ሊሆን አይችልም!

ሰላማችንን ዘላቂ እና ህዝባዊ መሰረት ያለው ለማድረግ ዛሬ አሰልጥነን ያስመረቅናቸው 11 ሺሕ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላትን ጨምሮ 341 ሺሕ የሠላም ሠራዊት አባላትን የከተማችን የሰላም ዘብ አድርገን አሰማርተናል።

ከ2013 ጀምሮ ሕዝባችንን በተደራጀ መልኩ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ማቀናጀት እና የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት ማድረግ መቻላችን እስካሁን ካስገኘልን ውጤታማ እና ስኬታማ ስራዎች በተጨማሪ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ሰላማዊ ማድረግ ችለናል።

ዛሬ የተመረቃችሁ የሰላም ሰራዊት አባላት ሕዝባችን የሰላሙ እና የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ባለቤትና ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆኑን በመረዳት በየአካባቢያችሁ የሰላምና የመሰረተ ልማቱ ዘብ በመሆን ህዝባችሁን በፍፁም ትህትና እና ፍቅር እንድታገለግሉ አደራ ማለት እወዳለሁ።"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 14/06/2024

የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ከሲዳማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በጋራ በመተባበር "የብሔራዊነት ትርክት ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የስልጠና መድረክ የልምድ ልውውጥ ተሞክሮ ተካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ መሰረት በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዘርፍ በኩል የተሰሩ ስራዎች በተሞክሮነት ቀርበዋል።

የመልእክት ስርጭት ቀረፃ እና ተደራሸነት፣ ስልተቀመርን ባማከለ መልኩ የመረጀ የበላይነትን መቀናጀት፣ለማህበራዊ ሚዲያ የሚያገለግሉ የፕሮዳክሽን ስራዎች አቀራረብ ገለፃ የተደረገባቸው ነጥቦች ናቸው።

ገለፃውን ያቀረቡት የዘርፉ ሀላፊ አቶ ስዩም ከበደ ፈጠራ እና ፍጥነት፣የመረጃ ቅንጅት፣በተዋረድ የተደራጀ የግንኙነት ስርአት ለህዝብ ግንኙነት ስራ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የፓርቲያችንን ራዕይ እና ፖሊሲ ለማሳካት፣የብሔራዊነት ትርክት ግቡን እንዲመታ ለማስቻል፣በዘመናዊው የሚዲያ የትግል ሜዳ ድል አድርጎ ለመቆም ስልታዊነትን በተላበሰ አካሄድ መጓዝ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

እንደ ፓርቲ የመረጃ ተደራሽነትን ማስፋት፣ተደራጅቶ ተደማሪ አቅም መፍጠር፣የተፅእኖ ፈጣሪነትን አቅም ማላቅ፣ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት መሸጋገር ለህዝብ ግንኙነት ስራችን የህልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።

እንደ ብልፅግና ፓርቲ ለህዝቡ የገባናቸውን ቃሎች በላቀ ውጤታማነት፣ ፈጠራን እና ፍጥነትን ጨምሮ ምላሽ ለመስጠት ጊዜውን የሚመጥን የህዝብ ግንኙነት ስራን መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው በዚህ ረገድ ተግባሩን በልዩ ዕቅድ ፣ በተቋም የተመራበት አግባብ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ የተደረሰውን ውጤት እና ስራዎችን በሃሳብ የበላይነት ለህዝቡ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል።

የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች እና አመራሮች በዝርዝር የቀረቡ የልምድ እና የተሞክሮ ውጤቶችን ተግባራዊ ማድረግና የብሔራዊነት ትርክት ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ሊደግፉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

