Amaizing GRACE

Amaizing GRACE

Share

ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው የሞተውና የተነሳው እኛ በእርሱ በማመን በፀጋ ብቻ የዘላለም ህይወት እንድናገኝ ነው።

25/11/2025

JESUS CHRIST

15/11/2025

✔️የመቅደሱ መድረክ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን
የሚሰበክበት መደረክ ነው። #የአዳራሽ #መድረኮቻችንስ?
✔️በቤታቸውም ቢሆን የሚሰበከው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
#በእኛ #ቤትስ?
✔️በመቅደሱና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰበከው
ከስንት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ዕለት ዕለት ነው።
#እኛስ?
✔️ዕለት ዕለት መተው የሚያቅታቸው ነገር ቢኖር ስለ ኢየሱስ
መስበክና ማስተማር ነበር። #እኛስ?
✔️ሐዋርያቱን እንደዚህ ያደረጋቸው ምንድን ነው ብየ ሳስብና ስጠይቅ ወደ ልቤ የመጣው ምላሽ ምዕራ 2 ላይ የወረደባቸው መንፈስ እና ምዕራፍ 4 ላይ በድጋሚ ደግሞ የተሞሉት የመንፈስቅዱስ ሙላት ነው የሚል ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እኔና እናንተም በመንፈስቅዱስ ሃይል መሞላት ይሁንልን።
✔️በዚህ መጨረሻ ዘመን በቀረልን ጥቂት ዘመን ስለ ሌላ ነገር መስበክ፣ ማስተማር፣ መዘመር እና መወያየት ትተን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንስበክ፣ እናስተምር፣ እንዘምር ደግሞም እንወያይ።

👉ምን ትላላችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ? ጥቅሱ አይጠርማችሁም?

26/10/2025

“የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤”
— ቆላስይስ 3፥16

1. የእግዚአብሔር ቃል (ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ) በሙላት
ይኑርባችሁ፦
👉የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም አገልግሎት እና ህይወት መሰረት ነው። ከቃሉ የተቀዳ መዝሙር፣ ስብከት፣ ትምህርት፣ ጸሎት....ሲሆን ውጤታማና ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ይሆናል።

2. በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገስጹ፦
👉የእግዚአብሔርን ቃል እና ተግሳጽ በጥበብ ማስተላሉፍ ውጤታማ ያደርጋል። ማስተማሩና መገሰጹ ላይ ብቻ ሳይሆን በጥበብ ከማድረጋችሁ ላይም አተኩሩ። ብዙዎች ይገስጻሉ ግን ያለ ጥበብ ስለሚያደርጉት ማቅናት አይችሉም። ውጤታማ አይሆኑም። ስንማማርና ስንገሳሰጽ በጥበብ ይሁን።

3. በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊ ቅኔ...ለእግዚአብሔር ዘምሩ
👉መዝሙር ለማንም ሳይሆን ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ለእርሱ የምንዘምረውም በልባችን (ከልብ የመነጨ) ነው። መንፈሳዊ ቅኔ የሚለው Sensitive መሆንን ጭምር የሚያመለክት ነው።

ከቻላችሁ መልዕክቱን ካነበባችሁ በኋላ ከ3-5 ደቂቃ በማስተዋል በአንድ መዝሙር ከልባችሁ ለብቻችሁ ለእግዚአብሔር ተቀኙ።
ስለታዘዛችሁ ተባረኩ።

17/10/2025

👉በቅድሚያ ከታች የተቀመጡትን ሁለቱን ፎቶዎች ለተወሰኑ ሰከንዶች ሁለቱንም ለየብቻ ተመልከት።
👉ከተመለከትክ ሦሰት ጥያቄዎችን ልጠይቅህ መልሱን በራስህ አእምሮ ያዝ።

ጥያቄ 1፦
ይበልጥ የሳበህ የትኛው ፎቶ ነው?

ጥያቄ 2፦
የመጀመሪያውን ፎቶ ስታይ ትኩረትህ ያረፈው ከልጅቷ ፎቶ ላይ ወይስ ከጀርባ ካለው ተፈጥሮ ላይ ወይስ ከሁለታቸው ላይ?

ጥያቄ 3፦
ሁለተኛውን የልጅቷን ፎቶ ስታይ ትኩረትህ የት ላይ ወደቀ?

