ላምበረት አቡነ አረጋዊ የልማት ፕሮጀክት 2014

ላምበረት አቡነ አረጋዊ የልማት ፕሮጀክት 2014

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ላምበረት አቡነ አረጋዊ የልማት ፕሮጀክት 2014, School, Addis Ababa.

Photos from ላምበረት አቡነ አረጋዊ የልማት ፕሮጀክት 2014's post 31/10/2022
Photos from ላምበረት አቡነ አረጋዊ የልማት ፕሮጀክት 2014's post 31/10/2022

ተመስገን ተመስገን ተመስገን !! አምላከ አረጋዊ ፈቅዶ እና ወዶ ሺዎች ይጠራሉ የተፈቀደላቸው እና የመርጥካቸው ግን ይገኛሉ እና እጅግ ውብ እና ድንቅ በሆነ መልኩ የልማት ፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ምርቃት ስነ-ስርዓት ጥቅምት 20-2015 ዓ-ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ተካሔደ!!
ምስጋና
ሁሌም አብርነትዎ የማይለየን በጠራንዎ ቦታ ሁሉ ጊዜዎትን አጣበው የሚገኙልን በቡራኬዎት በጸሎትዎ ከጐናችን የቆሙልን የፕሮጀታችንን አላማ ጠልቀው የተረዱልን ለክቡር አባታችን የለሚ ኩራ እና የካ ክ/ከተማ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መላከ ምህረት ዘካርያስ አዱኛ ላሳዩን ትልቅ አብሮነት እና ብርታታችን ስለሆኑልን እና በቀጣይም አብረውን ስለሚሆኑ አምላከ አረጋዊ ይስጥልን!!
ለደብራችን አስተዳዳሪ እርሶን ያለ ቅን ልብ ያለው ለለውጥ ለስራ የሚተኩ የሰከኑ አባት የሚችሉትን ብቻ ሳይሆን የማይቻልዎትንም የሚጥሩ አባታችን መላከ ሰላም መኮንን ደጀኔ ፣ እንዲሁም ስራን ማሳደር የማይወዱት ነገር ቀለል አድርገው የሚረዱት ትጉህ የስራ ሰው የደብራችን ጸሀፊ ክቡር ቀስስ እና መምህር ዬሴፍ ፣ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤው አባላት ፣አቶ እስክንድር ከአባልነትም በላይ ካለው ቀንሶ እየሰጠ ለማሳካታችን ትልቁን ፍርሻ ትወስዳለህ ፣ አቶ እንዳለ በቀናነት ነገሮችን መፍትሄ በመስጠት ለመሳካቱ የአንበሳውን ድርሻውን ስለተወጡልን፣ መሪጌታ ኪነጥበብ ቄስ ዘላለም እና ሌሎቻችሁም ሁሉ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን ፣ የደብራችን ህንጻ ኮሚቴዎች ሁላችሁም ከልብ ከልብ በጻድቁ ስም እናመሰግናለ፣
የማህበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የሽያጭ ማእከላቱን ስለፈቀደልን እናመሰግናለን!!
የካ ደሳለኝ መዝሙር ቤት፣ ቦሌ መድሀሃኒአለም ጌቴሰማኔ ንዋይ ቅዱሳት መሸጫ ፣ ኡራኤል ቤ/ክ ህንጻው ስር የንዋየት ቅዱሳት መሸጫ፣ እስጢፋኖስ ቃለ አብ መጽሀፍት መሸጫ መደብር፣ ከልብ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
የደብራችን ካህናት እና ዲያቆናት፣ የቢሮ ሰራተኞች፣ ትኬቶችን በመሸጥ ለምእመናን የፕሮጀክቱን አላማ በማስረዳት ሰፊ ስራ ስለሰራችሁልን እና ከዚህም በኋላ አብራችሁን ስለምትሰሩ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
የሰንበት ት/ቤቱ በአገልግሎቱ አብሮን ስለነበር እናመሰግናለን!!
የአካባቢ ወጣቶች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ እስከምሽት እየቆያችሁ ለዚህ ውጥን ስኬት ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
ሚዲያ:-
ኢቲ አርት ሚዲያ ከማስታወቂያ ስራው ጀምሮ በቦታው ላይ በመገኘት በቀጥታ ስርጭት ለአለም እንድንደርስ ስላረጋችሁልን እና የልማቱ አጋር በመሆን አብራችሁን ስለነበራችሁ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
በማስታወቂያ ስራው ላይ የተሳተፋችሁልን አርቲስት ህይወት ጌታሁን ፣ አርቲስት ናዶስ አዳነ፣ አርቲስት ተወዳጅ ቤኩማ፣ አርቲስት ብስራት ገ/ጻድቅን በጻድቁ ስም እናመሰግናለን አብሮነታችሁ አይለየን
በመጨረሻም መጠራታችሁን አውቃችሁ ከልባችሁ መክራችሁ በቦታው ላይ በመገኘት የፕሮጀክታችን አካል ስለሆናችሁ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!

