ሕይወት በየፈርጁ
Tefera Mulatu
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tefera Mulatu, College & University, ቃኘው ሻለቃ አደባባይ, Addis Ababa.
04/11/2025
30/05/2025
የአፋልጉኝ ጥሪ
ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግርማ ሞገስ ጨርቆስ ይባላል ግንቦት 13/5017 ከሚኖርበት ቦሌ አራብሳ አካባቢ እንደወጣ አልተመለሰም
ቤተሰብ በከባድ ጭንቀት ውስጥ ስላለ ወንድማችንን ያየ ወይም ያለበትን ቦታ የሚያውቅ በዚህ ስልክ ቁጥር እንዲጠቁመን በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን 🙏ቤተሰቦቹ በ0921912763 በመደወል ይተባበሩን ይተባበሩን🙏
https://www.facebook.com/sara.habeshi.31/videos/1558446301238405/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
11/05/2023
11/05/2023
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ባዕታ ማርያም ወርሃዊ
በዓል አደረሰን አደረሳችሁ።
እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄም ከእናቷ ከቅድስት ሐና “እም ሊባኖስ ትወጽእ መርዓት፡፡” ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች ተብሎ በተነገረው መሠረት
ነሐሴ ፯ ቀን ተፀንሰች፡፡
ግንቦት ፩ ቀን ሊባኖስ በምትባል አካባቢ በብጽአት ተወለደች፡፡
እመቤታችን በጾም በጸሎትም የተገኘች ናት፡፡
ንጽሕት በመሆኗም ማኀደረ መለኮት (የእግዚአብሔር ማደሪያ) ሆናለች፡፡
ከዚህ በኋላ እመቤታችን በእናት በአባቷ ቤት ፫ ዓመት ተቀመጠች
“ከመዝ ነበረት ውስተ ቤተ አቡሃ ወእማ ፫ተ ዓመት እንዘ ትጠቡ ሐሊበ እማ” (እንዳለ በነገረ ማርያም)፡፡
ኢያቄምና ሐናም ልጃቸውን ሲያሳድጉ ስላደረገላቸውም ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽመው እያመሰገኑት ፫ ዓመት ኖሩ በጾም እና በጸሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምጽዋት እየሰጡ በጐ ሥራን አበዙ፡፡
ልጃቸውን እመቤታችንን በንጽሕና እያሳደጉ ፫ ዓመት በተፈፀመ ጊዜ ቅድስት ሐና የተሳሉትን ስዕለት ለቅዱስ በማስታወስ ስዕለቱን እንዲፈጽሙ በነገረችው ጊዜ ደስ አለው፡፡
ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ‹‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ክርስቶስ ውበትሽን /ንጽሐ ባሕርይሽን/ ወድዷልና›› መዝ 44፡10-11 ብሎ እንደተናገረ ለወላጆቿ የብጽአት ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ከእናት ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ ፫ ቀን በ፫ ዓመቷ ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች፡፡
በዓታ ለማርያም ማለትም “የድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ማለት ነው፡፡”
ካህኑ ዘካሪያስም ስለምትመገበው ምግብ በተጨነቀ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከሰማያት ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጐናጽፎ ኅብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት የብርሃን ጽዋ እና የብርሃን መሶብ ይዞ ወደ ሰማይ ወጥቷል፡፡
እመቤታችንም ከዚህ በኋላ ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላአክት ጋር እየተጫወተች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡
የበላኤ ሰብዕ እመቤት እመቤታችን እኛንም በምልጃዋ ትጎብኘን አሜን
የእናታችን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት፣በረከትና ምልጃዋ አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addis Ababa