Mekdes,behailu & Frainds Construction Campany

Mekdes,behailu & Frainds Construction Campany

Share

please! if you want to build your house,business centers,schools & other type of construction including roads you are wellcome!

30/05/2024

ከሲኖዶስ የምጠብቀው እና የምጠይቀው

አቤቱ ጌታዬ እና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሳላውቅ በድፍረት አውቄ በትዕቢት ከመናገር እንድትጠብቀኝ እለምንሃለሁ። ጌታዬ መድኃኒቴ ኢይሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ በደምህ ከመሠርትሃት በኪዳንህም ካቆምካት፣ አካልህ ከሆነች፣ ብልት አድርጋ ከምትሰበስበን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኅብረት ከሚያወጣ ድፍረት፣ ምን አገባኝም ከሚል ፍርኅት እንድትጠብቀኝ እኔ ከሁሉ የማንሰው ኃጢአተኛ ልጅህ እለምንሃለሁ። ጌታዬ ሆይ ከእንግዲህስ ወዳጆቼ እንጂ ባሪያዎቼ አልላችሁም ብለህ ባከበርሃቸው፣ ምሥጢራትህንም ሁሉ በገለጽህላቸው ፍጹማን ወዳጆችህ፣ አንተ ታማኝ መልካም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ብለህ በምታከብራቸው ትጉኃን አገልጋዮችህ፣ ለባሕርይህ ለማይስማማ ሞት ራስህን አሳልፈህ በሰጠህላቸው ንጹሐን ምእመናን በጎችህ ብለህ እንኳን የአባቶቼን የየትኛውንም ሰው ኅሊና ሊጎዳ ከሚችል ክፉ ሐሳብም ሆነ ንግግር ትጠበቀኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። ጌታ ሆይ ከግብዝነት፣ ከአድርባይነት እና ከሚታወቅም ከማይታወቅም ጥፋት እንድትጠብቀን በጎውን እና እውነተኛውን ነገር ብቻም ለመናገር ከአንተ ውጭ እንኳን እኛ የበቁትም ቢሆኑ አይቻላቸውምና ስለቅዱሳንህ ሁሉ ይልቁንም የባሕርያችን መመኪያ የደኅንነታችን ዘውድ ስለምትሆን ንጽሕት እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ በመልካሙ መንገድ ብቻ ምራን፣ እኔንም ከዚህ መንገድ አታውጣኝ አሜን። ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ፤ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሜን።

አንዳንድ ሰዎች ስለሲኖዶስ በጻፍናቸው ተነሥተው ጉዳዩን ለመጠምዘዝ ከተቻለም መለያየት እና ጸብ በመፍጠር የሚፈልጉትን ለማሳካት እንደሚጥሩ ስለተሰማኝ፣ በቅንነት ሆነው ጥያቄያችንም የመብት ጥያቄ የመሰላቸው እና እራሳቸውንም የሆነ አካባቢ ተወካይ አድርገው የመብት ጥያቄ ጠያቂ እና አስተባባሪ ሆነው ስላየሁ የእኔ እና እኔንም የሚመስሉ ወንድሞቼ ጥያቄ ምን ዓይነት ጥያቄ እንደሆነ ስለቅዱስ ሲኖዶስ ያለኝን እምነት በማስቀደም በመግለጽ ጥያቄዬን በድጋሜ አቀርባለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፦

ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት አስፋፊዎች የመላእክት ወንድሞች የሰማያዊ ዜጎች አንድነት እንጂ የከርስቲያኖች የየአካባቢው ተወካዮች የሚሰበስቡበት ምክር ቤት እንዳለሆነ በደንብ አዋቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመጡ አባቶች ቢገኙበትም የየቋንቋቸው ወኪሎች ስብስብ እንዳልሆነም በደንብ አውቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከየአካባቢው ተወልደው አድገው በመጡ አባቶች የተመላ ቢሆንም የየተገኙበትና የየመጡበት አካባቢ ተወካዮች እና የወንበር ምድብ ቆጣሪዎች ስብስብ እንዳልሆነና ሊሆንም እንደማይችል፣ እንደማይገባውም በደንብ አውቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በሰማይ ያለች የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ሆነው ያገለግሉ ዘንድ የሚላኩ የእግዚአብሔር አምባሳደሮች ስብስብ እና ለላካቸው ለእግዚአብሔር መንግሥት ፍላጎት ብቻ የሚሠሩ በተፈጥሮ ከሰው ወገን ቢሆኑም በክህነት ምክንያት ከመላእክት ወገን የሆኑ እና እንደ መላእክትም ለሁሉም እኩል ቅርብ የሆኑ ሊሆኑም የሚገባቸው አባቶች ስብስብ እንደሆነ አምናለሁ። ከዚህም የተነሣ ከመካከላቸው ከላከው ከእግዚአብሔር እና ከሾመችው ከአካሉ ከቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ወጥቶ የራሱን ፈቃድ የሚከተል፣ የምድራዊ መንግሥታትን ፈቃድ ለመፈጸም እና ለማስፈጸም የሚሠራ አካል ቢገኝ ከማኅበረ መላእክት ወገን ሳለ የራሱን ሌላ መንግሥት ማቋቋም ከፈለገ ከዲያብሎስ እና እርሱን እሺ በጄ ካሉት ከሠራዊቱ የሚመደብ እንደሆነ አምናለሁ፤ አውቃለሁም።

በሐዋርያት መዓርግ ተሹሞና እና ተሰይሞ በጉባኤያቸውም ተገኝቶ እውጭ ላሉት ምሥጢር የሚሰጥ፣ ከእነርሱም ጋር የጥቅም ውል ያለው ቢኖር አልደነቅም። እንዲህ ያለው ከሐዋርያት ሲኖዶስ እያለ ከአይሁድ ጋር የጥቅም ውል የተዋዋለ እና ከጉባኤያቸውም የተሰናበተውን ይሁዳን እንደሚመስል እና በእርሱ ምክንያትም ሌሎች እንደማይተቹ በደንብ ተምሬያለሁና።
ረቂቅ ባሕርይ በነበረው በሳጥናኤል ምትክ ከመሬት አፈር የተፈጥረው አዳም እንደተተካ፤ በይሁዳም ምትክ ማትያስ በሐዋርያት እጩነት ቀርቦ በዕጣ እንደገባ ከአባቶቼ ተምሬያለሁ፣ አዋቃለሁምና የሚወጣ ቢኖር አልደነግጥም አልረበሽምም። እንዲህ ባላው ሰው ምክን ያት ቤተ ክርስቲያን ስሟ እንደማይጎድፍ ክብሯ እንደማይቀንስ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ አስቀድሞ አለማስገባት እየተቻለው ለይሁዳ እድሉን በመስጠት አስተምሮናልና።