30/10/2022
30/10/2022

ዛሬ ጥቅምት 20-2015ዓ-ም ከ7:00 ሰአት ጀምሮ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ቦሌ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል ይተማል እርሶስ?? የዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት አካል እንዲሆኑ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች!! ከእርሶ የሚጠበቀው መገኘት ብቻ ነው!!!

Photos from ላምበረት አቡነ አረጋዊ የልማት ፕሮጀክት 2014's post 30/10/2022

ዛሬ ጥቅምት 20 - 2015 ዓ-ም ከ7:00 ሰአት ጀምሮ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን ተጋብዛችኋል!!!
መላው ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ለዚህች ድንቅ ቀን በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!! በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኦርቶዶክስ ከፍታ ማረጋገጫ ግዙፍ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ምርቃት ስነ-ስርዓት እለቱ ላይ ደርሰናል!!

29/10/2022

ኦርቶዶክሳዊያን ለቤተክርስቲያን ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለመስራት ስካይላይትን ሊያጥለቅልቁት 1ቀን ብቻ ቀረው!!

ነገ በእለተ ሰንበት እሁድ ጥቅምት 20-2015 ቦሌ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል አይቀርም!!! ይህንን መንፈሳዊ ጥሪ ለመላው አለም ያካፍሉ ሀገር ውስጥ ካሉ በቦታው ይገኙ!! ውጪ ከሆኑ በኢቲ አር ቲ ሚዲያ ፌስቡክ እና ዩቱብ ቻናል በተለያዩ ቲክቶክ አካውንቶች ላይ በቀጥታ ይከታተሉ

Photos from ላምበረት አቡነ አረጋዊ የልማት ፕሮጀክት 2014's post 28/10/2022

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር እያደረጉ ለመላው አለም ያድርሱ!!
ኦርቶዶክሳዊነት መትረፍም ማትረፍረፍም ነው!! ይህንን አንድ ላይ ሆነን የምናረጋግጥበት መርሃ ግብር ላይ ተገኙ!!
የፊታችን እሁድ ጥቅምት 20-2015 ቦሌ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል አይቀርም!!! ይህንን መንፈሳዊ ጥሪ ለመላው አለም ያካፍሉ ሀገር ውስጥ ካሉ በቦታው ይገኙ!! ውጪ ከሆኑ በኢቲ አር ቲ ሚዲያ ፌስቡክ እና ዩቱብ ቻናል በተለያዩ ቲክቶክ አካውንቶች ላይ በቀጥታ ይከታተሉ

27/10/2022

የፊታችን እሁድ ጥቅምት 20-2015 ቦሌ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል አይቀርም!!! ይህንን መንፈሳዊ ጥሪ ለመላው አለም ያካፍሉ ሀገር ውስጥ ካሉ በቦታው ይገኙ!! ውጪ ከሆኑ በኢቲ አር ቲ ሚዲያ ፌስቡክ እና ዩቱብ ቻናል በተለያዩ ቲክቶክ አካውንቶች ላይ በቀጥታ ይከታተሉ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa