ኑ ትምህርት እናጥና

ኑ ትምህርት እናጥና

Share

ይህ ገጽ ትምህርት የሚተላለፍበት ገጽ ነው

25/12/2022

🚺 #አትመኝ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡
?? #አትቅና፦ እንደ ቃየን ወንድምህን ትገላለህ፡፡
?? #አትስከር፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡
?? #ዓለምን አትመልከት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ

✅ #በአባቶች አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡
✅ #እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡
✅ #በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድትገባለህ
✅ #ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡
✅ #ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ፡፡
✅ #አትዘሙት፦ እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል፡፡

✅ #ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይትነሣለህ
✅ #ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡፡


#ሼርርርር

ቻናሎቻችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇👇
Telegram: https://t.me/ye_ewketmaid
Facebookየእውቀት ማዕድwket
YouTube:
https://youtube.com/

25/12/2022

1. ቡና ለጉበታችን

- በኢጣልያውያን ተመራማሪዎች የተሰራ ጥናት እንዳረጋገጠው ከሆነ ቡና መጠጣት በጉበት ካንሰር ከመያዝ ይከላከልልናል፡፡ ጉበታችን በሂፐታይተስ ወይም በቅባት መብዛት እና በመሳሰሉት በሽታዎች ሊጠቃ ይችላል፡፡ እነዚህም በሽታዎች በጉበታችን ላይ ጠባሳ እየፈጠሩ በመሄድ የጉበት ካንሰርን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ቡና መጠጣት ግን በጉበታችን ላይ ጠባሳ የመፈጥር እድልን ይቀንሳል፡፡

2. ቡና እና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች

- ቡና በውስጡ ለጤናችን የሚጠቅሙን ብዙ ነገሮችን ይዟል፡፡ ለምሳሌ ቫይታሚን ቢ2 (ሪቦፍላቪን) ፣ ቫይታሚን ቢ5፣ ማግኒዚይም እና ፖታሲየም የመሳሰሉትን ለጤና የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮች በአንድ ስኒ ትኩስ ቡና ውስጥ እናገኛለን፡፡ እንዲሁም ቡና አንታይኦክሲዳንት በውስጡ ስለያዘ ጤናችን ለመጠበቅ ይረዳናል፡፡

3. ቡና ያነቃቃል

- ቡና በውስጡ ካፊን የተባለው ንጥረ ነገር ስላለው ከድካም ያነቃቃል እንዲሁም ሀይል ይሰጠናል፡፡ በዚህ ጊዜም አእምሯችን ስለሚነቃቃ የማስታወስ ችሎታችን ይጨምራል፤ የደስታ ስሜት ይሰማናል፡፡ በተጨማሪም ቡና የድብርት ስሜትን ያጠፋል፡፡


4. ቡና እና አልዛይመር

- አልዛይመር በአብዛኛው ከ65 አመት በላይ የሆናቸውን ሰዎች የሚያጠቃ የመርሳት በሽታ ነው፡፡ እድሚያችን እየገፋ በሚሄድበት ጊዜ አልዛይመር እንዳይዘን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና ጤናማ አመጋገብን መከተል አለብን፡፡ በተጨማሪም ግን ቡና መጠጣት በአልዛይመር በሽታ የመያዝ እድልን በ65% ዝቅ ያደርገዋል፡፡

5. የስኳር በሽታን በ50 % ይቀንሳል

- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዘወትር ቡና መጠጣት በስኳር የመያዝ እድልን እጅግ ይቀንሰዋል፡፡ ነገር ግን የተረጋገጠ የስኳር በሽታ ላለባችው የስኳር መጠንን መቀነሱ በተለያ ነገሮች ሊለያይ ይችላል፡፡


6. በቆዳ እና ጡት ካንሰር የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል

- የጡት ካንሰር እና ቡና መጠጣት በቀጥታ ባይገናኝም፤ ቡና መጠጣት በተለይ ላረጠች ሴት በጡት ካንሰር የመየያዝ እድልን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

7. የሰው ልጅ ፀጉር እድገትን ይጨምራል

- ቡና መጠጣት የፀጉር ስሮችን በማነቃቃት ለፀጉር እድገት ይረዳል፡፡ በተጨማሪም የጸጉር መበጣጠስን ይቀንሳል፡፡

8. የፋይበር አወሳሰዳችንን ይጨምራል

- ቡና ከሌሎች መጠጦች የተሸለ የፋይበር መጠኑ ከፍ ያለ ነው፡፡ ፋይበር ደግሞ ለአንጀት ጤንነት፣ ለድርቀት እንዲሁም ኮሌስትሮልን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