ቅዱስ ሲኖዶስ ለእጃችሁ በትር አትያዙ የተባሉ ሐዋርያት ወራሽ እንጂ ሰይፍ፣ ጎራዴና እና ዱላ ይዘው ክርስቶስን ለመያዝ የመጡ፣ ዳዊት በመዝሙሩ አገቱኒ ከለባት ያላቸው ለምድራዊ ገዥዎች ፍላጎት የሚጮሁ የዚያ ዘመን አይሁድ ወራሽ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ አምናለሁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዐመጻው ምክንያት መልአከ እግዚአብሔር በሰይፍ እጁን የቀጣውን ታውፋንያን ንስሐውን ተቀብሎ በተአምራት እጁን መልሶ ዐመጸኛውንም ወደ ትሕትና እና መታዘዝ የሚመልሱ የቅዱስ ጴጥሮስ ልጆች ስብስብ እንጂ እንደ አውሳብዮስ እና ጓደኞቹ የመንግሥታትን ጉልበት ተጠቅሞ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍሉ ሰዎች ስብስብ እንዳለሆነ አውቃለሁ፣ እንዲህ ሆኖ እንዲኖርም እጠብቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት እንደ ጠቢቡ ሰሎሞን ረቂቅ ፍርድ ፈርዶ ሕዝቡን የእግዚአብሔርን መጋቢነት የሲኖዶስን መንፈስንቅዱሳዊነት ሊያሳይ እንደሚተጋ እንጂ እንደ ኢሳይያስ የንጉሥ ድምፅ ፈርቶ እኔ ምን አገባኝ ብሎ ቤተ ክርስቲያንን ለዖዝያን ፍላጎት አሳልፎ በመስጠት ለምጻም የሆኑ ሰዎች ስብስብ እንዳልሆነ ፣ እንደማይሆን፣ ሊሆንም እንደማይገባው አምናለሁ፤ እጠብቃለሁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ተጭንቆና ተጠብቦ እንደ ጳውሎስ እስከ ዕልዋሪቆን እንደ በረተሎሜዎስም በላእተ ሰብእ ያሉበት ድረስ ሔዶ ለመስተማር የሚያስቡ አባቶች ስብስብ እንጂ እንደ አካባቢ የልማት ድርጅቶች በየአካባቢው ሕንፃ ለመሥራት ግንብ ለማቆም የሚሯሯጡ ዉሉደ ባቤል ደቂቀ ናምሩድ ስብስብ እንዳልሆነ አምናለሁ፣ ተስፋም አደርጋለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ እቄሣር ግቢ ቢገባ እዚያ ያሉትን ለውጦ እንደ ጳውሎስ ከቄሳር ቤት የሆኑት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል የሚሉ ጥቡዓን ስብስብ እንጂ እንደ ዴማስ በከተማ ውበት በቤተ መንግሥት ግርማ ተሰልቦ አላማውን ለውጦ የሚኖር ከተሜዎች ስብስብ እንዳለሆነ እረዳለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ዲዮስቆሮስ ጥርሱ እስኪረግፍ ቢደበደብ እንደ አትናቴዎስ አምስት ጊዜ ቢሰደድ በትዕግሥት መከራውን ተቀብለው ቤተ ክርስቲያንን የሚያሻግሩ ፣ ዐለም ትቷችኋል ቢባሉ ልክ እነደ አትናቴዎስ እኔም ዐለምን አልፈልገውም የሚሉ ልበ ሙሉዎች ስብስብ እንጂ በቤተ መንግሥት ማዕድ እና ሺንገላ ልባቸው የሚማልል አባቶች ስብስብ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ እጠብቃለሁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ሲሞን ገንዘባቸውን ይዘው እናንተ የያዛችሁትን መዓርግ ልያዝ፣ ጓደኞቼ ከደረሱበት ልድረስ ብለው በእኔ ጊዜ ነው ወይ መመሪያ የሚወጣው እያሉ ዘመድ አዝማድ ስጦታ አስይዘው በመላክ፣ ውለታ ቆጥረው በማስታወስ የሚወተውቱ ሲሞናዊያንን ገንዘብህ ይጥፋ፣ ሀሳብህም አይፈጸም እያለ እነርሱን ትቶ ማትያስን በይሁዳ ፈንታ በተካበት መንገድ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሚሆኑትን የሚሾም ወራሴ ጰጥሮስ ወሐዋርያት እንደሆነ አውቃለሁ አምናለሁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሠራኤ ሕግ ወፈጻሜ ሕግ የሆነውን ጌታቸውን የተከተሉ፣ ሙጽአ ሕግ የሆነችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በሕገ እግዚአብሔር በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈጽሙ አባቶች ስብስብ እንደሆነ አምናለሁ፣ አውቃለሁም።

ለዚህም ነው በዘወትር ጸሎታችን ያለውን እንደ ሁሉም ክርስቲያኖች ሁሉ ዕለት ዕለት “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” ብለው ያስተማሩኝን የማምነው፣ የምመሰክረው፣ የምጸልየውም።

ቤተ ክርስቲያን ከጉባኤያት ፣ ከምክር ቤቶች፣ ከስብሰባዎች ሁሉ በላይ የሆነችውም በተፈጥሮዋም፣ በአሠራሯም፣ በሒደቷም ከሁሉም በላይ በሆነው በጌታዋ በቤዛዋ በመድኃኒቷ እንዲህ ጸንታ የምትኖር ስለሆነች እና መሆንም ስላለባት እንደሆነ አውቃለሁ፣ አምናለሁም።

አንዳንድ ሰዎች ዘመን ሰጠን፣ ጉልበት አገኘን ብለው ይህን አስትተው እንደ ጎሣ ምክር ቤት፣ እንደ ፌዴሪሽን ምክር ቤት፣ እንደ ወንድማማቾች እድር፣ እንደ ተወላጆች ማኅበር፣ እንደ መሳሰሉት ቅርጽ እና መልክ ይዛ እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ መሆኗ ቀርቶ እንተ ታሕተ ኩሉ መንግሥታት፣ ፓርቲያት ፣ ብሔር ወጎሣ ወመማክርት እንድትሆን የሚፈልጉትን ሁሉ ነፍሴ አጥብቃ ትጸየፋለች፣ በሚቻለኝም ሁሉ እንደ አባቶቼ ይህን እቃወመዋለሁ። እንዲህ እንዲሆን የሚመኝ የሚሠራ ካለም ክርስቶስን ረዳቴ እና ጌታየ አድርጌ ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሞንን እንደረገመው እረግመዋለሁ፣ ከኅብረቱ እንደለየውም ቢያንስ ራሴን ከእንዲህ ያለው እለያለሁ።

የእኔ ጥያቄ ለሲኖዶስ፦

እኔ ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የመብት ጥያቄ የለኝም። ቅዱስ ሲኖዶስ የታዛዦች የአገልጋዮች ጉባኤ እንጂ የባላ ሥልጣናት ምክር ቤት አይደለምና።
እኔ ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የአካባቢ፣ የጎሳ፣ የቋንቋ፣ ... የመሳሰሉት የውክልና ጥያቄም የለኝም። የሰማያውያን የመላእክት ወንድሞች የሆኑ ይህን ዐለም የካዱ አባቶች ጉባኤ ነውና። ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የእገሌ ይሾም የእገሌ አይሾም ጥያቄም የለኝም። ጥያቂዬ የሕግ እና የሥርዓት እንጂ የመብት እና የፖለቲካ አይደለምና።

ቅዱስ ሲኖዶስ አማኞች እንደ ፓርቲ ያቋቋሙት በፈለጉ ጊዜ ሕጉን ቀይረው ዘመን የወለደውን ንጉሥ የወደደውን አስመስለው የሚሠሩት ተራ ተቋም እንዳልሆነ ስማር ኖሪያለሁ፣ በዐለም ባሉት ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉም እንዲህ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ አያለሁምና ምንም ዐይነት የመብት ጥያቄ የለኝም። የመብት ጥያቄ ያለው ክርስቲያን ሆኖ ሊኖር የሚችልም የለምና።

የእኔ ጥያቄ መዳኑ በቤተ ክርስቲያን ሊፈጸምለት እንደሚሻ አንድ ኃጢአተኛ እና ደካማ ሲኖዶሴ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኔም ቤተ ክርስቲያን ሆና ማየት ብቻ ነው። ቤተ ክርስቲያንን መገለጫዋን ቅዱስ ሲኖዶስን በሌላው እንዳደረጉት ኢትዮጵያን ይምሰል በሚል ሽፋን ምክር ቤት ይምስል፣ የጎሳ ውክልና ምጥጥን ስሌት ይጠቀም የሚሉትን የምቃወመው ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን የልጅነት ድምፄን፣ ክርስቲያናዊ ግዴታዬን ለመወጣት ብቻ ነው።

መብት በሚል አደገኛ የፖለቲካ ቃል በር አስከፍቶ ሲኖዶስን የጎሳ ምክር ቤት፣ ቤተ ክርስቲያንም የድኅነት ቤት የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ሐመረ ኖኅ መሆኗን አስጥሎ ጥቅመ ሰናዖር፣ ሐይመተ ፈርዖን ሆና እንድትቆጠር እና ራሷ ከሆነው ከጌታ ከክርስቶስ ከብልቶቿ ከንጹሐን ምእመናን ለመለየት የሚደረገውን ጥረት የምቃወመው ሊቀርብ የሚገባው ጥያቄ የሕግ እና የሥርዓት እንጂ የመብት እና የፖለቲካ አይደለም ብዬ ስለማምን ነው።

ባለፈው ጊዜ በሻሸመኔ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የታሠሩ የተገርፉ እና አሁንም የሚታሠሩ፣ ቤተ ክርስቲያናቸው እስካሁን የተዘጋባቸው፣ በአዲስ አበባ እንኳ ከሥራቸው ተፈናቅለው በደስታ የተቀበሉት ጥያቄያቸው የድኅነት የሕግ የሥርዓት ይከበር ጥያቄ ስለሆነ እንጂ የመብትማ ቢሆን እንዲህ አይሆንም ነበር። እነዚህ ሁሉ ጥያቄያቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን ከወንበዴዎች፣ በጎቹንም ከተኩላ ጠብቃችሁ አድኑን የሚል ትሑት እና የመጨረሻ አነሥተኛ ጥያቄ ነው። የእኔም ጥያቄ ድኅነት ፈለገው የመጡ ምእመናን የጌታን ደም በቁርባን ሰጥተው በማዳን ፈንታ የምእመናን ደም ላፈሰሱ፣ በልተው ላልጠገቡ ለተራቡ ተኩላዎች ሰጥታችሁ አታስበሉን፣ ይልቁንም ድኅነታቸውን ሽተው ለሚያድኑን እረኞች አብቁን የሚል ብቻ ነው።