Photos from አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 14/06/2024

የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
**********

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር የ2ኛ ዙር የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ ብድር ለማግኘት የተፈረመውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በብድር የተገኘው 207,200,000 የአሜሪካ ዶላር ሲሆን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የሳኒቴሽንና ሃይጂን አገልግሎት ተግባራትን ለማሻሻልና የዘርፉን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከር የሚውል ነው፡፡ ብድሩ ወለድ የማይታሰብበት፣ 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበት ሆኖ 6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ብድሩ ከአሀራችን የብድር አስተዳደር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የንብረት ታክስ በከተሞች ነዋሪ በሆነው ሕዝብ መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማስፈን፤ የመንግስት አገልግሎቶችን በተሻለ ጥራትና በዘመናዊ ዘዴ ማቅረብ ለማስቻል እና የከተማ መሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን በቀጣይነት ለመተግበር የሚወጣውን የኢንቨስትመንት ወጪ በንብረት ዋጋ ማደግ ምክንያት በሚጣል ታክስ አማካኝነት ለመሰብሰብ የሚያስችል ነው፡፡ አዋጁ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ተፈጻሚነት የሚኖረው ሲሆን፤ ክልሎችም ይህንን አዋጅ መሰረት በማድረግ ከተጨባጭ ሁኔታቸው ጋር በተጣጣመ አኳኋን የየራሳቸውን የንብረት ታክስ ህግ እንዲያወጡ ያስችላል። በዚሁ መሰረት ይህንን ለማስፈጸም የሚረዳ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

3. በ3ኛ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሪፎርም እና የካፒታል ማሳደጊያ ዕቅድ ላይ ነው፡፡ የባንኩን የሀብት ጥራት ለማሻሻል እና በአስተማማኝ መልኩ የካፒታል መጠኑን በማሳደግ ለኢኮኖሚው ዕድገት እና ልማት የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርግ ለማስቻል የሚረዱ የውሳኔ ሃሳቦች ለሚኒስትሮች ም/ቤት ቀርበዋል፡፡ እነዚህም የባንኩን አስተዳደራዊ ውጤታማነት ማጎልበት፤ የሂሳብ መግለጫዎቹን ጠንካራና ተቀባይነት ባለው መልኩ እንዲዋቀር ማድረግ እና የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ የሚረዳ የመንግሥት የፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻል የሚሉ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በማሻሻያ እቅዱ ላይ ተወያቶ ወደቀጣይ ተግባር እንዲገባ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ባለፉት 16 ዓመታት በስራ ላይ የቆየው አዋጅ ሁሉንም የልማት ተዋናዮች ያሳተፈ የብልጽግና ዕቅድ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ፣ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮና መርሆች አንጻር፣ ከአቻ ማዕከላዊ ባንኮች መልካም ተሞክሮ፣ከገንዘብ ፖሊሲ ውጤታማነት እንዲሁም በፋይናንስ ራስን ከመቻል አንጻር ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ፤ ባለፉት አመታት በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የጂኦ-ፖለቲካ ለውጦች በመኖራቸው፤ የባንኩን ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የማስፈን፣ ዋጋን የማረጋጋት እና ለኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ የማድረግ ተልዕኮ ለማሳካት አዋጁን ማሻሻል እንደሚገባ ስለታመነበ

14/06/2024

ፓርቲያችን ብልፅግና ሃገራዊ ገዥ ትርክቶቻችንን በማፅናት ብሔራዊ አንድነትን ለመፍጠር ይተጋል!

ፖርቲያችን ብልፅግና ከሚከተላቸዉ ዋንኛው እና የመጀመሪያው በሀገር ደረጃ የጋራ የሚያደርጉንን ገዥ ትርክቶችን በመገንባት ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማፅናት ነዉ።

ገዥ ትርክት ብሔራዊነትን ያማከለ
መደማመጥ የተሞላበት ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ የተሻለ ልማትን የምንሰራበት የፓርቲያችንን እሴት የሚያሳካ ድል አድራጊነት ነው።