👉ምናልባት ትክክል ከሆንኩ የመለስካቸውን በአእምሮህ ውስጥ ያሉትን መልሶች ልንገርህ። የመረጥከውና ይበልጥ የሳበህ ፎቶ ሁለተኛው የልጅቷ ፎቶ ነው።
👉የመጀመሪያውን ፎቶ ስታይ ትኩረትህ ከአንዳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ከሁለቱም ላይ አርፏል። ይህ ማለት ከልጅቷ መልክና ከልጅቷ ጀርባ ካለው ተፈጥሮ (እጽዋት) ላይ አተኩረሃል ማለት ነው።
👉ሁለተኛውን ፎቶ ስታይ ደግሞ ትርጉም የሚሰጥ ሌላ ነገር ስለሌለ ትኩረትህ የልጅቷ መልክ ላይ ብቻ ሆኗል።

ትክክል ነኝ አይደል? Thank you

ዋናው መልዕክት፦
ሁለቱም የልጅቷ ፎቶዎች ናቸው። ነገር ግን ሁለተኛው በ Editing ተሰራና ከጀርባ ያለው ተፈጥሮ Blurred እንዲሆን (እንዲደበዝዝ) ተደረገ። Blurred መሆን ማለት ከልጅቷ ጀርባ የሆነ ነገር አለ ግን ምን እንደሆነ እንዳይታወቅ ተደረገ ማለት ነው።
በ Editting ይህ የተደረገበት ሁለት አላማዎች አሉ፦
✔️የመጀመሪያው አላማ፦ የልጅቷ ውብ መልክ ብቻ ጎልቶ እንዲታይ ስለተፈለገ ነው።
✔️ሁለተኛው አላማ፦ ደግሞ ሰዎች አንድም ሳያስቀሩ ሙሉ ትኩረታቸውን በልጅቷ መልክ (ውበት) ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ስለተፈለገ ነው። 100% ልጅቷ ላይ እንዲያተኩሩ ተፈልጓል።

👉ልክ እንደዚሁ የክርስቶስ አገልጋዮች Blurred (መደብዘዝ) አለባቸው። አላማውም፦ በእነርሱ ላይ ያለው የክርስቶስ መልክና ውበት ብቻውን ጎልቶ እንዲወጣና እንዲሁም ሰዎች ሁሉ እነርሱ በሚሰብኩትና በሚያገለግሉት ክርስቶስ ላይ ብቻ ትኩረታቸውን እንዲጥሉ ለማድረግ ነው። እውነተኛ የክርስቶስ አገልጋይ እርሱ ደብዝዞ ክርስቶስን ብቻ የሚያሳይ እንጅ ከክርስቶስ ጋር እኩል (ሃምሳ ሃምሳ) ደምቄ ልታይ የሚል አይደለም። የማገለግላቸው ሰዎች ትኩረታቸውን በክርስቶስ ላይ ብቻ ሳይሆን በእኔም ላይ ማድረግ አለባቸው የሚል አይደለም። እሱም ይታይ እኔም ልታይ የሚል አይደለም።
👉ተፈጥሮው እኛን አገልጋዮችን ቢወክል የልጅቷ መልክ ደግሞ ክርስቶስን ቢወክል ዋና መልዕክቱ እኛ እንደተፈጥሮው እንደብዝዝና ክርስቶስ እንደ ልጅቷ ጎልቶ ይታይ የሚል ነው። ሲቀጥልም እኛ እንደተፈጥሮው እንደብዝዝና የሰዎች ትኩረት እንደ ልጅቷ በክርስቶስ ላይ ብቻ ይሁን የሚል ነው።
👉በአጭር ቃል በእኛ ላይ ያለ አስደናቂ መልክ (ክርስቶስ) ስላሉ ለሰዎች ሁሉ እሱን አጉልተን ለማሳየት Blured እንሁን። እዩት እዩት እንጅ እዩኝ እዩኝ አንበል። እወቁት እወቁት እንጅ እወቁኝ እወቁኝ አንበል።

👉በ1ኛ ጢሞ 3:16 ላይ እግዚአብሔርን የመምሰል ታላቅ ሚስጥር ማለት በአጭሩ በስጋ የተገለጠውን፣ በመንፈስ የጸደቀውን፣ ለመላዕክት የታየውን፣ በአህዛብ የተሰበከውን፣ በአለም የታመነውንና በክብር ያረገውን ክርስቶስን መምሰል ማለት ነው። የክርስቶስ መልክ በእኛ ሙሉ በሙሉ ሲታይ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ወደ መምሰል መጣን ማለት ነው። ይህ እግዚአብሔርን የመምሰል ሚስጥር ደግሞ ዕለት ዕለት የምንለማመደው እንደሆነ ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞ 4:7-8 ላይ ጢሞቲዎስን "እግዚአብሔርን ለመምሰል ራስህን አስለምድ" ከሚለው ተነስተን መረዳት እንችላን። ለአሁኑና ለሚመጣው አለምም ተስፋ ያለውና ለነገር ሁሉ የሚጠቅም እንሆነ ቀጥሎም ይናገራል።