ይህ ካልሆነ ሲኖዶሱ ሲኖዶስ አይደለም ያሰኝና ብዙዎችን ሊያስወጣ፣ ምእመናን ሊከፋፍል፣ ... ሌላም ሌላም ችግር ሊያስከትል ስለሚችል የእነዚያ ሰዎች የድኅነት ጥያቄ የእኔም ልባዊ ጥያቄ ነው።

አባቶቼ የምታመልኩት የምታገለግሉት፣ እኔም ኃጢአተኛው እና ደካማው የማመልከው ላገለግለውም የምመኘው ሕያው እግዚአብሔር በሚያውቀው ጥያቄዬ አንድ እና አንድ ብቻ ነው።

ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትም ሆነ ማንኛውም ነገር በሕግ እና በሥርዓት ፣ ቀኖናውን መሠረት ባደረገ ለማንም በማያዘነብል፣ ለምእመናን ድኅነት እና ለቤተ ክርስቲያን እድገት እንጂ ለፓርቲዎችና እና ለፖለቲከኞች መሣሪያ ባልሆነ ግልጽ እና ሁሉም ሊያውቀው በሚችል በሲኖዶስ በጸደቀ የምርጫ መመሪያ እና ባለማድላት በተመሰከረላቸው አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሲፈጸም ሕግ ሥርዓት ሲተገበር የማየት የልጅነት ጥያቄ ብቻ ነው።

በእኛ ዘመን ለምን ሕግ ይወጣል? ቀኖናስ ለምን ይጠበቃል የሚል ድምጽ ለሚሰሙት እንዴት ይረብሻል በእውነት። ይህ ድምፅ ይሰማል የሚል እምነት ባይኖረኝም መረበሹን አለመናገር ግን ድምፃቸውን እንደ አማራጭ ማስቆጠር መስሎ ስለተሰማኝ ከፊል የተስማማሁ ስለመሰለኝ ነው ያነሣሁት እንጂ ይደረጋል ብዬ አላስብም።

ጥያቄዬ ቅዱስ ሲኖዶስ በዓላማው በክብሩ ጸንቶ እንዲኖር ቅዱስ ጳውሎስ የሚያውኳችሁ ይቆረጡ እንዳለው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመጣል እና ቤተ ክርስቲያንን ለማወክ ያሰፈሰፉ ሁሉ በሕግ ተቆርጠው እንዲወድቁ ብቻ ነው።

ጥያቄዬ ቤተ ክርስቲያንን ተሳታፊዎች የሚዘውሯት ተራ ምድራዊ ተቋም ሳትሆን ሰማያዊ መልኳን ይዛ እንድትጸና ሕግ ሥርዓቷ ይከበር የሚል ብቻ ነው።

ጥያቄዬ አሳሳቾች በሚፈጽሙት ችግር ምእመናን እንዳይረበሹ ለድኅነታቸውም መሰናክል እንዳይበዛ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይከበር የሚል የልጅነት ጥያቄ ብቻ ነው።

ይህን መጥየቅ ካልቻልኩማ ምኑን ልጇ ሆንኩት፣ ስማረው የኖሩክትስ ምን ይጠቅመኛል። ለድኅነት ካልሆነስ ምን ይረዳኛል። ቤተ ክርስቲያኔ ቤተ ክርስቲያን ካልሆነችስ ምን ይጠቅመኛል። ፓርቲማ መች ቸገረኝ፣ ሕግ ጥሰት እና ድፈረትማ በዓለም ሁሉ ሞልቶ የለ። ከዚህ ሁሉ የጥፋት ባሕር ቀዝፋ የምታሽግር መርከቤን ሽንቁረው ውኃውን አስገብትው አብረን እናስጥምህ ሲሉኝ ዝም ካልኩኝማ ምኑን ሰው ሆንኩ? የተርሴስ ተጓዦች የተጨነቁትን ያህል ካልተጨነቅሁ ምን እጠቅማለሁ? እነሱ እንዳደረጉት ለመርከቢቱ የከበደውን ነገር ባላውቀው እንኳ ሸክም ካልቀነስኩ ምን ረባሁ? የተኛውን ካልቀሰቀስኩ ወደ አምላክህ ጩህ ካላልኩ ከእነዚያ ተጓዦች የማንስ እጅግ ምስኪን አልሆንምን? ስለዚህ የእኔ ጥያቄ የድኅነት እንጂ የመብት ጥያቄ አይደለም። የመብት ጠያቂዎችንም መስማት አልፈልግም። እርሱ ለፖለቲካ ፣ ለድርጅት፣ ለዚህ ዓለም ሰው ሰራሽ ተቋም እንጂ እግዚአብሔር ለመሠረታት፣ ፍጽምት እና አለነውር እንድትሆን ላደረጋት ቤተ ክርስቲያን የመብት ጥያቄ የለኝም፣ ሊኖረኝም አይችልም። የእኔ ጥያቄ እንተ ላዕኩሉን እንተ ታሕተ ኩሉ ሊያደርጉ የመጡትን በሕግ በሥርዓት ቆርጣችሁ፣ መርከባችን ከሚያናውጥ ማዕበል ቀዝፋችሁ አድኑን የሚል የድኅነት የሕግ የሥርዓት ጥያቄ ብቻ ነው።

በዚህ የምትቀየሙ ሁሉ፣ ሳላውቅ የበደልኳቸሁ ካላችሁም ይቅር በሉኝ፣ እንድትድን ለምን ትጠይቃለህ ግን አትበሉኝ። እንድድን በወልደ እግዚአብሔር ሞት ተጠርቻለሁና።

23/02/2024

"ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ፤ ጻድቁን አገልግዬ እዚሁ አርፋለሁ ሲሉ ደመ ከልብ ሆነው ዐፈራቸውንም ሳይቀምሱ ቀርተዋል"
ከዝቋላ ገዳም አበው

"አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” እንዳይሉ፥
የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል፡
በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ"

መዝ 79፥10

22/02/2024

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
From the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Current message forwarded. It is known that among the ancient monasteries under the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, which is ancient, historical, national and international, Zqala Debre Kozor Abune Gebre Spirit Holy Monastery is one of the most important. This ancient and historical monastery is a monastery where many relics and relics are found, and it is remembered that it has suffered serious damage due to looting and burning. According to the information received from the diocese today:
1. Abatekelmariam Asrat, the pastor of the monastery
2. Secretary of the monastery Father Kidane Maryamshadow
3. Abba G/Maryam Abebe, the monastery's book teacher and abbot
4. Manani Hailemariam Woldesenbat who lives on probation On February 12th, after being taken by an armed group called "ONG Shene", all four of them were killed by a rock yesterday, and the father, Abba Kidanemariam G/Senbat, is known to be injured in the monastery. Currently, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church has also sent a message to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church to rescue the monks and the monastery so that the militants do not have a way to enter the monastery and the Mananyan and the heritage of the monastery are in danger.She conveys.
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Office of the Patriarch General
February 14, 2016
Addis Ababa -
Ethiopia

05/01/2024
05/01/2024

ለምን መወለድን መረጠ?
እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረ በኋላ ሕግና ሥርዓት ሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ፍጥረታት ሦስት ዓይነት ሕግጋት ሰጥጧል፡፡

በልቦና ብቻ የሚታሰብ ፣ በሕሊና ብቻ የሚሳል ሕግ የሰጣቸው ፍጥረታት አሉ፡፡

የልቦና ሕግ የሰጠው ለሰው ነው፡፡ ስለዚህም ሕጉ ሕገ ልቦና ይባላል፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረ በኋላ በተፈጥሮ ሕግ ብቻ እንዲኖር አላደረገውም፡፡ በልቦናው የሚሳል ሕግ ሰጥቶታል፡፡ ይሄ ሕግ አዳም ፍጡር መሆኑን እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑን እንዲለይ የሚያደርግ ሕግ ነው፡፡ ምክንያቱም የሕግ አንድ ጥቅም የአንዱን ሕግ የተሰጠውን አካል ደረጃና ወሰን ማመልከት ስለሆነ፡፡

እግዚአብሔር ይሄን ሕግ የሰጠበት ዋናው ምክንያት አዳምን ሲፈጥረው በአርአያውና በአምሳሉ ስለሆነ ለአዳም ፈጣሪነትንም ጭምር ገንዘቡ እንዲያደርግ ስለሰጠው ይሄን እግዚአብሔር የሰጠውን ስጦታ አሳስቶ አኔ ፈጣሪ ነኝ ወደሚል ክህደት ውስጥ እንዳይገባ ፍጡርነቱንም የሚያስታውስ ሕግ ሰጥቶታል ፡፡ ፈጣሪነቱንም ሰው እንዲሰራ ፣ እንዲያስብ ወደ ኋላ ወደ ፊትም እንዲመረምር የሚያደርግ ጸጋ ነው የሰጠዉ፡፡ ይህን ጸጋ ሲጠቀም ግን ሌላ ፈተና ደግሞ ይመጣበታል፡፡

