03/05/2026
ቀን 25/08/2018
#የት/ቤታችን መስራችና የሰው ሀይል አስተዳደር የሆኑት የ #ዶ/ር መስከረም ለገሰ (Dr. Meskerem Legesse) ከ አሜሪካ ኮሎራዶ ዩኒቨርስቲ የተሰጣቸውን የ #ፒ.ኤች.ዲ ዶክትሬት ድግሪ ምክንያት በማድረግ #በመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የምርቃት ፕሮግራም ተካሄደ።
#በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ የመቄዶንያ አረጋዊያን፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ዘማሪያን፣ ቤተሰብ፣ የስራ ባልደረቦችና ጓደኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተዘጋጀው የምርቃት ፕሮግራም ላይ በመገኘት የዝግጅቱ ተካፋይ ሲሆኑ፦
#የመቄዶንያ አረጋዊያን ለዶ/ር መስከረም ከፍ ያለ ምስጋና እና ምርቃት ያቀረቡ ሲሆን.... አክለውም...
የሀይማኖት አባቶች በሰጡት መልዕክት ዶ/ር መስከረም ከእውቀት ጋር ትህትናን፣ ከስኬት ጋር አገልግሎትን በማጣመር ለብዙዎች ተምሳሌት መሆናቸውን ገልጸው ልባዊ ምርቃትና በረከት አቅርበዋል።
በተለይም የመቄዶንያ አረጋውያን በእናታዊና በአባታዊ ፍቅር የተሞላ ቃል በመናገር ዶ/ር መስከረም ለደረሱበት ከፍተኛ የትምህርት ማዕረግ እንኳን ደስ አለዎት ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። ይህ ምርቃት ለእርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለቤተሰብ፣ ለተቋም እና ለሀገር ጭምር የኩራት ጊዜ መሆኑ ጠቅሰዋል።
ዶ/ር መስከረም ለገሰ በትምህርት ዘርፍ ያሳዩት ትጋት፣ በአመራር ያሳዩት ብልህነት፣ እንዲሁም ለሰው ልጆች ያላቸው ርህራሄ የዚህን ክብር ባለቤት መሆን የሚገባቸው እንደሚያደርጋቸው ተነግሯል።
#ዶ/ር መስከረም በበኩላቸው ይህ ስኬት የእኔ ብቻ አይደለም የሁሉም ቤተሰቦቼ እና ወዳጅ ዘመዶቼ ነው። ባሳለፍኳቸው አመታት ከጎኔ ላልተለያችሁ ወዳጆቼ እና ቤተሰቦቼ አመሰግናለሁ በማለት ይህን ላደረገች እና ሁልጊዜም በስራዬ ሁሉ የማስቀድማት፣ ሁልጊዜም የምጠራት፣ ፈጥና የምትደርስልኝ እናቴ #ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ከእነ ልጇ ክብሩን ትውሰድ በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ ታላቅ የምርቃት ፕሮግራም በደስታ፣ በምስጋና፣ በአባቶች ምርቃትና ፀሎት ተጠናቋል።