ማጠቀለያ፦ Blurred (እንደብዝዝ) እንሁን እና ክርስቶስ ብቻ በእኛ ላይ ይታይ። የሰዎች ትኩረት ሁሉም በእርሱ ላይ ብቻ ይሁን። አሜንንን
Andu in Christ

16/10/2025

#ትንቢቱ #ሲፈጸም

“ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።”
— ኢሳይያስ 53፥12

1. ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና 👇

“ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።”
— ማርቆስ 15፥37
“ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።”
— ዮሐንስ 19፥30

2. ከአመጸኞችም ጋር ተቆጥሮአልና 👇

ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዶች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ። መጽሐፍም፦ ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ ያለው ተፈጸመ።
---ማርቆ 15:27-28

3. ስለ አመጸኞችም ማለደ 👇

ሉቃስ 23:33-34
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³³ ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ በዚያ እርሱን ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ።
³⁴ ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት።

👉ብዙዎችን ይወርሳል እንደተባለም በሞቱና በትንሳኤው በክርስቶስ የምናምነውን እኛን የራሱ አድርጎናል። ወርሶናል። በአለም ላይ ያሉ በእርሱ ያመኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በእርሱ ተወርሰዋል። በነፍሱ የገዛን የእርሱ ተከታዮች ነን። እርሱን አምነን ተከትለነዋል። እርሱም የዘላለም ህይወት ሰጥቶናል። ለዘላላምም አንጠፋም። 👇
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁷ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
²⁸ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
²⁹ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
Please ይህን እውነት Share አድርጉት። 🙏🙏

22/08/2025

#የተነሳው እና #ያረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ አማኞች የስጋ ትንሳኤ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲያስተምር ቀጥሎ ያለውን ሃሳብ ተናገረ። ሙሉ ምዕራፉ የሚያወራው ስለ ስጋ ትንሳኤ እንደሆነ ባለመርሳት ቀጥሎ ያለውን አንብቡ።

“ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥23

👉በማይሞትና በማይበሰብስ አካል በክብር የተነሳውና ወደ ሰማይ ያረገው በኩሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ካስረዳ በኋላ በመምጣቱ (ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ) ግን ለእርሱ የሆኑት (ማርያምን ጨምሮ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑት በሙሉ) በማይሞትና በማይበሰብስ የትንሳኤ አካል በመነሳት ባለ ተራ ይሆናሉ ይለናል። ስለዚህ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በትንሳኤ አካል ከሙታን የተነሳና እንደ እርሱ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ ማንም የለም። ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማርያምም ከሙታን ተነስታ አርጋለች ብሎ ማስተማር የእግዚአብሔርን ቃል መካድ ነውና ወደ ቃሉ እንድትመለሱ እመክራችኋለሁ። ቀጥሎ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በማስተዋል ተመልከቱት።
“ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ #ማንም #የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።”
— ዮሐንስ 3፥13
👉ማንም የሚለው ቃል ማርያምንም ይጨምራል። እርሷም ከሌሎች በክርስቶስ ከሆኑ ወንድሞቿና እህቶቿ ጋር በመሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ጊዜ የሚጠብቃትን የስጋ ትንሳኤ ገና ትጠብቃለች። መድሃኒቴ ያለችው ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች አማኞች ብቻ ሳይሆን ለእርሷም አዳኟ ነውና።

29/07/2025

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥያቄ የሆነባችሁ ሃሳብ ካለ ኮሜንት ላይ አስቀምጡ።

Photos from Amaizing GRACE's post 24/07/2025

#አንድ #ጥልቅ #ነገር #ላካፍላችሁ

👉የመጀመሪያው የአይሁድ ቤተ መቅደስ የታነጸው በንጉስ ሰለሞን ዘመነ መንግስት ጊዜ ነበር። ጊዜውም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1000 ዓመተ አለም ገደማ ነው። ንጉስ ሰለሞን ከሞተ በኋላ የነገሰው ልጁ ሮብዓም ነበር። በሮብዓም ዘመን ግን አንድ የነበረው የእስራኤል መንግስት ለሁለት ተከፈለ። ወንድሙ ኢዮርብዓም አስሩን ነገድ የያዘበት ሰሜን እስራኤል ተብሎ ሲጠራ ዋና ከተማውም #ሰማርያ ነበር። ሮብዓም ደግሞ በነገሰበት ስፍራ ሁለቱን ነገድ ይዞ የቀጠለበት ደቡብ እስራኤል ሲሆን ዋና ከተማውም #ኢየሩሳሌም ነበር።