እግዚአብሔር ለቅዱሳን ጸጋ ሲሰጣቸው በተሰጠው ጸጋ ምክንያት ፈተና እንዳይመጣባቸው ከፈተና መከላከያውንም አብሮ ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ የይስሐቅ ልጅ ቅዱስ ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ሌሊቱን ሲታገል አድሮ አግዚአብሔርን አሸነፈ ተብሎለታል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ እግዚአብሔርን እኮ ታግዬ አሸንፊያለሁ ድል አድራጊ ነኝ በሚል የትዕቢት ፈተና እንዳይወድቅ ሌሊት ሲታገል ያደረው ሹልዳውን መታው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያዕቆብ እያነከሰ ይሄድ ነበር፡፡ /ዘፍ 32፡24-32/

ቅዱስ ጳውሎም እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጥቆ ሰው ሊያየው የማይችለውን አይቶ ሰው ሊሰማው የማይችለውን ሰምቶ ሲመለስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ ለሥጋዬ መውጊያ የሚሆነኝ ጎን ጎኔን የሚጎስመኝ ሰይጣን ተሰጠኝ፡፡ ጌታንም ሦስት ጊዜ እባክህ ይሄንን ጎን ጎኔን የሚወጋኝን ሰይጣን አርቅልኝ ብዬ ለመንኩት፡፡ እሱ ግን የሰጠውኽ ጸጋ ይበቃሃል ተወው አለኝ ይላል፡፡ እግዚአብሔር በቅዱስ ጳውሎስ ላይ ጨክኖበት ሳይሆን በመገለጥ ታላቅነት እኔኮ ከሁሉም ተነጥዬ እስከ ሰማየ ሰማያት ሄጄ የመላእክትን ዝማሬና አኗኗር ያየሁ ታላቅ ሐዋርያ ነኝ ብሎ እንዳይታበይ ከዚህ የትዕቢት መንፈስ መጠበቂያ ነው የሰጠው፡፡

እግዚአብሔር ሁልጊዜም ቢሆን ጸጋ ሲሰጥ እንዲሁ አይተወውም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ ምክንያት መውደቅም ስለሚኖር ማለት ነው፡፡ ጥሩ የማስተማር ጸጋ ፣ የቅዳሴ ተሰጥኦ ፣ የመጽሐፍ ጸጋ ፣ ገንዘብ የመሰጠት ጸጋ ፣ የማስተባበር ወዘተ የተሰጣቸው ሰዎች ይሄን ዓይነት ከፈተና የመጠበቂያ ካልተሰጣቸው በትዕቢታቸው ይወድቃሉ፡፡ የመላእክት አለቃ የነበረው ሳጥናኤልም እንዲሁ ነው የወደቀው፡፡ የሁሉም አለቃ የመሆን ጸጋ ሲሰጠው መጠበቂያ አልተሰጠውም ነበርና ከሦስቱ ሥላሴ አራተኛ እሆናለሁ ብሎ በትዕቢት ወድቋል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ ወድቀዋል፡፡

ሕግ ተሰጥቶት እንኳን ሰው ሕግን ባለማክበሩ ምክንያት ወድቋል ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ለአዳም ይሄን ታላቅ ጸጋ ሲሰጠው በጸጋው ምክንያት ሌላ ፈተና መጥቶበት ከጸጋ እንዳይወድቅ መጠበቂያ ደግሞ ሰጠው፡፡ ሁሉን ግዛ ፣ ንዳ ተብለህ ቢሰጥህም አንተ ፈጣሪ አይደለህም፡፡ የሁሉም የበላይ ንጉሥ ብትሆንም በባሕሪህ ግን ንጉሥ አይደለህም፡፡ የሁሉም አለቃ ሆነህ ሁሉ ቢታዘዝልህም በባህሪይ ገዢ አይደለህም ሲል የማይነካት ሕግ ተሰጠችው፡፡

ይሄን አትብላ ይሄን ደግሞ ብላ ብሎ እግዚአብሔር ሲሰጥ ሳስቶ አይደለም፡፡ አዳም ቢበላ ከእግዚአብሔር የሚጎድልበት ነገር የለም፡፡ አዳም ባይበላ የሚቀርበት ነገር የለም ፡፡ ግን መለያ ያስፈልጋል፡፡ በቤተክርስቲያናቸንም ሰባቱ የክህነት ማዕረጋት መለያ አለ፡፡ ዲያቆን የማያደርገው ካህኑ የሚያደርገው አለ ፤ ካህኑ የማያደርገው ጳጳሱ የሚያደርገው አለ ፤ ጳጳሱ ደግሞ ብቻውን የማያደርገው ከሁለት በላይ አባቶችን ይዞ የሚያደርገውና የሚፈጽመው ሕግ አለ፡፡

ይሄ ከፈተና ሰዎችን ለመከላከል እንጂ የእግዚአብሔርን ጸጋ ለመቀነስ የተደረገ አይደለም፡፡ ምዕመናን የማያደርጉት ካህናት የሚያደርጉት ፣ ሴቶች የማይፈጽሙት ወንዶች የሚፈጽሙት ፣ ሕጻናት የማያደርጉት አዋቂዎች የሚፈጽሙት አለ፡፡ ይሄ እግዚአብሔር በፈጠራቸው ፍጥረታት በተለይ በሰውና በመላእክት ዘንድ ያለ ነው፡፡ ለአዳም እንዲህ ያለ ሕግ ነው የተሰጠው ፡፡

ደመ ነፍሳዊ የሆነ ሕግ የተሰጣቸው ፍጥረታት አሉ፡፡

ለእንስሳት ፣ ለአራዊት ፣ ለእጽዋት ፣ በዚህ ምድር ላይ ላሉ ሁሉ የተሰጣቸው ሕግ ነው፡፡ አውቀው ፣ አስበው ፣ ተምረው የሚፈጽሙት ሳይሆን በተፈጥሮ እግዚአብሔር ባስቀመጠላቸው ሥርዓት ምክንያት የሚኖሩበት ነው፡፡ ለእንስሳት መውለድ መዋለድ ፣ ለእጽዋት ዘራቸው መብቀል ፣ ግንዳቸው ተቆርጦ መብቀል ፣ ለውኃዎች መፍሰስ ፣ የፀሐይና የምድር መስተጋብራዊ ሥርዓት በእያንዳንዳችን ሰውነት ውስጥ ያለው የተፈጥሮ ሥርዓት ለመተንፈስ ፣ ለማዳመጥ ፣ ለመናገር ፣ የደም ዝውውር የተሰጠው ሥርዓት በሙሉ እግዚአብሔር በተፈጥሮ ለፈጠራቸው ፍጡራን የሰጠዉ ነው፡፡
ፍጡር ከዚህ ማመጽ አይችሉም፡፡ ካልሆነ ህልውናው ያከትማል፡፡ ይሄኛው ሕግ ጽድቅና ኀጢአት የሚገኝበት አይደለም፡፡ አንድ ሰው በተፈጥሮ ምክንያት ቢበላ ፣ ቢጠጣ ፣ ደሙ ባይዘዋወር ፣ ባይተነፍስ ፣ ባይናገር ፣ ባይሰማ ፣ አልተናገርክም ፣ አልሰማህም ተብሎ የሚመጣበት እዳም የለም፡፡ በራሱ ላይ የሚያስከትለው አደጋ ከሌላ በስተቀር፡፡
የአነዋወር ሕግ የሰጣቸው ፍትረታት ደግሞ አሉ፡፡
ይህ ሕግ ለመላእክት የተሰጠ ሕግ ነው፡፡ መላእክት ይሄን ብሉ ይሄን አትብሉ ተብሎ የተሰጣቸው ሕግ የለም ፡፡ በኋላም በሕገ ልቦናም ፣ በሕገ ኦሪትም ፣ በሕገ ሐዲስም ለመላእክት የተሰጠ አዲስ ሕግ የለም፡፡ እነርሱ በአነዋወር የተሰጣቸው ሕግ አለ፡፡ ያ ሕግ አምልኮተ እግዚአብሔርን ይዘው ሲያመሰግኑና ሲያገለግሉ የመኖር ሕግ ነው፡፡ ከዚህ ከተሰጣቸው ሲያፈነግጡ እንደ ዲያቢሎስ ይቀጣሉ፡፡

ሐዋርያው ይሁዳ በመልዕክቱ በቁጥር 6 ላይ “ መኖሪያቸውንም የተውትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆዋቸዋል” በማለት ተናግሯል፡፡ አለቅነታቸውን ያልጠበቁ ማለት ክብራቸውን ያልጠበቁ ማለት ነው፡፡ መላእክ ማለት በአንድ በኩል አለቃ ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ መልዕክተኛ ማለት ነው፡፡ እነሱ አለቆች ሆነው ከብረው ስሙን ቀድሰው ክብሩን ወርሰው መኖር ነው አለቃ ያሰኛቸው፡፡ ይሄን አንጠብቅም ፣ አናመሰግንም ያሉትን መላእክት እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በጨለማ እስር ቤት ዘግቶባቸዋል ብሏል፡፡ በአነዋወር ሕግ ጽድቅና ኃጢአት አለ፡፡ የአነዋወር ሕግ ያልጠበቁ መላእክት ተቀጥተዋል፡፡ ያነዋወር ሕጋቸውን የጠበቁት መላእክት ደግሞ ከብረው ኖረዋል፡፡

