ከአለቃየ ዶክተር ቡርቲ ጋር ከስራ መልስ!
የምስራቁ ጽሀይ
በዚህ ፔጅ የማህበረሰብን ሞራል ሀይማኖት ባህልና ወግ የሚፃረር ማንኛውንም ጽሁፍ ማጋራት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ኢትዮጵያ
26/10/2025
የእውነት የዚህ አይነት ነውረኝነት የተሞላበት ድርጊት ተፈጽሞ ከሆነ እጅግ በጣም ያሳዝናል ብቻ ሳይሆን ያሳፍራል። እናም የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ይገባቸዋል።
ለሸገር ከተማ ፖሊስ፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለፍትህ ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም ሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ለምትሰሩ ድርጅቶች ሁሉ!
በትናንትናው ዕለት ሸገር ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሱፐር ደብል ቲ ኃ/የ/የ/ማ (የሮዳስ ቀለም እና ሱፐር ፋይበር ውሀ ማጠራቀሚያ አምራች) ዙርያ መሠረት ሚድያ የምርመራ ዘገባ ሰርቷል (https://tinyurl.com/48rbrfwr)
በዘገባው ላይ ድርጅቱ ሰራተኞቹ ላይ ከድብደባ ጀምሮ በርካታ ወንጀሎችን እየፈፀመ መሆኑ ተጠቅሷል። ማህበራዊ ሚድያ ላይ በዜናው ስር ከሚሰጡ አስተያየቶች ማየት እንደሚቻለው በርካታ ህዝብ ወንጀሉን እና በደሉን በደንብ ያውቀዋል፣ ነገር ግን ማንም ጉዳዩን ሊያወጣ አልፈለገም።
ዜናው መውጣቱን ተከትሎ በርካቶች ወደ መሠረት ሚድያ በመምጣት የደረሰባቸውን ዘግናኝ ግፍ፣ ድብደባ እና ወንጀል እየተናገሩ ይገኛሉ። እነዚህ ዜጎች "የኢትዮጵያ ልጆች ነን አድኑን፣ ያናግሩን ማስረጃ አለን" እያሉ ነው።
ለማሳያ እንዲሆን በምስሉ ላይ የሚታየው ግለሰብ የድርጅቱ ሰራተኛ የነበረ ነው። ከድርጅቱ መውጣት ፈልጎ ሲወጣ 2 ሚልዮን ብር ሰርቋል ተብሎ ሲወነጀል ከዚህ በፊት ሰዎች ላይ የደረሰውን ስለሚያውቅ ጠፋ፣ የድርጅቱ ባለቤት ግን ከተደበቀበት ካስያዘው በኋላ የወሰደው ወደ ህግ ሳይሆን ፓራላይዝድ እስኪሆን ድብደባ አስፈፅሞበታል። ከዚህ በኋላ በእግሩ ለመሄድ 10 ዓመት ይፈጅበታል እንደተባለ ሰምቻለሁ (ጉዳቱ ከጀርባው ላይ ሲሆን ሚድያ ላይ ለማቅረብ የሚከብድ ከባድ ጉዳት ስላለበት ይህ ከፊት የተነሳ ፎቶ ቀርቧል)።
ከዚህ ውጪ የአካል፣ የአዕምሮ፣ እና ፆታዊ ጥቃት ደረሰብን ያሉ ብዙ ናቸው፣ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች እንዳሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ደጋግመው ተናግረዋል። በቅጥር ግቢ ውስጥ በግልፅ የሰራተኞች ማሰሪያ እና መደብደቢያ ቤት እንዳለ የአደባባይ ሀቅ ነው።
እነዚህ ዜጎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው የዕለት ጉርስ ለራሳቸው እና ለቤተሰባቸው ለማግኘት ሲሉ ነው፣ የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ አጣርቶ ወንጀሉን ወደ ህግ እንዲመራ እንዲሁም ተጎጂዎች የሞራል እና የአካል ጉዳት ካሳ እንዲሰጣቸው መደረግ አለበት ብዬ አምናለሁ።
የሚድያ ስራም እንዲህ የተሸሸገን ጉዳይ አውጥቶ ለህዝብ ማቅረብ ነው።
#መሠረትሚድያ
Click here to claim your Sponsored Listing.