👉ከዚያም የሰሜኑ መንግስት (አስሩን ነገድ የያዘው ሰሜን እስራኤል) በጣኦት አምልኮ ምክንያት በ 722 ዓ.ዓ የአህዛብ መንግስት በሆነው በአሦር መንግስት ተማረከው ሄዱ አልተመለሱምም።

👉የደቡቡ መንግስት (ሁለቱን ነገድ የያዘው ደቡብ እስራኤል) ደግሞ በ 586 ዓ.ዓ ገደማ የአህዛብ መንግስት በሆነው በባቢሎን መንግስት ተማርከው ለ70 ዓመታት በባቢሎን ቆዩ። በዚህ ጊዜ ነበር ሰለሞን የሰራው ቤተመቅደስ የፈራረሰው እና የቤተ መቅደሱ የተቀደሱ ዕቃዎችም ወደ ባቢሎን የተጋዙት።

👉ነገር ግን ከባቢሎን ከተመለሱ በኋላ ሁለተኛውን ቤተ መቅደስ ሰርተው አጠናቀቁ። ካልተሳሳትኩ 263 ዓ.ዓ ገደማ ላይ አንቲያኮስ ኤጳፋነስ የተባለ አንዱ የግሪክ ንጉስ እሪያ (አሳማ) እንደሰዋበት እና መቅደሱን እንዳረከሰው ታሪክ ይናገራል። ከዚያ በኋላ ግን አይሁዶች እንደገና ቤተ መቅደሱን በማንጻት መጠቀም ጀመሩ። የሮም አንዱ ገዥ በሆነው በንጉስ ሔሮድስ ዘመንም ቤተ መቅደሱ ጥገና (እድሳት) እንደተደረገለት ይነገራል።

👉ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ እያለ በማቴዎስ 24:1-2 ባሉት ቁጥሮች ውስጥ ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ ትንቢት ተናገረ። ይህም ትንቢት በ 70 ዓ.ም የሮም ጀኔራል በሆነው በጀኔራል ታይተስ (ቲቶ) መሪነት በሮማውያን እጅ ወደመ (ፈረሰ)። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን አይሁዶች ምንም አይነት ቤተ መቅደስ ስለሌላቸው ሶስተኛውን ቤተ መቅደስ ለመስራት ዝግጅታቸውን ሁሉ አጠናቀዋል። ነገር ግን በ690 ዓ.ም ገደማ ቤተ መቅደሱን በሚሰሩበት በቀድሞው ቦታ ላይ ከመካ እና መዲና በመቀጠል ሶስተኛ ቅዱስ ስፍራ (መስጊድ) ሙስሊሞች ስላነጹበት እርሱን ማፍረስ ይጠበቅባቸዋል። ሆኖም ግን ሐሰተኛው መሲሕ ሲመጣ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊና ኢኮኖሚያዊ አለመግባባቶችን በመፍታት ለተወሰኑ አመታት ስለሚያስመስል በእርሱ ጊዜ በእርሱ አማካኝነት ሦስተኛውን ቤተ መቅደስ በሰላም ይሰራሉ። ለመስራት ሲነሱም በቅድሚያ መስዋዕት ያቀርባሉ።

#አሁን #ወደዋናው #መልዕክቴ #ልምጣ👇
👉እንደምታውቁት ቤተ መቅደስ በብሉይ ኪዳን ጥላነቱ የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለአለም አቀፏ ቤተ ክርስቲያን (Universal Church) ነው። በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የህያው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተብላ ተጠርታለችና (1ኛ ቆሮ 3:16)። አሁን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያድረው በእጅ በተሰራ ቤት ውስጥ ሳይሆን በክርስቶስ አካል በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው።

👉የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነችው የክርስቶስ አካል (ቤተ ክርስቲያን) የተመሰረተችው ደግሞ በታረደው በክርስቶስ ኢየሱስ ክቡር ደም (በበጉ መስዋዕትነት) በኩል ነው። የተዋጀችውና የነጻችው ፣ መንግስትና ካህናት የሆነችው በደሙ በኩል ነው። (ራዕ 5:9-10)። እርሷ እንደ ተቋም ከመምሰረቷ (ሐዋ 2) በፊት የክርስቶስ ኢየሱስ ክቡር ደም መስቀል ላይ ፈሷል (የእግዚአብሔር በግ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ተሰውቷል)። ቤተክርስቲያን የበጉ መስዋዕትነት ውጤት ናት። በጉ በደሙ ያስገኛት አካሉ ናት።