እነዚህን ሕግጋት እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ለ22 ቱ ፍጥረታት ሰጥቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል ሁለቱ ፍጡራን ወድቀው ተገኝተዋል፡፡ አንዱ ሰው ነው፡፡ ሰው የተሰጠውን ሕግ እንቢ ብሎ ከገነት ተባሯል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ከመላእክት መካከል በሳጥናኤል የሚመሩት ርኩሳን መላእክት የምንላቸው ወድቀዋል፡፡

አንዳንድ ሰው የሚጠይቀው ጥያቄ አለ፡፡ ዲያቢሎስ በበደለው መላእክት ሁሉ አልተቀጡም፡፡፡ አዳም በበደለው ግን የሰው ዘር ሁሉ ተቀጥቷል ፡፡ እግዚአብሔር በእውነት ፍትሐዊ ከሆነ አንድ አዳም በበደለው በደል ሁሉን እንደቀጣ ለምን አንድ ዲያቢሎስ በበደለው መላእክት ሁሉ አልጠቀጡም የሚል አለ፡፡

የመላእክትና የሰው አፈጣጠሩ ልዩ ስለሆነ ነው፡፡ መላእክት ሁሉንም ነገድ በአንድ ቀን በአንድ ቅጽበት ነው የተፈጠሩት፡፡ ሰው ግን መጀመሪያ አዳም ከምድር ቀጥሎ ሄዋን ከአዳም ጎን ፣ ከዛ ደግሞ አቤልና ቃየል ከአዳምና ከሄዋን እያለ ስለሆነ ሁላችንም በአዳም አብራክ ውስጥ ነበርን ፤ ሁላችንም በሔዋን መኀጸን ውስጥ ነበርን፡፡ ስለዚህ አዳም እኛን ይወክላል፡፡ በአዳም ኀጢአት ምክኒያት በዘሩ የመጣን ሁሉ እስከ ክርስቶስ መወለድ ያሉት ተቀጥተዋል፡፡
መላእክት ግን አንዳቸው ከአንዳቸው ስለማይወለዱ በዘመንም ስለማይቀዳደሙ በወሰኑት ውሳኔ ነው የተቀጡት፡፡ ያን ጊዜ በመላእክት ዓለም ድብልቅልቅ ሲፈጠር እግዚአብሔርን አምልከው አለቅነታቸውን ጠብቀው የተገኙት ቅዱሳን መላእክት ባሉበት ጸንተዋል፡፡ አለቅነታቸውን ያልጠበቁት መላእክት ደግሞ ተዋርደው ቀርተዋል፡፡ ዘር ስለሌላቸው ጽድቁም ኀጢአቱም በዘር ሊተላለፍ አይችልም፡፡ ሰው ግን በዘር ስለሆነ የሚዋለደው ከልጅ ልጅ በረከቱም ይተላለፋል ፣ ኀጢአቱም እንዲተላለፍ ሆኖ ነበር፡፡

ሁለቱ ባጠፉት ጥፋት ተቀጥተውበታል፡፡ እንስሳትና ሌሎች ግን ውኆች ፣ ፀሐይ ፣ ጨረቃ ፣ ከዋክብት ፣ ምድር ላይ የተፈጠሩት ፍጥረታት በሙሉ ግን የተሰጣቸው የተፈጥሮ ሕግ ስለሆነ አይቀጡበትምም አይሸለሙበትምም፡፡ አንድ እንስሳ ጥሩ ሠራ ተብሎ አይሸለምም ፣ ኀጢአት ሠራህም ተብሎ አይወቀስም፡፡ እጽዋትም በጎ ነገር ሆኑ ፣ ተቆርጠው ለቤተክርስቲያን ሥራ መስሪያ ፣ ለታቦት መቅረጫ ዋለ ተብሎ አይጸደቅበትም፡፡ ቤት ተሰርቶባቸው ኀጢአት ሲሰራባቸው ቢውል ቢያድር አይቀጡበትም፡፡ የአነዋወር ሕግና የልቦና ሕግ ተሰጣቸው ፍጡራን ግን ተመስግነውበታልም ተቀጥተውባታልም፡፡ ሰው እንግዲህ ከእነዚህ አንዱ ነው፡፡

አዳም ይሄን ሕግ ጥሶ ከገነት ወጣ፡፡ ሲወጣ አልቅሶ ፣ ተጸጽቶ ፣ ንስሐ ገብቶ የፈጣሪውን ምህረት በማግኘቱ ምክንያት ጌታችን መድኀኒታችን ኢሱስ ክርስቶስ ከአምስት ቀን ተኩል (5500 ዘመን) በኋላ እንደገና አዳምን በሐዲስ ተፈጥሮ በሥጋ ተፈጥሮ ለመፍጠር ፣ ከወደቀበት ለማንሳት በዱካው ተከትሎ ሰውን ለማዳን ተወለደ፡፡

ለምን መወለድን መረጠ? እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ከመወለድ የተሻለ ነገር ስለማያውቅ ነውን? ስለሌለውስ ነውን? ስለማይችልስ ነውን?

ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር የሰራቸውና የፈጸማቸው ነገሮች በሙሉ ሰውን ከመውደድና ከማፍቀር የተነሳ ፍቅሩን እንዲረዳው ከማድረግ የመነጩ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ያደረገለትን ነገር ከከሃሊነቱ በላይ አፍቃሪነቱን ፣ ከፈጣሪነቱ በላይ አባትነቱን ፣ ሁሉን ቻይ መሆኑን ከማሳየት በላይ ሁሉን ታጋሽ መሆኑን ፣ ባለስልጣን መሆኑን ከማሳየት በላይ ባለ ፍቅር ፣ ባለ ቸርነት ፣ ባለ ይቅርታ መሆኑን ማሳየቱ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

እግዚአብሔር አዳም ንስሐ እንደገባ ና ከሲኦል ውጣና ገነት ግባ ማለት ይቻለው ነበር፡፡ ወይም ከመላእክት አንዱን ልኮ ሂድ ቅዱስ ሚካኤል ፣ ሂድ ቅዱስ ገብርኤል አዳምን ከሲኦል አውጥተህ ገነት አስገባው ማለትም ይቻለው ነበር፡፡ ወይም እንዲሁ ገቢር ሳያስፈልገው በሃሳብ ብቻ ( የዕለተ እሁድን ፍጥረታት በሃሳብ ብቻ እንደፈጠረው ) አዳምን ከሲኦል አውጥቶ ገነት ማስገባት ይቻለው ነበር፡፡ ይሄን ቢያደርግ ግን ሁለት ነገሮችን ማከናወን አይቻልም ነበር፡፡

ሰው ለመረዳት ይከብደዋል፡፡

የሰው ተፈጥሮ አንድን ነገር በሂደት የሚረዳ ነው፡፡ አንድ ልጅ በመጀመሪያ እናቱ ነፍሰ ጡር መሆኗን ፣ ከዛ መውለዷን ፣ ማደጉን ፣ ከዛም መጎልመሱን አይተን አገባ ብንባል እንረዳዋለን፡፡ ድንገት ግን አንድ ልጅ በድንገት ማን እንደወለደውም ፣ ከየት እንደተወለደም ፣ መወለዱን የማናውቀው ሰው አገባ ብንባል ግራ ይገባናል፡፡ ለሰው ይሄ ከባድ ነው፡፡
አንድን ነገር ሰው የሚረዳው በሂደት ነው፡፡ ሲዘራ ፣ ሲበቅል ፣ ሲታረም ፣ ሲደርቅ ፣ ሲታጨድ ፣ ሲወቃ ካለየ በስተቀር አእምሮ እሱን ለመረዳት አይችልም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ያደረገውን ነገር በድንገትና በስልጣን ቢያደርገው አንረዳውም፣ አያገባንም፡፡

በደብረ ታቦር የተፈጸመውን ብናስበው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ሂዶ ብርሃነ መለኮቱን በገለጸ ጊዜ ድንገት እንደ መብረቅ ሆነ፡፡ ፊቱም ተለወጠባቸው፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ እንኳን ያንን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ለመረዳት ገና የብቃቱ ደረጃ ስላልደረሰ አቤቱ ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ቤት እንስራ ፤ አንድ ለኤልያስ ፣ አንድ ለአንተ ፣ አንድ ለሙሴ ፣ ኤልያስ ሰማይ እየለጎመ ፣ ሙሴም መና እያወረደ ፣ ባህር እየከፈለ ፤ አንተም ድውይ እየፈወስክ ፣ የቸርነት ሥራ እየሰራህ እዚህ እንሁን፡፡ በአይናቸው እንቅልፍ ከበደባቸው ይላል ፡፡ ይሄ እንቅልፍ ከድካም ወይም ከስንፍና የመጣ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ አቅም እንዲህ አይነቱን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በአንድ ጊዜ የሚገለጥ ለመረዳት አቅም ስለሌለው ነው፡፡