9. ድብርትን/ የሚደብት ስሜትን/ ይቀንሳል
- ቡና ውስጥ ያለው ካፊን የተባለው ንጥረ ነገር ድብርትን ይቀንሳል፤ በተጨማሪም በድብርት የመያዝ እድልን ይቀንሳል ብለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

10. ኢንፍላሜሽንን ይቀንሳል

- ቡና የሰውነት ብግነትን ለመቀነስ የሚረዳ ንጥረ-ነግር በውስጡ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

11. በፓርኪንሰንስ በሽታ የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል

- አንድ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ በቀን ከ2-4 ሲኒ ቡና መጠጣት የፓርኪንሰን በሽታ ምልክቶችን ችጅጉን ቀንሶ ተገኝቷል፡፡

12. ቡና እድሜን ይጨምራል

- በእንግሊዝ አገር የሚገኝ አንድ የጥናት አሳታሚ ተቋም አዲስ የወጣ ጥናት መሰረት አድርጎ እንደጠቆመው በቀን ውስጥ ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት የጠጪውን እድሜ ላይ ለውጥ ያመጣል ይላል
የቴሌግራም https://t.me/generalknowlage111

17/12/2022

አርቲስት ሙኒት መስፍን ስለ አእምሮ ጤና
=========================
ብዙ አስገራሚ ስራዎች ስለሰራ ወጣት አነበብኩ። ደስ የሚል ቤተሰብ አለው። ብዙ ስኬቶች አስመስግቧል። የሚገርሙ ስራዎች ይሰራ ነበር። ብዙ እቅድ ነበረው። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እራሱን አጥፍቶ ተገኘ።

ወገኖቼ ሲጨንቃችሁና ግራ ሲገባችሁ ለጓደኞቻችሁ ደውሉ። ለቤተሰብ አሳውቁ። የሀይማኖት ሰዎችን አማክሩ። ወደ ሀኪም ሂዱ። አንዳንዴ ሰዎችን ማናገር ይከብዳል። "ተጨናንቄያለሁ እርዱኝ" ማለትም ይከብዳል። ግን ለብቻ ሲሆን በብቸኝነት ሲሆን የበለጠ ከባድ ነው።

አሜሪካ ራስ የማጥፋት ሀሳብ ያላቸውና የጨነቃቸው ሰዎች የሚደውሉበት 24 ሰአት የሚሰራ ነፃ የስልክ መስመር 988 አለ። ሁሉም ሀገር ላይ እንደዚህ አይነት አገልግሎት መኖር አለበት። ምንም አይነት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ብትሆን፣ ምንም አይነት ቤተሰብ ቢኖርህ፣ ምንም አይነት ስራ ላይ ብትሰማራ አእምሮ ደህና ካልሆነ ሁሉም ነገር እያለህ ምንም እንደሌለህ ልታስብ ትችላለህ። አእምሮህ ህይወት ትርጉም አልባ እንደሆነ ሊነግርህ ይችላል።

አእምሮህ አንዳንዴ ከመጠን ያለፈ ውሸት ሊነግርህ ይችላል። በማንኛውም ከባድ ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ነገሮች መልካም እንደሚሆኑ ተስፋ እንደሚኖርህ እመኛለሁ። ሁልጊዜ ተስፋ አለ። የስነ ልቦና ህክምና ውስጥ ተስፋ አለ። የቤተሰብና የጓደኛ እገዛ ውስጥ ተስፋ አለ። በእምነት ውስጥ ተስፋ አለ። በጊዜ ውስጥ ተስፋ አለ።

እገዛ ሲያስፈልግህ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበል። ሳይረፍድ ቶሎ እገዛ ማግኘት ደግሞ የተሻለ ነው። እኔ የስነ ልቦና ህክምና አድርጌ ብዙ ተጠቅሜያለሁ። እገዛ የሚያስፈልጋችሁ ሰዎች የስነ ልቦና ህክምና እንድታደርጉ አበረታታችኋለሁ። የሚስማማኝን የስነ ልቦና ህክምና ለማግኘት ጊዜ እንደወሰደብኝ አልደብቃችሁም። ሆኖም ያስፈልገኝ ስለነበረ 'ቴራፒ' ማድረግ አልተውኩም።