👉ልብ በሉ #የሰለሞን #ቤተ #መቅደስም #ሆነ #ከባቢሎን #ምርኮ #መመለስ #በኋላ #የተገነባው #ቤተ #መቅደስ #የታነጸው #አብርሃም #ልጁን #ይስሃቅን #ሊሰዋ #ባለበት #ስፍራ ላይ እንደሆነ አይሁዶች በሚገባ ያምናሉ ደግሞም ያውቃሉ። አብርሃም ልጁን ይስሃቅን ሊሰዋው ባለበት ጊዜ ግን በይስሃቅ ፈንታ በዚያ ቦታ #ሰው #ሳይሆን #እግዚአብሔር #ያዘጋጀው #አንድ #በግ ተሰውቷል።
➕“አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፥ #በልጁም #ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው።”
— ዘፍጥረት 22፥13

👉የሰለሞን ቤተ መቅደስም ቢሆን የተሰራው በዚያው ቦታ ሲሆን የበጉ ደም ከፈሰሰበት ከብዙ አመት በኋላ ነው። አብርሃም የሰዋው በግ ለክርስቶስ ጥላ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም። በጉ በይስሃቅ ፈንታ ተሰውቶ ይስሃቅ ከሞት እንደተረፈ ሁሉ የአዲስ ኪዳኑ የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ እኛ ምትክ ሆኖ በመሰዋቱ በእርሱ በማመን ከዘላለም ሞት ድነናል። ሰዎች ያዘጋጁት በግ ከዘላለም ሞት ሊያድናቸው አልቻለም እግዚአብሔር ያዘጋጀው በግ ግን ሃጢአትን ማስወገድ ብቃት ስላለው ከዘላለም ሞት አዳነን። እስራኤላውያን ወደ ሊቀ ካህናቱ ይዘውት የሚመጡት በግ የአንድን ሰው ሃጢአት እንኳን ማስወገድ ብቃት የለውም። እግዚአብሔር ያዘጋጀው በግ ግን የአንድን ሰው ብቻ ሳይሆን የአለምን ሃጢአት የማስወገድ ብቃት ተገኝቶበታል። አሜንንን
➕“በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።”
— ዮሐንስ 1፥29

16/07/2025

👉የተከፈለልህን አሜን ብለህ በእምነት ተቀብለህ ከማረፍ እና የከፈለልህን አካል ከማመስገን ይልቅ የማትችለውን በራስህ ጥረት ለመክፈል መግደርደር፣ መሯሯጥ እና መድከም #ትዕቢተኝነትህን ያሳያል። እግዚአብሔር ደግሞ ትዕቢተኞችን ይቃወማል። ስለዚህ በራስህ ለመጽደቅ ያለህን ከንቱ ጥረት ተወውና የእግዚአብሔር ነጻ የፍቅር ስጦታ በእምነት አሜን ብለህ ተቀበል።

👉የዘላለም ሞት ሊከፍልህ ቀን እየጠበቀ ያለው የሃጢአት ዕዳህ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሙሉ በሙሉ ከፍሎታል። አሜን ብለህ ከልብህ #በእምነት #ብቻ ስተቀበል የተከፈልህ በአንተ ላይ በፀጋ ይቆጠርልሃል።

👉እኔ የተከፈለልኝን አሜን ብየ በእምነት ተቀብየ በነጻነት፣ በሰላም፣ በእረፍት እና በጸጋ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር ከጀመርኩ 16 አመታት አልፈዋል። ክብር ሁሉ ሃጢአትን ማስወገድ የሚችለውን ብቃት ያለውን የመስዋዕቱን በግ (ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን) ለሰጠን ለእግዚአብሔር አብ፣ በራሱ ፈቃድ ራሱን በፍቅር ለአባቱ አስገዝቶ ወደ ምድር በስጋ በመምጣት በመስቀል ላይ ለታረደልን ለእግዚአብሔር ወልድና ክርስቶስ በደሙ በዋጃት በክርስቶስ አካል ውስጥ ላለው የርስታችን መያዣ ለሆነው ለእግዚአብሔር መንፈስ (ለመንፈስቅዱስ) ራሱን በሶስት አካላት ለገለጠው ለአንዱ አምላክ ይሁን። አሜንንን

በዘሬ አይግባ ያልኩት/Singer Elias Abeta 10/07/2025

#በዘሬ #አይግባ #ያልኩት (ዘማሪ ኤልያስ አብጤ)

ኦርጅናል መዝሙሩ ነው ሊንኩን ተጭናችሁ ስሙት። በዛውም ሰብስክራይብ በማድረግ ይተባበሩን።

በዘሬ አይግባ ያልኩት/Singer Elias Abeta “ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየ...

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa