19/08/2023
ብቻህን መቆም!
በህይወትህ ውስጥ ትልቁ ፈተና የልብህን እውነት ሰዎች እንዲረዱህ ማድረግ ነው። ቤተሰብ፣ ወዳጅ የልቤ የምትለው ጓደኛ ላይረዳህ ሁሉ ይችላል፤ የሚሻለው መተው ነው! አንዳንዴ ብቻህን መታገል ግዴታ የሚሆንበት ወቅት አለ።
እነሱ እንዲረዱህ የምታባክነው ጉልበትና ልፋት ዕድሜህን ነው የሚጨርሰው፤ እምነትና ተስፋህን ፈጣሪ ላይ ጥለህ ከልብህ ብትለፋ ግን የማይቻለውን ሁሉ አድርገህ በተግባር ታሳያቸዋለህ! ጠንከር በል ወዳጄ!