12/06/2022
በፕሮግራሙ ዙሪያ ጠቅለል ያሉ ነጥቦች‼
============================
(በተሰባሰበው ገንዘብ የኛው የሆነ ትልቅ ተቋምና አዳራሽ ብንገነባበትስ?)
||
✍ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ ታቅዶ የነበረው ዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር ሳይካሄድ ቀርቷል። በዚህ ዙሪያ መነሳት ካለባቸው ነጥቦች መካከል ብዬ የማስባቸውን ላካፍላችሁ ወደድኩ።
★
①) ለፕሮግራሙ አለመሳካት ሰበቦቹ ራሳቸው የፕሮግራሙ አዘጋጆች መሆናቸው ታውቋል። የተሳሳቱት ጥቃቅን የሚባል ስህተት ሳይሆን ቀድሞ ማጠናቀቅ የነበረባቸውን መሠረታዊ ነገር ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ አለመሳካቱን ቢያንስ ትናንት እንኳ ማሳወቅ አለመቻላቸው ነው። ቀድመው ቢያሳውቁ ኖሮ በአንፃሩ ብዙዎችን ከልፋት መታደግ ይቻል ነበር። እነርሱ ተሳስተው ታላላቆችንም አሳስተዋል። መሠረታዊ ሂደቶችን ያጠናቀቁ መስለው፤ ሌሎችም by default «ይሄንማ ሳያሟሉ አይቀርም!» በሚል እምነት መድረክ ላይና ሚዲያ ላይ ፕሮግራሙን አስተዋውቀዋል፤ አስተዋውቀናል። ትልቅ ፕሮግራም ብቻ ማለም በቂ አይደለም፤ ትልቅ ዝግጅትም እንደሚጠይቅ ማወቅ ያስፈልጋል። ካላወቁ የሚያውቅን መጠየቅና አጋር መፈለግ ይቻላል።
°
②) እንኳን እንደዚህ ትልቅ ፕሮግራም ማዘጋጀት ትንሽ ፕሮግራም ማዘጋጀት ምን ያክል ትልቅ ትግል እንደሚያስፈልግ አዘጋጆቹ ሰዎችና አላህ ብቻ ያውቁታል። እኛ ካምፓስ ስንማር ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች «የእንኳን ደህና መጣችሁ!» ፕሮግራም ለማዘጋጀትና ከተመራቂዎች ደግም የሽኝት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ስንት ፍዳ እንደምንበላ በተጨባጭ አውቃለሁ። ቦታ ማመቻቸት፣ ኡስታዞችንና ተጋባዥ እንግዶችን ማመቻቸት፣ ለምሳና ለሻይ ቡና ወጪ ገቢ ማሰባሰብ፣ ተሸላሚዎች ካሉ ለነርሱ ማፈላለግ፣ ጥሪውን ለተማሪዎች ማድረስ… ብቻ እንቅልፍ እንደት እንደሚነሳ አውቃለሁ። ከአላህ እገዛ ቀጥሎ በዙሪያችን የሚያግዙን ልምዱ ያላቸው ሰዎች ባይኖሩ ኖሮ እንደማናሳካው የታዘብኩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩ። ጭራሽ ሃገር አቀፍ ፕሮግራም ሲሆን ደግሞ አስቡት! ቢሆንም ግን መሠረታዊ ነገርን ሳያሟሉ ለጥሪ መቸኮል አያስፈልግም። ምነው ትኬት እንደት እንደሚቆረጥ ያመቻቹበትን ዘዴና ልፋት ለቦታው ተጠቅመውት በነበር!
°
③) ዙሮ ዙሮ ጥፋት ተከስቷል። እነዚህን ሰዎች አሁን ላይ ብንቀጣቸው፣ ብንገርፋቸው… ያጠፉትን ጥፋት ማካካስ አንችልም። ከክፍለ ሃገር ድረስ የለፉትንና ልባቸው የተሰበሩትን ሁሉ መጠገን አንችልም። የሆነው ሆኗልና አሁን መሄድ ያለብን ወደ መፍትሄው ነው። ዳሜጁ ተከስቷል፤ መሥራት ያለብን damage control ላይ ነው። መወቃቀሱ መፍትሄ የለውምና!
°
④) እኛ የሻነው ሳይሆን አላህ የሻው ሆኗል።
እንዲህ ብሎን የለ፦
(وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا)
«አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡»
[አል-ኢንሳን: 30]
(وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ)
«የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡»
[አ-ት'ተክዊር: 29]
√ ደግሞ ይህ የሆነው እኛ ለማናውቀው አላህ ግን ለሚያውቀው የተሻለ ኸይር ነገር ሊሆን ይችላል።
ስቴዲዬም ቢካሄድ ደግሞ እንደባለፈው አንዱ ባርቆብኝ ነው ብሎ ችግር ቢፈጠርና የሰው ህይዎት ቢጠፋስ? በቃ! ለበጎ ነው!
(وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