አቡቀለምሲስ ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩው መግቢያ ላይ ሰማያት ተከፍተው ባየ ጊዜ ወደኩ ነው የሚለው፡፡ ለምን ቢባል የሰው ልጅ ሥጋዊ ደማዊ አቅም እንደዚህ አይነት መሸከም የሚችል አቅም የለውም፡፡ ነቢዩ ዳንኤልም ቅዱስ ገብርኤል ዳሶ እስከሚያነሳው ድረስ የሰማያት ምስጢር ሲገለጡለት ወደኩ ነው የሚለው፡፡ ይሄ ሁሉ የሰውን አቅም ነው እንጂ የሚያሳየው የእነዚህን የቅዱሳን የብቃት ደረጃ አይደለም፡፡

ሰው የፈለገውን ያህል በጸጋ ቢበቃ ፣ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር እንኳ ቢያደርግለት ሥጋዊ ደማዊ ድካም ሁልጊዜም አለ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በድንገት ቢያደርገው ኖሮ ሰው መረዳት አይችልም፡፡ ይሄን መረዳት ከሰው አቅም በላይ ነው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱሳን መላእክት በገድለ ቅዱሳን ውስጥ ለታላላቅ አባቶቻችን እንኳን ሲገለጥላቸው በሽማግሌ አምሳል ፣ በመልእክተኛ አምሳል ፣ በአሽከር አምሳል የሚገለጡት፡፡

እግዚአብሔርም ለእነዚህ ቅዱሳን ሲገለጥ በተለያየ አምሳል ነው፡፡ ነቢዩ ዳንኤል እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ሲያየው በዘመናት የሸመገለው ይለዋል፡፡ በእስራኤል ልማድ ሽማግሌ ክቡር ስለሆነ በዚያ በልማዱ አየው እንጂ እንዴትም ለመረዳት ይቸግረው ነበር፡፡ አቡቀለምሲስ ቅዱስ ዮሐንስም በዙፋኑ ላይ በተቀመጠ ጎልማሳ አምሳል አየው እንጂ እንዴት ይረዳው ነበር? ነቢየ ልዑል ኢሳይያስም ኦዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት ብሎ በንጉስ አምሳል ባያየው ኖሮ እንዴት ይረዳው ነበር?

እግዚአብሔር ሰውን ማፍቀሩን ፣ ለሰው ቸር መሆኑን ለመግለጽ ሰው በሚረዳው ፣ በሚገባውና ሰው በሚወደውና በሚቀለው መንገድ ነው የመጣው፡፡ ሥጋወና ደሙን እንኳን ሲሰጠን ለሰው ከምግብና ከመጠጥ ያነሰ ፣ ከእንስሳት ጋር እኩል የሚሆንበት በጣም ቀላሉን መርጦ ነው የሰጠን፡፡ ጾም ፣ ስግደት ፣ ቁመት ከባድ ነው፡፡ ሥጋውና ደሙን በእነዚህ ሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ማንም አይቆርብም ነበር፡፡ ስለዚህ ለሰው እጅግ ቀላል በሆነው በህብስትና በወይን ነው የሰጠው፡፡

የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ የሆነችውን ንስሐን እንኳን ሲሰጠን ሰው መናገር ፣ ከጓደኛና ከቤተሰብ ጋር ማውራት ቀላል ስለሆነ ሂዱ ከንስሐ አባታችሁ ጋራ ተነጋገሩ ብሎ እንዲህ በቀላል ነገር ነው የሰጠን፡፡ በአርባና በሰማንያ ቀናችን የእግዚአብሔር የልጅነትን ጸጋ የምናገኝበትን ጥምቀት ሲሰጠን ለሰው የመጨረሻ ቀላሉ ውኃ ስለሆነ ጠጅ ፣ ወይን ወይንም ሌላ ውድ ነገር አላደረገውም፡፡ እግዚአብሀየር ለሰው እንዲህ ነው የሚያደርገው፡፡

የእግዚአብሔር ዓላማ ለሰው ያለውን ፍቅሩን መግለጥ ነው፡፡
ፍቅር ሦስት ነገሮችን ይይዛል፡፡
1ኛ. በፍቅር ውስጥ ትህትና አለበት፡፡ ፍቅር ትሁት የሆነ ስብዕና ይፈልጋል፡፡
2ኛ. ፍቅር መገለጥ አለበት፡፡
ፈቅር የሚታሰብ ሳይሆን የሚገለጥ ነው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ (1ቆሮ 13) የፍቅር መግለጫውን ነግሮናል፡፡ እንደ አለማዊያን ሊቃውንት ፍቅር የቃላት ርቀት አይደለም የሚያሳየው፡፡ ስለዚህ የፍቅር ትልቅነቱ መገለጥ መቻሉ ነው፡፡
3ኛ. ፍቅር አቅምን ይመጥናል፡፡ እንዲት እናት ለልጇ ልዩ ፍቅር ስለሚኖራት ከልጇ ጋራ ስትነጋገር፣ ስታወራ እሷ በምትችለው ቋንቋ ሳይሆን ልጇ በሚረዳው ቋንቋ ነው፡፡ አንድ መምህር ለተማሪዎቹ ፍቅር ካለው ተማሪዎቹን የሚያስረዳቸው ተማሪዎቹ በሚገባቸው አቅም ነው፡፡ መጫወት ካለበት አብሮ እየተጫወተ፣ አቧራ መንካት ካለበት አብሮ እየነካ፣ ዝቅ ብሎ መዋረድ ካለበት አብሯቸው ተዋርዶ ነው፡፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የተገለጠው በእነዚህ በሦስቱ ነው፡፡
ፍቅር ትህትና አለውና ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ምድር ላይ መምጣት ይበቃው ነበር፡፡ በመካከላችን መወለዱ ይበቃው ነበር፡፡ ሲወለድ ግን ያደረገው ከዚህ እንኳን የባሰ ነው፡፡ ከቤተ መንግስት ወደ ቤት ከመጣ ከሰማይ ወደ ምድር ከወረደ ይበቃው ነበር፡፡ እሱ ግን ከዚያ ሁሉ መርጦ በረት ተወለደ፡፡

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እመቤታችንን “ወለተ ነዳያን” ይላታል፡፡የድኆች ልጅ ናት፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሷ ስለተወለደ እግዚአብሔርም እጅግ ከፍ ስላደረጋት ዛሬ እናመሰግናታለን እንጂ የናዝሬት ሰዎችኮ እመቤታችንን አያውቋትም፡፡ ለዚህ ነው ናትናኤል ለፊሊጶስ ለመሆኑ ከናዝሬት ደግ ነገር ይወጣልን? ያለው (ዮሐ 1) ፡፡ ናዝሬት የድኆች ከተማ ናት፡፡ አቅም የሌላቸው ፣ ለመንገስ ፣ ለመክበር ፣ ለመሾም የማይታሰቡ እነሱም የማያስቡ ሰዎች ያሉበት የተናቀች ከተማ ናት፡፡ እዚያ ውስጥ ነው እመቤታችን የኖረችው፡፡

ቅዱስ ያሬድ ናዝሬት ከገሊላ በቦታ ታንሳለች በጸጋ ግን እጅግ ትበልጣለች ይላል፡፡ ጌታም የኖረው በዚያ ነው፡፡ የእመቤታችን ጠባቂ ተደርጎ የተመረጠው ቅዱስ ዮሴፍ እንኳን እንጨት የሚሰራ አናጺ ነበር እንጂ በዘመኑ ታላቅ የሚባለውን የክብር ሥራ የሚሰራ አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር የመጨረሻውን ተዋርዶ ነው የመረጠው፡፡ በረት እንኴን ሲወለድ ቅዱስ ያሬድ እንደሚነግረን በለሶን በሚባል ቅጠል ጠቀለለችው ነው የሚለው፡፡ ልብስ አልተገኘለትም፡፡

ለምስጋና የተላኩት እንኳን ዛሬ በዓል ሲከበር የሚወርቡት ሊቃውንት መዘምራን መሪጌቶች አይደሉም፤ እረኞች ናቸው፡፡ ዕለቱን አጥንተው ፣ ዕለቱን ተምረው ፣ ዕለቱን በቤተልሄም ተገኝተው ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት የሚለውን መዝሙር የወረቡት እረኞች ናቸው፡፡ እረኞች ደግሞ በዘመኑ እጅግ የተናቁ ናቸው፡፡ እንዲያጅቡት ፣ እንዲያሞቁት ያደረገው መጋረጃዎቹን ፣ ምንጣፎችን አይደለም፡፡ አህዮችን ፣ ላሞቹን ፣ ጥጆቹን ነው፡፡ የተቀበለው የመጨረሻውን ተዋርዶ ነው፡፡