ሁላችንም ብዙ የአእምሮ ጤና ጉዳዮች አሉብን። ብዙ የስነ ልቦና ጠባሳ የሚተዉ ጥቃቶች በህፃንነታችን ወይም ካደግን በኋላ ደርሶብን ይሆናል። ለብቻችን ለመቋቋም መሞከር ከባድ ነው። እገዛና ድጋፍ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበሉ። እገዛ መጠየቅ ጥንካሬ ይፈልጋል። ለራሳችሁና ለምትወዷቸው ሰዎች ስትሉ ጠንከር ብላችሁ እገዛ ጠይቁ።

ሰላምና ፍቅር ለሁላችሁም። ሁላችሁም ደህና እንድትሆኑ እመኛለሁ። ለአእምሮ ጤና ትኩረት እንስጥ!!!!

ጸሐፊ፦ አርቲስት ሙኒት መስፍን
ትርጉም፦ ዶ/ር ዮናስ ላቀው
..
ሰብስክራይብ ያድርጉና ቤተሰብ ይሁኑ!
ለዩቲዩብ: እዚህ ይጫኑ👉https://youtu.be/PDUCC1WD5mw
ለቴሌግራም: እዚህ ይጫኑ👉 https://t.me/psychaddis

17/12/2022

🌀💠 የለውዝ /ኦቾሎኒ/19 የጤና በረከቶች 💠🌀

✅ ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ ከ1,6ዐዐ ዓመት በፊት በፔሩ የተገኘ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከዛም በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት ላይ ተሠራጭቶ በዓለም ታዋቂ ሆኗል፡፡ ለውዝ ከምግብነት ባሻገር ለጤናም ሰፊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገራል፡፡ እነዚህን ጠቀሜታዎች በዝርዝር አስቀምጠናል እንሆ…

1. በተለምዶ ከሚባለው ጋር በተዛመደ መልኩ በዕርግጥም ለውዝ ለተዋልዶ ስርዓት ጤንነት ተመራጭ ነው፡፡ በተለይም ከእርግዝና በፊትና በዕርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ በውስጡ የሚገኘው ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ወቅት በጽንሱ ዕድገት ላይ ሊያጋጥም የሚችለውን ችግር 70 በመቶ ያህል ያስወግዳል፡፡

2. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላል – በለውዝ ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኘው ማንጋኒዝ ለስብና ለካርቦሀይድሬት መፈጨት፣ ለካልሲየም በሰውነታችን ህዋሳት መዋሀድና በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን የተስተካከለ እንዲሆን ያስችላል፡፡

3. በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ጥሩው ኮልስትሮል እንዲጨምርና መጥፎው የኮልስትሮል ዓይነት ደግሞ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ በለውዝ ውስጥ የሚገኘው የመዳብ ማዕድን ሰውነታችን በልብ ህመም እንዳይጠቃ ይከላከላል፡፡

4. የሐሞት ጠጠር እንዳይከሰትና የሐሞት ከረጢት ጤናን ያስጠብቃል፡፡

5. ድብርትን ይከላከላል፡፡

6. የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡

7. የልብ ህመም፣ ካንሰርን፣ የነርቭ ህመሞችን እንዲሁም ከቫይረስና ከፈንገስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎችን ይከላከላል፡፡

8. የአእምሮ ብቃትን ከመጨመርም በተጨማሪ እንደ ፓርኪንሰንና አልዛይመር ዓይነት በሽታዎች እንዳይከሰቱ
ይረዳል፡፡

9. በካንሰር መጠቃትን ይቀንሳል፡፡

10. ሐይል ሰጪ ከመሆኑም በላይ ጥቂት በልተው ለረጅም ሰዓታት እንዳይርቦት ስለሚያደርግ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

11. በእርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ የሚወለዱ ህጻናት እንደ አስም በመሳሰሉት በሽታዎች እንዳይጠቁ ያደርጋል፡፡

12. ለታዳጊዎች የአካል ግንባታ ለውዝ እጅጉን ተመራጭ ነው፡፡

13. በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡

14. የጸጉር ስሮችን በማጠንከር ለጸጉር ጤንነት ተመራጭነው፡፡

15. ስትሮክ የሚሰኘውን ወደ አንጎል በሚሄደው የደም ፍሰት መዛባት ሳቢያ የሚከሰተውን የአንጎል ላይ አደጋ ይከላከላል።

16. ፍሪ ራዲካል በተሰኙት ሞሎክዩሎች ሳቢያ በሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ይቀንሳል።

