Fenot Arte

Fenot Arte ሁሌም አዲስ በፍኖት አርት ቤት

" "ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል። ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ...
03/04/2024

" "

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል። ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል። አልጋው የሚገኘው በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው። ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል።

"በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል፣ በሀይቁ ላይ ዳክዬዎች ይዋኛሉ......ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ፣... ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል....." በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ ይተርክለታል። በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።

አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ጠራች። ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ነጭ ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ! "ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ። "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት። "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር አለችው።" ልብ የሚነካ ነገር.... ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።

አንዳንድ ሠዎች እንዲህ ናቸው እነሡ እየሞቱ የሠውን የሕይወት ብርሃን ያለመልማሉ። የሠው ህይወት ማዳን ባንችል እንኳን ቢያንስ ለሠው ተስፋ እንስጥ ይሄም የመልካምነት አንዱ ገፅ ነውና።🙏😊

💚 https://t.me/FENOT_ARTE 💚
💛 https://t.me/Loveerdey 💛
❤️ https://t.me/Loveerdey ❤️

መነበብ ያለባቸው መጻሕፍት
28/03/2024

መነበብ ያለባቸው መጻሕፍት

ግባ ትጠቀማለህ
13/06/2023

ግባ ትጠቀማለህ

እንሆ ጀምረናል ይከተሉን ያስተዋውቁን
13/06/2023

እንሆ ጀምረናል ይከተሉን ያስተዋውቁን

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fenot Arte posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category