በረት ሲባል ዛሬ ኢትዮጵያ እንደሚሰራው በእንጨት ዙሪያው ታጥሮ ወይም በቤት ውስጥ ከብቶች እንደምናሳድርበት ዓይነት አይደለም፡፡ የእስራኤል በረት የዋሻ በረት ነው፡፡ ከዋሻ የሚሰራው ነው፡፡ ዋሻውን ፈልፍለው ነው በረት የሚያደርጉት፡፡ የተወለደበት ወቅት ደግሞ የብርድ ወቅት ነው ፡፡ በብርድ ወቅት ዓለት ዋሻ ውስጥ መተኛት ምን ያህል ብርድ እንደሆነ ማሰብ ነው፡፡

በእስራኤል ሀገር ወቅቱ የበረዶ ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህ በጣም በሚቆረጥመውና በሚበርደው ሰዓት ነው ጌታ የተወለደው፡፡ ከወቅቶች እንኳን ምቹውን ወቅት አልመረጠም፡፡ ለምሳሌ ጥሩ ወቅት አለ፡፡ የበጋው ወቅት ቢወለድ እርሱም አይበርደውም ግን የተወለደው ከወቅቶች እንኳን ተመርጦ የሚወድቀው የችግርን ወቅት ነው፡፡ የልደት ወቅት በእስራኤል የችግር ወቅት ነው፡፡ እህሉ የሚደርስበት አይደለም፡፡ ወይኑ የሚወድቅበት ጊዜ ነው፡፡ የቀጠና ወቅት ነው፡፡ እሱ ግን ይሄንን ነው የመረጠው ፡፡ በዚህ ፍቅሩን አሳይቶናል፡፡ ይሄ ትህትናው ነው፡፡

ሁለተኛው የፍቅር መግለጫ ፍቅር መታየት ወይም መገለጥ መቻል አለበት፡፡ እውነተኛ ፍቅር የሚሰማ ፣ የሚዜምለት ሳይሆን የሚታይ ነው፡፡ አንድ ሊቅ አዳም እግዚአብሔርን ምን ያህል ትወደኛለህ? ብሎ ጠየቀው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ አንድያ ልጁን ልኮ እጅና እግሩን በመስቀል ተቸንክሮ ይሄን ያህል ነው የምወድህ አለው ይላሉ፡፡ በቃላት አይደለም የገለጠለት፡፡ በተግባር ነው ፍቅሩን የገለጠለት፡፡ እጁንና እግሩን በመቸንከር ፣ ጎኑን በመወጋት ፣ በመጠማት ፣ በመሰደድ ፣ የእሾህ አክሊል በመቀናጀት ፣ ራቁቱን በመስቀል ፣ የሽፍቶች መቀለጃ በመሆን ፍቅሩን በሚታይ ነገር ነው የገለጠው፡፡

ለምሳሌ በቤተክርስቲያናችን ብዙ ሥዕላት አሉን፡፡ ለምንድን ነው በቤተክርስቲያናችን የምናደርገው? ለማጌጥ እኮ አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያን ጌጧ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው (ራእ 19)፡፡ እንጂ እኛ የምንቀባው ቀለም ፣ የምናላብሳት ቆርቆሮ ወይም ደግሞ በጥሩ ብሎኬት ስለሰራነው ቤተክርስቲያን አታጌጥም፡፡ በሥዕል ለማስጌጥ አይደለም እንደዚህ የምናደርገው፡፡ ሥዕሎቹ ግን ፍቅር የሚገልጡ ናቸው፡፡

በአንድ እግራቸው አባ ተክለሃይማኖት ቆመው ሲጸልዩ ፍቅር ነው የተገለጠው፡፡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቁራ በዓይናቸው ላይ መጥቶ በጽናት ሲጸልዩ ለሰው ልጅ ያለ ፍቅር ነው፡፡ እነ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ባሕር ገብተው ሲጸልዩ ፍቅር ነው እንጂ ለእነሱ ለጽድቅማ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ይበቃቸዋል፡፡ በእነሱ ልቦና የተጸለየ አንድ አቡነ ዘበሰማያት እኛ ዓመት ሙሉ ከምንደግመው ዳዊት ይበልጣል፡፡

የስቅለቱን ሥዕልን ፣ እመቤታችን ልጇን አቅፋ የምናየው ሁሉ የፍቅር መግለጫ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን እንዲህ የወደደው ፤ ሰው ሆኖ እስከ መውረድ ፣ ሰው ሆኖ እስከ መወለድ ፣ በልሳነ ብዕሲ እስከ መናገር ፣ በግዕዘ ሕጻናት እስከ ማደግ ነው የደረሰው ፡፡ የሚታይ ፍቅር ነው፡፡

እኛ ለወላጆቻችን ፣ ለልጆቻችን ፣ ለትዳር አጋሮቻችን ፣ ለሀገራችን ፣ ለቤተክርስቲያናችን ያለን ፍቅር በቃላት የሚገለጥ እንጂ በተግባር የሚታይ አይደለም፡፡ ቅዱሳን ደግሞ ለቤተክርስቲያናቸው ያላቸው ፍቅር የሚታይ ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመንኮራኩር መፈጨት እርሱ ፍቅር ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ስንክሳሩ ፣ ገድላቱ ፣ የሚነበቡት ፍቅሩን እንድናይ ነው፡፡ እግዚአብሔርን እንዲህ ነው የወደዱት የሚል ነው፡፡

በከተማ በቤታቸው በሞቀ ቦታ ሆነው ሲጸልዩ እግዚአብሔር በጎ ነገር ሲሰራላቸው አዩና እኛ በሞቾት ቦታ ሆነን እንዲህ ስንጸልይ ይሄን ካደረገልን ሁሉን ትተን በርሃ ብንገባማ ምን ያደርግልን ይሆን? ብለው ገቡ ነው የሚለው፡፡ ይሄ ፍቅር ነው፡፡ የሚነገርለት ሳይሆን የሚታይ ነው፡፡

ሊቃውንት ይሄን ሁሉ ድርሰት የደረሱት ረዥም ጸሎት አምሯቸው አይደለም፡፡ ይሄን በወንጌል ተምረውታል፡፡ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃውያን ጸሎታቸውን በማስረዘም የሚጸድቁ ይመስላቸዋል ተብሏል፡፡ ጸሎት በማስረዘም የሚጸደቅ ሆኖ አይደለም፡፡ ፍቅሩ አላልቅላቸው ብሎ ነው፡፡ አባ ኤፍሬም የእመቤታችን ፍቅር እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ በበዛልኝ ነበር የሚለው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ታሪክ 14 ሺህ ድርሰት በላይ ነው የደረሰው፡፡ ምግብ ሆኖኝ በተመገብኩት መጠጥ ሆኖኝ በጠጣሁት እያለ ነበር ሲመኝ የነበረው፡፡ ይሄን ሁሉ ሥራ የሰራ ለምንድን ነው ያልጠገበው ቢባል ፍቅር አይጠገብምና ነው፡፡

በጌታችን ልደት ፍቅሩን ነው ያየነው፡፡ በረት ተወለደ ስንል የተወለደበትን ቦታ ሳይሆን ፍቅሩን እየተናገርን ነው፡፡ ልደቱንም የፈጸመው ለሰው በሚረዳው መልኩ ነው፡፡ ሰዎች ነንና ሰው ሆኖ መጣ፡፡ ሕጻን ሆኖ ተወለደ፡፡ በእኛው ቋንቋ ተናገረ፡፡ የምንበላውን በላ ፣ የምንጠጣውን ጠጣ፡፡ ከኀጢአት ብቻ በስተቀር የምንሰራውን ሁሉ ሰራ፡፡

ሙታን ከመሞታቸው በፊት ከሞቱም በኋላ እንኳን ሥጋቸው ነፍሳቸው ያለችበት ቦታ የሚያውቅ ጌታ አልዓዛር የትነው አለ፡፡ እጽዋት ፍሬ እንዲያፈሩ ፣ ወፎችና እንስሳት እንዲመገቡዋቸው ያደረገ ጌታ ተራበ ወደ በለስ በቀረበ ሰዓት በለሷን ፍሬ አጣባት ተብሎ ተነገረ፡፡

