16/02/2022
▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓
(በቴዲ አፍሮ)
ርሀቤ ቢከሰኝ ~ ባዶ ሆዴን አይቶ
አፌ መሰከረ ~ ችሎት ላይ አዛግቶ
በህይወት ፍርድ ቤት
የተሾሙት ዳኛ ~ መፃፉን ሲገልፁ
ያልሰራ አይብላ ~ ይል ነበር አንቀፁ
ይህንን ስትሰማ
ፈጥና መጣችና ~ ሆና ጠበቃዬ
ከፍርድ አዳነችኝ ~ የሊስትሮ እቃዬ
እኔም እሱዋን ይዤ
አንገቴን ለስራ ~ ጎንበስ እንዳረኩት
ችግሬን በብሩሽ ~ ሲጠረግ አየሁት
የኩራቴን በትር
ወርውሬ ስጥለው ~ ከጄ ላይ ወደዛ
እንኳን የሰው ጫማ ~ የኔም ፊቴ ወዛ
ካመታት ቀጠሮ
ከጊዜ በኃላ ~ የዋለው ችሎት
ጥረቴን አየና ~ ቢፈርድልኝ ሀብት
ከትቢያ ተነስተው ~ እንዲሉ ከማማ
እኔም በተራዬ
ከላይ ተቀምጬ ~ አስጠረኩኝ ጫማ
እንግዲህ አዝናለው
ባለውለታዬ ~ ክብሬ ነሽ እያልኩዋት
ከታች ያነሳችኝ
የሊስትሮ እቃየን ~ ከላይ እረገጥኳት
እንግዲህ አዝናለሁ
ውድዋ…………… የሊስትሮ ዕቃዬ
ምንም እንኩዋን ~ ብትሆኝ ባለውለታዬ
በጫማ ስረግጥሽ ~ አይክፋሽ ግድ የለም
ባታውቂው ነው እንጂ
ለዋለላት ሁሉ ~ እንደዚህ ናት አለም
~||~
ከ ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro)
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ።
07/10/2020