ገዥ ትርክት የጋራ የወል ታሪኮቻችንን ወይም እምነቶቻችንን በታሪክ እንድናፀና/እንድንፅፍ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ አይነተኛ መሳሪያ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የሆኑ የጋራ ማንነት ያለን በህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት እሳቤ የምንኖር ህዝቦች ስንሆን ብሔራዊነትን ለማፅናት እንዳንሰራ የሚያደርጉን ሀይሎች እንዳሉም ይታወቃል ። ይሁን እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ከሚለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ስለሚበልጥ በብልፅግና ዕሳቤ ሆነን በርካታ የልማት ስራዎች ማጠናከር መደገፋችን አጠናክረን ቀጥለናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች ዋነኛው መነሻው አባባሽ ጉዳይ ነጠላ ትርክት መሆኑንና አንድ ነገር የሚፀናው በሀገሪቱ በተገነባው የጋራ ትርክት በመሆኑን በመረዳት ብዝሃነትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ለአሰባሳቢ ትርክት ቅድሚያ በመስጠት የሚያግባባንን አሰባሳቢ የጋራ ትርክት ማጉላት ይጠበቅብናል።

ፓርቲያችን ሀገራችን ለበርካታ አመታት የምትታወቅበትን የመተባበር እና የመደጋገፍ እሴቶቻችንን ለማጎልበት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን የአሁኑ ዘመን ትውልድም ከፋፋይ እሳቤዎች ራሱን በማራቅ በጋራ በሚያቆሙን ገዥ ትርክቶች ላይ በማተኮር የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ሊያደርግ ይገባል።

Photos from አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 13/06/2024

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ተግባርን በውጤት 3ኛ ሩብ አመት የወረዳ ማጠቃለያ አባላት ኮንፈረንስ መድረክ አካሄደ።

Photos from አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 10/06/2024

የአባላት ድጅታል መታወቂያ ምዝገባ ያለበት ሁኔታ ተገመገመ።
ሰኔ 02/10/2016 ዓ.ም
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ፅ/ቤት የአባላት ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ያለበት ሁኔታ በመገምገም ። በዚህ በጀት አመት እንደ ወረዳ ያሉንን አባል በዚህ ወር መጨረስ መቻል አለብን ሲሉ የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ አብደላ ሀሰን ገልፀዋል።

Photos from አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 10/06/2024

የቀደሙትን የኮሪደር ልማት ስራዎች ግምገማ ስናጠናቅቅ ቀጣዩን ግምገማችንን በስራው ስፍራ ተገኝተን እንደምናካሂድ ቃል ገብተን ነበር። የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሶስት ወር መርሃግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል።

በቀጣይ ስራ ሀብት ቁጠባ ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ በቀሪ ኮሪደሮች ስራዎቻችን ፈጣን እና ፈጠራ መር ልንሆን ይገባል። ጥራትን ማስጠበቅ እና ለዜጎቻችን ሁሉ የተመቸ ከባቢን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባራት ናቸው።

ይህ ፕሮጀክት የሚራመደው በብዙሃን ትብብር ነው። ከጅማሮው በስራችን ባገኘነው በጎፈቃድ ምስጋና አቀርባለሁ። ይህም በእቅድ እና አፈፃፀም ላይ የታየውን ጥረታችንን እና መልካም ፈቃዳችንን የመጠነ ሆኖ ታይቷል።

በዚህ ከተማችንን ለተሻለ ለውጥ ለማብቃት በተደከመበት ታላቅ ስራ ሂደት ውስጥ በዜጎቻችን ላይ ፈጥረነው ሊሆን ለሚችል አለመመቸት ይቅርታ እንጠይቃለን። ኢትዮጵያችን እንድትለወጥ በፅናት እንደምንሰራ በዚህ የኮሪደር ልማት ስራ ሂደትም ያሉ የዲዛይን እና የጥራት ክፍተቶችም ካሉ ማስተካከል እንደምንቀጥል እንድትተማመኑ ለመግለፅ እፈልጋለሁ።

በግሉ ዘርፍ ያሉ አጋሮቻችንን ጨምሮ ትናንት ምሽት በጎዳናዎች ፍቅራችሁን ለገለፃችሁልን፤ በአጠቃላይም በዚህ ስራ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Adisse Abeba
Addis Ababa
ADISSEABABA