07/03/2023
የፈጣሪ ያለ
Comedian Eshetu on TikTok #በአሁን ሰዓት በዶንኪ ትዩብ ከተወዳጆቹ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር የመጨረሻውን ሰዓት እየጠበቅን ነው:: #ኢትዮጵያ🇪🇹🇪ቲክቶክ #.....
እዉነቱን ብቻ እንነጋገር።
07/03/2023
የፈጣሪ ያለ
Comedian Eshetu on TikTok #በአሁን ሰዓት በዶንኪ ትዩብ ከተወዳጆቹ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር የመጨረሻውን ሰዓት እየጠበቅን ነው:: #ኢትዮጵያ🇪🇹🇪ቲክቶክ #.....
ሰበር ዜና
ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1_0 በሆነ ውጤት አሸነፈች
10/12/2022
እውነተኛ ፍትህ ለስራ !!
“ምንም ሳልሰራ ደመወዝ እየተከፈልኝ ነው” ያለው ግለሰብ ለተቋሙ ቅሬታ አስገብቷል
በዓመት 130 ሺህ ዶላር ደሞዝ የሚከፈለው ግለሰቡ “ቢሮ ገብቼ ጋዜጣ ከማንበብና ምሳ ከመብላት ውጪ ስራ የለኝም” ብሏል። በርካቶች ስራን በሚያማርሩበት በዚህ ወቅት አየርላናደዊው ግለሰብ “ሳልሰራ ደመወዝ እየተከፈልኝ ነው” ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል ሲል አል አይን ነው የዘገበው።
25/11/2022
Tarrif lela kifyaw lela.bemn yigenagnal
የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያው ምን ያህል በትክክል እየተተገበረ ነው? ታሪፍ ማሻሻያው ምን ያህል በትክክል እየተተገበረ ነው?
25/11/2022
Liyu Testo new
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ጎል ያስቆጠረ ብቸኛ ተጫዋች ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ጎል ያስቆጠረ ብቸኛ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡
በዓለም ዋንጫው በምድብ 8 ትናንት ምሽት ፖርቹጋል ጋናን ስታሸንፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፍጹም ቅጣት ምት የውድድሩን የመጀመሪያ ጎሉን በዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ደግሞ በተሰለፈባቸው 192 ጨዋታዎች 118ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።
ይህን ተከትሎም በተከታታይ አምስት የዓለም ዋንጫዎች ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል።
ሮናልዶ በ2006ቱ የጀርመን የዓለም ዋንጫ፣ በደቡብ አፍሪካው የዓለም ዋንጫ፣ በብራዚል የዓለም ዋንጫ፣ በ2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ እና በ22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ በተከታታይ ጎል ማሰቆጠር ችሏል፡፡
ሮናልዶ 192 ጨዋታዎችን ለሃገሩ ያደረገ ሲሆን 118 ጎሎችን በማስቆጠር የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡
22/11/2022
Great Ethiopia
ጨረቃ ላይ ውሃን ለማግኘት እንዲሰራ ኃላፊነት የተሰጠው ኢትዮጵያዊ የናሳ ተመራማሪ-ዶክተር ኢንጂነር ብርሃኑ ቡልቻ
**************
ወደ አሜሪካ ስመጣ የሚደግፈኝ አልነበረም፣ ነገር ግን ትልቅ ህልም ነበረኝ፡- ጨረቃ ላይ ውሃን ለማግኘት ላይ የሚሰራው ኢትዮጵያዊ የናሳ ተመራማሪ
ኢትዮጵያዊው የናሳ ተመራማሪ ዶክተር ኢንጂነር ብርሃኑ ቡልቻ በጨረቃ ላይ ያለውን ውሃ የመለየት ችግር መፍትሄ ለመስጠት ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመስራት ላይ የሚገኝ ሳይንቲስት ነው፡፡
ተመራማሪው ከዚህ በፊት ጨረቃ ላይ ውሃ ለማግኘት የሚያስችል በመጠን አነስተኛ የሆነ ቁስ የኳንተም ፊዚክስ ቀመርን በመጠቀም መስራቱ የሚታወስ ሲሆን ይህን ምርምሩን ከግብ ለማድረስም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
"ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ስመጣ የባህል ልዩነቱ እና የሚደግፈኝ ባለመኖሩ ተቸግሬ ነበር" የሚለው ኢንጂነር ብርሃኑ፤ "ሁሌም የማስበው ጠንክሮ መሥራት እና በትምህርት ስኬታማ መሆንን ነበር" ይላል፡፡
በልጅነቱ መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነብ ስለ አጽናፈ ዓለም/Universe/ አፈጣጠር እና ተያያዥ ክስተቶች ያነበባቸው ታሪኮች ስለ ህዋ ይበልጥ ጥያቄዎችን እንዲጠይቅ እና ምርምር የማድረግ ፍላጎት እንዲያድርበት ማድረጉን ለቢቢሲተናግሯል።
"በውስጤ ነገሮች እንዴት ተፈጠሩ የሚለው በጣም ያስደንቀኝ ነበር፤ ዩኒቨርስ ምን እንደሚመስል እና ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ የበለጠ ለማወቅ ትልቅ ጉጉት ነበረኝ" ሲልም ይገልፃል።
በልጅነቱ ለማወቅ እና ለመስራት በሚያልመው የህዋ ምርምር ዘርፍ ላይ ከብዙ ጥረት በኋላ የደረሰው ኢንጂነር ብርሃኑ፣ አሁን ላይ በጨረቃ ላይ ያለውን ውሃ የመለየት ችግር መፍትሄ ለመስጠት እና ሰዎች ጨረቃ ላይ መኖርን እንዲያልሙ የሚያስችል አስደናቂ ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛል።
ከሰሞኑ በሜሪላንድ የሚገኘው የናሳ ጎዳርድ የጠፈር በረራ ማእከል ኢንጂነር ብርሃኑ በዚሁ የምርምር ማዕቀፍ ውስጥ ያበለፀገውን ፕሮቶታይፕ ለማጠናቀቅ እንዲያስችለው 2.5 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ እንዳቀረበለት የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል።
በዚህ ፕሮቶታይፕ ላይ የሚሰራውን የቴክኒካል ስራ ለማጠናቀቅ ሌላ ሁለት ዓመት ሊፈጅ ቢችልም የተጀመረው ስራ እንደሚሳካ ኢንጂነር ብርሃኑ ያለውን ተስፋ ይገልፃል።
ውሃ ከምድር ወደ ጨራቃ ሊጓጓዝ ቢችልም ወጪው የማይቀመስ እና ስራው ውጤታማ ባለመሆኑ የኢንጂነር ብርሃኑና የቡድን አጋሮቹ ምርምር ትልቅ ውጤት የሚያስገኝ ነው፡፡
በዚህ የምርምር ዘርፍ ውስጥ ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች ጨረቃ ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ውሃ መኖሩ ቢረጋገጥም የውሃ ውህዶችን በትክክል መለየት ግን ሳይቻል ቆይቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በጨረቃ ላይ ያሉትን የውሃ አካላት ከውህዳቸው ጋር ለመለየት እና ብሎም በትክክል ቦታውን ለማመላከት የሚያግዘው የኢንጂነር ብርሃኑ የምርምር ስራ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
በምርምር ስራዎች ላይ ብዙ መሰናክሎች አንደሚያጋጥሙት የሚገልፀው ኢንጂነር ብርሃኑ ሁልጊዜም ማለምን እንደማያቆም፣ በህልሙ ላይ ደግሞ አቅዶ መስራት እንደሚፈልግ ይናገራል፡፡
20/11/2022
የሚመካ ብኖር በእግዚአብሔር እና በስራው ይመካ
በዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ዕለት አስተናጋጇ ኳታር በኢኳዶር 2 ለ 0 ተሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 22ኛው የዓለም ዋንጫ በደማቅ ሥነ ስርዓት ዛሬ ተጀምሯል።
አስተናጋጇ ኳታር ከደቡብ አሜሪካዋ ኢኳዶር ጋር የመክፈቻ ጨዋታዋን አድርጋለች።
በጨዋታውም ኳታር በኢኳዶር 2 ለ 0 ተሸንፋለች
ኳታር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 18 ቀን 2022 ድረስ ለምታስተናግደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ስምንት ስታዲየሞች መርሐግብሮቻቸውን ለማከናወን ተሰናድተዋል፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
17/11/2022
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 6 መሰረት የሚጸና ጋብቻ ተፈጸመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፍቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው፡፡
አንቀጽ 7 (1) - ወንዱም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈጸም አይችሉም፡፡
አንቀጽ 7 (2) - በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው ቢኖርም ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንዳቸው ወላጆች ወይም አሳዳሪ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት የፍትሕ ሚኒስትሩ ከመደበኛው የጋብቻ እድሜ ከሁለት ዓመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡
አንቀጽ 8 (1) - በቀጥታ የሥጋ ዘመዳሞች (በወላጆችና በተወላጆች) መካከል ጋብቻ መፈጸም ክልክል ነው፡፡
አንቀጽ 8 (2) - ወደ ጎን በሚቆጠር የሥጋ ዝምድና አንድ ወንድ ከእህቱ ወይም ከአክስቱ፣ እንዲሁም አንዲት ሴት ከወንድሟ ወይም ከአጎቷ ጋር ጋብቻ መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡
አንቀጽ 9 (1) - በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈጸም ክልክል ነው፡፡
አንቀጽ 9 (2) - ወደ ጎን በሚቆጠር የጋብቻ ዝምድና፣ ባል ከሚስቱ እህት ወይም ሚስት ከባሏ ወንድም ጋር ጋብቻ መፈጸም ክልክል ነው፡፡
አንቀጽ 26 (1) - በሃይማኖት ስርዓት መሰረት ጋብቻ ሊፈጸም የሚችልበትና የአፈጻጸሙ ስርዓት እንደየሃይማኖቱ ይወሰናል፡፡
አንቀጽ 26 (2) - በዚህ ሕግ ለማንኛው የጋብቻ አፈጻጸም መሟላት አለባቸው የተባሉት ሁኔታዎች በሃይማኖት ስርዓት መሰረት ለሚፈጸም ጋብቻም መሟላት አለባቸው፡፡
አንቀጽ 27 (1) - በባህል ስርዓት ጋብቻ ሊፈጸም የሚችልበትና የአፈጻጸሙ ስርዓት በአካባቢው ባህል ይወሰናል፡፡
አንቀጽ 27 (2) - በዚህ ሕግ ለጋብቻ አፈጻጸም መሟላት አለባቸው የተባሉት ሁኔታዎች በባህል ስርዓት ለሚፈጸም ጋብቻም መሟላት አለባቸው፡፡
16/11/2022
ሰበር ዜና
የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ከዛሬ ጀምሮ ይወጣል
*******************
የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚወጣ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የገንዘብ ሚኒስሩር አቶ አህመድ ሽዴ እና ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ኢትዮቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል በሚዛወርበት (ፕራይቬታይዝ በሚደረግበት) ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ መስጠታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ወደ ግል ለማዛወር አውጥቶት የነበረው ዓለም አቀፍ ጨረታ በአለም አቀፍ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝና በአገር አቀፍ ደረጃም ምቹ ሁኔታ ስላልነበረ መቋረጡን አስታውሰዋል።
ዓለም አቀፍ ኩባንያን ለማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ጨረታው ለቀጣይ ሶስት ሳምንታት እስከ እ.አ.አ ዲሴምበር 19 ቀን 2022 ክፍት ተደርጓል።
አሁን በተፈጠረው ስምምነት መሰረትና አለም አቀፋዊ ሁኔታውን ግምት ውስጥ በማስገባት ከሳፋሪኮም ቀጥሎ አንድ ተጨማሪ ኩባንያ ለማስገባት ጨረታ ወጥቷል ብለዋል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/
16/11/2022
ህዳር ፯\፫\፪፼፲፭ ዓ.ም።
የዓለም የሕዝብ ብዛት 8 ቢሊዮን ደረሰ
**********************
የዓለም የሕዝብ ብዛት 8 ቢሊዮን መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው ስሌት አመላክቷል።
እንደ ተመድ ስሌት በዛሬው ዕለት 8 ቢሊዮነኛው ሕፃን ተወልዷል። የዓለም ሕዝብ ቁጥር 7 ቢሊዮን የደረሰው የዛሬ 12 ዓመት ነበር።
በፈረንጆቹ 1950 የዓለም ሕዝብ ቁጥር 2.5 ቢሊዮን የነበረ ሲሆን ባለፉት 70 ዓመታት ውስጥ የሕዝብ ብዛቱ ከ3 እጥፍ በላይ ጨምሯል ሲል ቲአርቲ ገልጿል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/
16/11/2022
ኢትዮጵያዊያን በዓለም መድረክ፥
በዛውም በዳኝነት ስልጣን።ደስ ስል!!!!
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ በተባበሩት መንግሥታት የክርክር ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው ተሾሙ
**********************
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሰለሞን አረዳ ከ2023 እስከ 2030 ላለው ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የክርክር ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው ተሹመዋል።
የዳኝነት ምርጫው የተካሄደው እኤአ ህዳር 15 ቀን 2022 በኒውዮርክ በተደረገው 34ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።
አቶ ሰለሞን በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ25 ዓመታት በላይ የአገልግሎት ልምድ ያላቸው የህግ ባለሙያ መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የተመድ የክርክር ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው የሚሾሙ ዳኞች በዓመት ውስጥ ለ 6 ወራት ያህል ድርጀቱን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/