01/05/2026
የወራቤ ኮ/ ስ/ ሆስፒታል የሳይካትሪ መረጃ
የአእምሮ ጤና ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነውደ እኔንም አንታንም እነሱንም እናንተንም ይመለከታናል
01/05/2026
17/12/2025
Ethiopia launches first specialised TMS therapy for depression
Ethiopia has launched its first specialised programme offering Transcranial Magnetic Stimulation (TMS) therapy, a non-invasive treatment for depression, at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College. College Provost Dr Muluken Tesfaye described it as a significant step forward for mental health care.
At the inauguration ceremony, Dr Muluken said TMS therapy reflects growing investment in mental health and could expand access to treatment for thousands across Ethiopia.
Dr Muluken added that, as a Center of Excellence in Neuro-Modulation Therapies, the programme brings together cutting-edge technology, specialised expertise and evidence-based care to deliver innovative treatment options and improve patient outcomes. He explained that neuro-modulation therapies are advanced, non-invasive techniques designed to regulate neural activity, helping to treat a wide range of mental health conditions and neurological disorders, while also supporting the enhancement of cognitive functions.
The service is aimed at patients who do not respond to standard therapies such as medication or psychotherapy. TMS works by sending targeted magnetic pulses to stimulate specific brain areas, offering new hope for treatment-resistant depression.
The programme is supported by GIZ Hospital Partnerships, BMZ, and the Else Kröner-Fresenius-Stiftung, with MAG & More GmbH providing the TMS device and technical support.
The launch follows advanced training in Germany for SPHMMC staff at the Department of Psychiatry and Psychotherapy, University Hospital LMU in Munich. Those trained include Dr Surafel Worku, Country Lead for the BEAM Project, and Dr Meskerem Abebe, Head of Psychiatry at SPHMMC.
12/10/2025
11/10/2025
የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ተከበረ።
*************************************************
የዘንድሮው የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 34ኛ ግዜ በሀገራችን ለ14ኛ ግዜ "የአእምሮ ጤና አገልግሎትን በድንገተኛና ከፍተኛ አደጋ ወቅት ተደራሽ እናድርግ" በሚል መሪ ሃሳብ፣ በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት በተለያዩ መርኃ ግብሮች ተከብሯል።
የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ታሪኩ ታደሰ የአእምሮ ሕክምና ለረጅም ጊዜ ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱንና ከለውጡ በኋላ በመንግስት በተሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሁለንተናዊ ጤንነት በማረጋገጥና ለአእምሮ ጤና አገልግሎት ልዩ ትኩረት በመስጠት በዘርፉ ተጨባጭ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
ለአብነትም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ገፈርሳ ሳይት በ27 ሄክታር መሬት ላይ እንደ ሀገር የመጀመሪያ የሆነዉ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታ መከናወን መጀመሩንም ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስቴር ማኅበረሰቡና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የአእምሮ ጤና አገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት እና ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመረውን ተግባር ለማሳካት ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ከፊተኛ አማካሪ እና
ተወካይ አቶ ሌሌሳ አማኑኤል እንደተናገሩት በድንገተኛና ከፍተኛ አደጋዎች ወቅት የአእምሮ ጤና አገልግሎት መስጠት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዉ በተለያዩ አደጋዎች ሳቢያ ለስነ-ልቦና ቀውስ ለተጋለጡ ዜጎች ፈጣንና የተቀናጀ የአእምሮ ጤና አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በሀገሪቱ በሚገኙ የጤና ተቋማት የአእምሮ ህክምና አገልግሎቱን በማስፋት ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ህይወት ሰለሞን የዘንድሮው መሪ ሀሳብ የድንገተኛ አደጋዎችን ተከትሎ የሚከሰተውን የአእምሮ ጤና ችግር ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት ቅድሚያ መሰጠቱን አመላካች መሆኑን ገልፀዉ ፤ ለዚህም መንግስት የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ ችግሩን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን በበኩላቸው በአእምሮ ጤናና ህመም ላይ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ የግንዛቤ ክፍተቶች፤ በህሙማኑ ላይ አድሎና መገለል መኖር የህክምናው ተደራሽነት ውስንነት የሚያመጣ መሆኑን አንስተው በአሁኑ ጊዜ በሁሉም የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ የአእምሮ ጤና ክብካቤና የአእምሮ ህመም ህክምና እንዲሰጥ እየተሰራ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዉ፤የአዕምሮ ጤና ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኝ፣ ጥበቃ እንዲደረግለትና ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን፣ በተለይም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ለተጎዱ ሰዎች ተደራሽ እንዲሆን መስራት ይገባናል ብለዋል።
በመረሃ ግብሩ በዘርፉ ልዕቃን ጥናትና ምርምር ቀርበዉ የፓናል ዉይይት ተደርጎበት ምክረ ሃሳብ ተሰጥቶበት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጧል።
ጦርነት እና የአዕምሮ ጤና
ከዶ/ር ቤተል ጥበቡ
ተጨንቃለች፣ ቀና ብላ ሰው አታይም፣ አልፎ አልፎ ፊቷን ትጠርጋለች የሆነ ነገር ከፊቷ ላይ ለማውረድ የፈለገች ይመስላል፣ አንዳንዴ ትንጠራራለች ሰውነቷ የተጨማደደ ይመስል
ኮስተር፣ በረጅሙ ትተነፍሳለች የሆነ ሀይል ከሰውነቷ እንዲወጣ፣ ስትናገር ቀስ ብላ ነው፣ ሰው አትፈልግም ራሷን ታገላለች አንዳንዴም ታለቅሳለች
በሰፊው ዳስ ውስጥ ለብዙ ሆነው ይኖራሉ ካገሩዋ ተሰዳ ከመጣች ጊዜ ጀምሮ ሰላም የላትም
ከዛ ጦርነት ቀጠና በሰላም ስለወጡ ብዙዎች ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ፣ ለሷ ግን አሁንም ጨለማ ውስጥ ናት ያሳለፈችውን ነገር እንደ አዲስ በጭንቅላቷ ትኖረዋለች፣ ሁሉም ነገር ይታያታል፣ ሁሉም ድምጽ ይሰማታል፣ የቦታው ጭስ፣ የእለቱ ሙቀት፣ በሰዐቱ የነበራት ጭንቀት ሁሉንም እንደገና ትኖረዋለች ለሷ አሁንም እዛው ናት ጦርነት ውስጥ
ህፃናት በካምፑ ውስጥ ይሮጣሉ፣ ሴቶች በድንጋይ ጉልቻ ሰርተው ቡና ይጠጣሉ፣ ወንዶች ጥላ ስር ጋደም ብለው ይወያያሉ፤ ሁሉም ከጦርነት የተረፋ ናቸው ስለአሳለፉት ሰቆቃ ያወራሉ ፈጣሪን ያመሰግናሉ የጦርነትን አስከፊነት ያየው ነው የሚያውቀው
እሷ ግን ካምፑ ውስጥ አይደለችም፣ አንዳንዶች ሊያረጋጉዋት ይዘዋት ይወጣሉ፣ አሁን እኮ ሰላም ነው ይሏታል: አልፈነዋል ተረጋጊ የጓደኞቿ ምክር ነው፣ በርቺ እንጂ ይላሉ
እሷ ሁኔታውን ለማስታወስ ቅርብ ናት፣ የሰው መመሳሰል፣ የነገሮች ሽታ፣ ስለጦርነቱ ወሬ፣ የድምፅ መመሳሰል፤ የምታየው የምትሰማው ነገር ሁሉ ያስታውሳታል፣ እንደ ህልም የነበረችበትን ደግማ ትኖረዋለች
ሲነካት ይሰማታል፣ ይጎትታታል፣ ስትደፈር የነበረው ስሜት፣ ላንቃዋ እስኪበጠስ ስትጮህ፣ ስትሰደብ፣ የሰውየው ድምፅ፣ መልኩ፣ ሲቅርባት የነበረው ሽታ፣ ያወጣው የነበረው ድምፅ፣
ያየችው ሬሳ፣ የባሩድ ሽታ፣ ለህይወቷ ምን ያህል ፈርታለች ልሞት ነው፣ መሞት ለሁሉም አለ በዚህ ልክ ግን አጠገቧ ቀርቦ አያውቅም ያሳለፈችውን ጭንቀት አሁንም ትኖረዋለች፣ አለማስታወስ አትችልም ልትሸሸው ትሞክራለች ግን ሰላም አይሰማትም
አይኗን ትጨፍናለች፣ ጆሮዋን በጆቿ ይዛ ትጮሀለች፣ ሰውነቷ ተኮማትሯል፣ እግሩዋን ትሰበስባለች፣ ኮርነር ላይ ሆና ትጮሀለች፣ ያልባታል፣ ልቧ በፍጥነት ይመታል
የሚያስታውሳትን ነገር ሁሉ ትሸሻለች፣ አትተኛም ህልሙዋን ትፈራዋለች፤ እንቅልፍ ተኝታ አታውቅም፣ ደስታ ከራቃት ቆይቷል መሞትን ትመርጣለች፤ ከሞት ሸሽታ መጥታ፣ ሞት አማራት ሞትን ፈለገችው እሷ ስትፈልገው ደሞ ሞት ራቃት
አይሆንም አለች መሞት አለብኝ ይህ ስሜት መቆም አለበት ከዚ በላይ መሰቃየት አልችልም ጮኸች
ይህን ስሜት የሚያስቆመው ሀይል ምንድን ነው ከሞት በቀር ጠየቀች
ይህ የድህረ አደጋ የአዕምሮ ውጥረት ህመም (post-traumatic stress disorder ) ነው
ሰላም ቅንጦት አይደለም፣ ለአዕምሮ ጤና የቤተሰብ፣ የማህረሰብ፣ የሀገር ሰላም ለሁሉም ያስፈልጋል፡፡
ካለ አዕምሮ ጤና ጤና የለም
03/12/2023
Click here to claim your Sponsored Listing.