24/05/2026
አስታውሱ፥ ተላላኪ አትሁን/ኑ።
እንዴት ሰው በራሱ ቤት፥ ሌላ የሚወስንለት ሰውን ያውም ተሽጦ፣ ባሪያ ሆኖ፥ ለሚስቱ ባል ይገዛል⁉🤔
ለዛ ነው፤ ሰዎች ለሆዳችሁ፣ ለከርሳች፣ ለጊዜያዊ ጥቅምና ዝና እራሳችሁን አትሽጡ። ህሊናችሁን በከርሳችሁ አትለውጡ/አትሸጡ የምንላችሁ። ነገ ደግሞ ሌላ ገበያ ላይ ገዢ ፍለጋ እንደምትንከራተት ያውቃሉ። ይንቁሐል። ያራክሱሐል።
አቶ ስብሐት ነጋ በአንድ ወቅት እንድህ ሲል ነበር በአንድ የያየሰው ሽመልስ ኢንተርቪው የተናገረው፦ "ላኪ ለጥቅሙ ነው። ተላላኪ ግን የራሱን ጥቅም ነው የሸጠው!" በማለት የተናገረው።
እናም እናንተ በሐገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ወገኖቻችን የወለጋ ተወላጆች፦
●ወገን መስለዋችሁ፣
●የተቀየማችሁትን ሰው የተበቀሉላችሁ መስሏችሁ፣
● መንግስትንም የሚገለብጥሏችሁ መስሏችሁ፣ የራሳችሁን ጥቅም ለሌሎች ሽጣችሁ፣
● በራሳችሁ ቤትና ንብረት ሌሎችን አዛዥ በማድረግ፣ የህዝባችንን ጥቅም ከመሸጥ አልፋችሁ፣
●አዋቂና ታዋቂ የሆንን መስሏችሁ፥
● የራሳችሁን ታጋዮች ስማቸውን እየጠራችሁ ስትሳደቡ፣ በሐሰት ስትከሱ ስትኮንኑ የነበራችሁት።
አሁንስ ተጸጸታችሁ⁉ አረጋገጣችሁ⁉ ወደፊትስ ምን ለመስራት አሰባችሁ⁉
አሁንም በድጋሚ አስታውስ፥ በገዛ ቀዬህ፣ በራስህ ሞት፣ በራስህ ህዝብ ላይ ታምጽባቸው ዘንድ፣ ክህደት ትፈጽምባቸው ዘንድ የገዙህ ሰዎች፣ ነገ አንተን እንደሚበሉህ እንዳትዘነጋ።
በቅድሚያ አስታውስ!! በሬ የሚሸጠው ለሁለት አላማው ነው። አንደኛ በሙያው፤ ሁለተኛው ለስጋው ነው። ስለዚህ ሰንጋ መሆንህን ወይስ ባለሙያ መሆንህን አስታውስ። ሰዎች የገዙህ፣ የመረጡህ በዬትኛው አቋምህ ነው። ለስጋ የተገዛ ሰንጋ፣ ለሙያ አይታማም። መጀመሪያውኑ የተገዛው ለስጋው (ለጮማው) ነው።
የተሰጠህበትን (የተፈጠርክበትን) ተሰጥኦህን ለይ። እወቅ። ለዚህ ነው፤ ሰዎች ከመሬት ተነስተው የወደዱን፣ ያከበሩን ያገዘፉን የመሰሉ ሰዎችን በተመለከትክ ጊዜ፦ > በማለት በአባባላቸው የሚያስጠነቅቁን።
ስለዚህ ትናንት እነሱን አልገዛም፣ አልሸጥም፣ ህዝቤንም አልሸጥም ያላቸውን ሰው፣ በሐሳብም፣ በብዕርም፣ በሪዎትም ....... ወዘተ ማሸነፍ ሲያቅታቸው፤ አንተንና መሰሎችህን ገዝተው ሲያሰድቡህ፣ ሲያዘልፉህ፣ በሐሰት ሰውን ሲያስኮንኑህ የነበሩት።
እነዚያ ሰዎች በገዙበት ዋጋ ልክ እንኳን ዋጋ እንደሌለህና በገዙት ነገር በበቂ ሁኔታ ማትረፍ እንደማይችሉ ሲያውቁ፣ ዋጋህን ዳግም አራክሰው፣ አንዴ ከስረናልና ዳግም ዋጋ አልባ አድርገው የሚጥሉህ።
ትናንት አቅም ያለህ፣ እውቀት ያለህ፣ ብልህና አስተዋይ አድርገው ያዳነቁህ ሰዎች ለምክክር እንኳን ቦታ እንደማይሰጡህ አሁን ካወክ፣ ዳግም ላለመሳሳት እና ላለመላላክ ይቅርታ ለራስህና ለህዝቡ ቃል መስጠት ይጠበቅብሐል።
መልካም ሰንበት!!"
ሰኔ 16-2018ዓ.ም። ዕለተ-ሰንበት (እሁድ)
አጉልዞ_ጥያቄ ከአንገር_ጉትን_ወለጋ
አድስ አበባ ኢትዮጵያ
በቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ👇👇👇
https://t.me/my_Angergutin_77
በዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ👇👇👇
https://www.youtube.com/
ይህ ቻናል በወለጋ አንገር ጉትንና በዙሪያው ለሚገኙ ህዝቦች የሚወያዩበት፣ መረጃ የሚለዋወጡበት እንድሆን ታስቦ የተከፈተ ህዝባዊ ቻናል በመሆኑ በሓላፊነት ስሜን፣ በሰከነ መንገድ ለህ...