17. እብጠትና ሌሎችን ከቆዳ ጋር የተያያዙ ህመሞችን ይከላከላል። ቆዳን ከውስጥ በማለስለስ የተለያዩ የቆዳ ችግሮችን ይከላከላል።

18. ለውዝ በተለያዩ የቫይታሚን ዓይነቶች የበለጸገ ነው።

19. ለውዝ በፖታሲየም፣ ማንጋኒዝ፣ መዳብ፣ ካልሲየም፣ ማግኒዚየም፣ ብረት፣ ሴሬኒየም እና ዚንክ በመሳሰሉት ማዕድናት የበለጸገ ነው። ቡናን መጠጣት ከጤና አኳያ
ያለው ጠቀሜታ፡-
– የማስታወስ አቅምን ይጨምራል
– ድብርትን ያስወግዳል
– ለራስ ምታት እና አስም ፍቱን ነው
– በኩላሊት ጠጠር እንዳንጠቃ ይከላከላል
– ጉበታችን እንዳይታወክ ይከላከልልናል
– በሰውነታችን ላይ በስራ ብዛት የሚፈጠሩ ህመሞች እንዳንጠቃ ይረዳል
– ለድንገተኛ ሞት የሚያበቃ የልብ በሽታ እንዳንጠቃ ይጠብቃል
– በስኳር በሽታ ከመያዝ ይከላከላል
– በነቀርሳ በሽታ እንዳንያዝ ይረዳል


ሼርርርር

01/06/2021

የስድስተኛ ክፍል ስነዜጋ ምእራፍ 3
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ
የእኩልነት አለመኖር ምን ጉዳት አለው ?
የመንግስት እኩልነት ምን ላይ ያስፈልጋል ?
የጾታ እኩልነት ምንድን ነው
የጾታ እኩልነት እንዴት ይገለጻል ?
የአካል ጉዳተኞች እኩልነት ምንድን ነው ?
የጾታ እኩልነት ምንድን ነው ?
የጾታ እኩልነት በምን ይገለጻል?
የአካል ጉዳተኞች እኩልነት ምንድን ነው
የሐይማኖት እኩልነት ምንድን ነው

18/05/2021

From grade 6 unit 2 short not
Coma used to list of some sing
Same coma used to join two sentence
Collocation is the grope of words
In the past tense ligula verbs add to –d/-ed
Consonant later after -y change to –i in the past
vowel words after -y add only –ed
-e cancel in the past
Some adjectives are in ligula
Consonant before one vowel dabble
>> >> two vowel don’t dabble vowel.

18/05/2021

የስድስተኛ ክፍል አማርኛ ትምህርት ምእራፍ 4
አንድን ነገር አሳጥረን ለመጻፍ በደንብ ማንበብ፣ ሃሳቡን መረዳት፣ ዋና ነጥብን በለየት፣ ሃሳብ አለመድገምና ቅደም ተከተል መጠበቅ ያስፈልጋል ።
ትምህርተ አንክሮ ውስጣዊ ስሜቶችን ይገልጻል ።
ህዝባር ቃልን ለማሳጠር፣ የጊዜ አቆጣጠርንና አድራሻን ለይቶ ለማወቅ ይረዳል
አያያዥ ቃላት ቃልን ከቃል፣ ሃረግን ከሃረግ፣ አ.ነገርን ከአ.ነገር ያያይዛሉ
አንድ ነጥብ ቃልን ለማሳጠር
ሁለት ነጥብ ቃላትንና የጊዜ መለኪያዎችን ለመግለጽ ይረዳናል
ሶስት ነጥብ ቃላትን ለመግደፍ ይረዳል
አራት ነጥብ የአረፍነ ነገርን መጠናቀቅ ያመላክታል
ትምህርተ ጥቅስ ስሜትን ለመግለጽ ይረዳል
ነጠላ ሰረዝ ነገሮችን ለመዘርዘር ይረዳል
ድርብ ሰረዝ አረፍተ ነገሮችን ይለይልናል
ስም = ድርጊት ፈጻሚ
ተሳቢ = ድርጊት የተፈመበት
ግስ = ድርጊት
ተጨማሪ ከመጽሃፋችሁ መልሱ

13/05/2021

የስድስተኛ ክፍል የተቀናጀ ሳይንስ ትምህርት ምእራፍ 2
ልዩ ቁስ በአንድ የተወሰነ ስፍራ ውስጥ የራሱን ባህሪ ይዞ ይገኛል
የልዩቁስ ባህሪያት ኬሚካዊና አካላዊ ተብለው ይከፈላሉ
ኬሚካላዊ ልንለካቸው የምንችላቸው ባህሪያት ናቸው
የአካላዊ ባህሪ አይነቶች 3 ናቸው
የልዩቁስ ሁነቶች ፈሳሽ፣ ጠጣርና ጋዝ ናቸው።
ልዩ ቁሶችን በስሜት ህዋሳቶቻችን መቅመስ፣ ማሽተት፣ ቀለሙን ማየት፣ መመዳሰስና ቅርጹን በማየት መለየት እንችላለን ።
የማይለወጥ ዋጋ የሚባሉት እፍጋት፣ ንጥነ ቅለትና የመሳሰሉት ናቸው ።
የእፍጋት ፎርሙላ ክብደት/ምድገት ነው ።
የምድገት ፎርሙላ ግ/(ሴ.ሜXሴ.ሜXሴ.ሜ) ነው
የውሃ ነጥበ ብርደት 0C ነው ።
የውሃ ነጥበ ፍሌት 100C ነው ።
ትነትና ፍሌት ይለያያሉ ።
ውሃን በማጥለልና በማፍላት ማጣራት ይቻላል
የፋብሪካ ዝቃጭ፣ የሰዎችና እንሰሳት ጽዳጅ፣ የቤት ቆሻሻ፣ ከመጽዳጃ ቤት የሚወጣ ጽዳጅ ውሃን ይበክላል ።
የምግብና የውሃ ብክለት ኮሌራ፣ አሜባ፣ ጃርዲያና ተቅማጥን ያስከትላል ።
የብልሃርዚያ በሽታ በቆሻሻ ውሃ በመዋኘት ይከሰታል ።
ኮሌራ ተቅማጥና ትውከትን ያስከትላል ።
ፈጣን የልብ ምት፣ ድካም፣ ደም ማነስና ራስን መሳት በኮሌራ ምክኒያት ይከሰታሉ
አሜባ አንታአሜባ ሂስቶሊሲስ በሚባል ባለአሃድ ህዋስ ይከሰታል ።
አሜባ የራስ ምታትንና የሆድ ቁርጠትን ያስከትላል
ጃርዲያ ጃርዲያ ላምባ በሚባል ቫይረስ ምክኒያት ይከሰታል ።
የጃርዲያ ምልክቶች ማቅለሽለሽና የሆድ ቁርጠር ናቸው ።
ብልሃርዚያ ውስጣችን በሚኖር ጠፍጣፋ ትል አማካኝነት ይከሰታል ።
የብልሃርዚያ አስተላላፊ ቀንድ አውጣ ነው ።
የብልሃርዚያ ምልክቶች ትኩሳት፣ የደም ማነስ፣ ሳልና የቆዳ ሽፍታ ናቸው ።
የብልሃርዚያን በሽታ መድሃኒት የገኘው አክሊሉ ለማ ነው ።
መስኖ ውሃን በሰው ሰራሽ ዘዴ ማጠጣትነው
መስኖ ውሃን ለመቆጠብ ፣ ጊዜን ለመቆጠብና በስትክክል ውሃን ለማዳረስ ይጠቅማል
መስኖ ድህነትን ለማጥፋት ፣ ስራ ለመፍጠርና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል ይረዳል
ለመስኖ ስራ መቆጣጠሪያ ያስፈልገዋል
ውሃን በመገደብ (በሃይለ ማይ) ኤሌክትሪክ ማመንጨት ይቻላል
ሴርያዊ እትበት የቮልቴጅ ተከፋፋይነት ፣ ተያያዥነት አላቸው
ኩልኩል እትበት ትይዩነት ፣ እኩል ቮልቴጅ ፣ ቀጥታ ግንኙነት አላቸው
ከዜርያዊ እትበት ይልቅ ኩልኩል እትበት ተመራጭ ነው
ከወደዳችሁት ላይክና ሼር አይለያችሁ እናንተም በመለጠፍ ተሳተፉ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Addis Ababa