ዓለምን በውኀ ያጥለቀለቀ ፣ ሰባቱን ውቂያኖስ የፈጠረ ምድርን በውኀ ላይ የሰራ አምላክ ተጠማሁ አለ ተባለለት፡፡ ምድሪቱን እንኳን በልዩ ልዩ አበባና ቅጠል የሸፈነ ራቁቱን ተወለደ ፣ ራቁቱን ተሰቀለ ተባለ፡፡ ንጹኀ ባህሪ አምላክ ዝቅ ብሎ እግር አጠበ፡፡ ስለዚህም የልደት በዓል ታላቅ በዓል የሚያደርገውም ፍቅር የተገለጠበት በመሆኑ ነው፡፡ በፍቅር ጀመረ በፍቅር ጨረሰው፡፡ በቤተልሄም በመታየት የተጀመረው ፍቅር በቀራንዮ ላይ በአደባባይ ከፍ ብሎ በመስቀል ነው የተጠናቀቀው፡፡ ለዚህ ነው ቀራንዮ ላይ ተፈጸመ ያለው፡፡

ስለዚህ ልደት የፍቅር በዓል ነውና እኛም ልንፋቀርበት የሚገባ በዓል ነው፡፡ ተጣልቶና ተቀያይሞ ልደትን ማክበር አይቻልም፡፡ ከ3ቱ አካላት ጋር ታርቀን ነው ልደትን የመንናከብረው፡፡ ከራሳችን ፣ ከወዳጆቻችን እና ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን መሆን አለበት፡፡ ይሄን ሳያደርግ የሚያከብር ሰው ልደትን እያከበረ አይደለም፡፡ እንዲሁ በበዓሉ ቀን እየተዝናና እየበላ እየጠጣ ሊያከብረው ይችላል፡፡ ይሄ ክብር አይደለም፡፡

አንድን በዓል አከበርን የምንለው ስንከብርበት ነው፡፡ በበዓሉ ሳንከብርበት አከበርን ማለት አንችልም፡፡ በበዓሉ እኛም ጸጋ አግኝተን ካልከበርንበት ግን አላከበርንም፡፡ ሲጨፍሩ ሱጠጡ ፣ ዝሙት ሲሰሩ የሚያድሩ ሰዎች ይሄ ነው ችግራቸው፡፡ አልከበሩበትምና አላከበሩትም፡፡ ጌታ የተወለደበት ምንም እንኳን ብዙ ምክንያት ቢኖርም ዋናው ግን አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ላይ "ፍቅር ኀያል ወልድን ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው” እንዳለው የሳበው፣ ያወረደው ፍቅር ነው፡፡ እኛ ለእርሱ ያለን ፍቅር ሳይሆን እሱ ለእኛ ያለው ፍቅር ማለት ነው፡፡

በዕለተ ልደቱ ምንድን ነው የተፈጸመው? ይሄን ፍቅር የሚገልጹ ምን ነገሮች ሆኑ?

የመጀመሪያው ከድንግል ተወለደ፡፡ ይሄ ልደት ልዩ ልደት ነው፡፡ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖነ ድንግል በተሰኘ ድርሰቱ ላይ አራት ዓይነት ልደት አለ ይላል፡፡
የአዳም ከምድር መወለድ
የሔዋን ከአዳም ጎን መወለድ
የቃየል ከአዳምና ከሔዋን መወለድ ነው
የኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ ነው ይላል፡፡

በሦስቱ ልደቶች አልተጠቀምኩም፡፡ አዳም ከምድር በመወለዱ ፣ ሔዋን ከአዳም ጎን በመወለዷና ቃየል ከአዳምና ከሔዋን በመወለዳቸው ያገኘሁት ጥቅም የለም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በመወለዱ ግን ተጠቀምኩ ጸጋ አገኘሁ ይላል፡፡

ከአራቱ ልደቶች ሦስቱ ያለዘር የተከናወኑ ናቸው፡፡ የአዳም ከምድር መወለድ ፣ የሔዋን ከአዳም ጎን መገኘትና የኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥበብ እንበለ ዘርዓ ብዕሲ ተከናውኗል፡፡ የቃየል ከአዳምና ከሔዋን መወለድ ግን በዘር ተከናውኗል፡፡

ከአራቱ ልደቶች ሦስቱ በሞት ተዘግተዋል፡፡ አዳም ከምድር ተወለደ ሞተ፡፡ ሔዋን ከአዳም ጎን ተወለደች ሞተች፡፡ ቃየል ከአዳምና አሔዋን ተወለደ ሞተ ፡፡ የሦስቱም ታሪካቸው መጨረሻ ሞት ሆኗል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም የተወለደው ግን ሞትን የሚያሸንፍ ብርቱ ኀያል ሆኗል፡፡

ከአራቱ ልደቶች መካከል ሁለቱ እንደ ሰው ጠባይ የተከናወኑ ናቸው፡፡ የቃየል ከአዳምና ከሄዋን መወለድ እናትና አባት ያለው ስለሆነ እንደ ሰው ጠባይ የተከናወነ ነው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ ያለ አባት የተከናወነ ቢሆንም እናት አለውና ሰው ሊረዳው የሚችል ነው፡፡ አዳም ከምድር ተወለደ ፣ ሔዋን ከአዳም ጎን ተወለደች የሚለውን ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ባይወለድ ኖሮ አንረዳውም ነበር፡፡

ከአራቱ ልደቶች ሦስቱ የሚደገሙ አይደሉም፡፡ አንዱ ግን ሁልጊዜ ይደረጋል፡፡ አዳም ከምድር ተወለደ አይደገምም፡፡ ሔዋን ከአዳም ጎን ተገኘች አይደገምም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወለደ አይደገምም፡፡ ሦስቱ ልደቶች ውሱንነት አላቸው፡፡ ድካምና ስንፍና አለባቸው፡፡

የአዳም ከምድር መወለድ በኋላ ለሚሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ ምሳሌ ቢሆንም ስንፍና አለበት፡፡ ምክንያቱም አዳም ከምድር ቢወለድም ለሌሎች የእሱ ከምድር መወለድ ያስገኘው ጸጋ የለም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በመወለዱ ግን ለሁላችን የሚሆን የልደት ጸጋ አስገኝቷል፡፡

የሔዋን ከአዳም ጎን መወለድ ለእኛ ተጨማሪ ጸጋን አላስገኘልንም፡፡ የቃየል ከአዳምና ከሔዋን መወለድ እንደዚሁ ያመጣልን አዲስ ጸጋ የለም፡፡ የክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ ግን በጸጋ እንደሞላና ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ የምወለድበትን ዕድል አሰጥቶናል፡፡ ስለዚህ የእሱ ልደት ከልደቶች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ምንድን ነው የሚለው? ሦስት ነገሮች ይለዩታል፡፡

ያለ አባት ከእናት የተወለደ በመሆኑ

አስቀድሞ ያለ እናት ከአባት ተወልዶ ነበርና ያለ አባት ከእናት የተወለደ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ያለ አባት ከእናትማ አዳምስ ከምድር ተወልዶ የለም ወይ? ሔዋንስ ከአዳም ጎን ተገኝታ የለም ወይ? መገኛቸውን እንጂ አስገኛቸውን መች አየነው? እንል ይሆናል፡፡ አዎ! አዳም ከምድር ነው የተገኘው፡፡ ምሳሌ ነው፡፡ በኋላ ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀደመችው ምድር ከተባለችው ከድንግል ማርያም ለመወለዱ ምሳሌ ስለሚሆን ነው፡፡ የአዳም ከምድር መወለድ ግን ድካምም ስንፍናም አለበት ብለናል፡፡ ለምን? አዳም ከምድር ተበጀ (ተወለደ) ሲያጠፋ ወደ ምድር ተመለሰ ፡፡ አዳም መገኛውም መመለሻውም አንድ ነው የሆነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወለደ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የሚወጣ የለም ተብሏልና ወደ ላይ አረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ስለዚህ የእሱ ያለ አባት ከእናት መወለድ የተለየ ነው፡፡ ሔዋን ከአዳ ተገኘች ብለናል፡፡ ሔዋን ከአዳም ብትገኝም አንቺ በድለሻልና ፈቃድሽ ፣ ታዛዥነትሽና ስልጣንሽ ሁሉ በባልሽ ስር ይሁን ተብላለች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ሲወለድ ግን እሱ በትህትና ለእናቱ ታዝዞ በቸርነቱና በልጅነቱ ለእናቱ ታዘዘ እንላለን እንጂ እሷ ጌታዋን ነው የወለደችው፡፡ ንጉሷን ነው የወለደችው፡፡ ፈጣሪዋን ፣ አስገኝዋን ነው የወለደችው ፤ እሱ እናቱን ፈጠረ እሷም ፈጣሪዋን ወለደችው እንዳለ ሊቁ፡፡ ስለዚህ የሔዋን መወለድ ከክርስቶስ መወለድ ይለያል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ሲወለድ የማይደረግ ተደርጎ ፣ የማይፈጸም ተፈጽሞ ፣ የማይቻል ተችሎ ነው፡፡
እግዚአብሔር ከምድር ሰውን አበጀው ስንል ስለ እግዚአብሔር ብቻ ነው የምንናገረው፡ ምድር እንዲህ አይነት ጠባይ ነበረባት ፣ እንዲህ ነበረች ብለን አንናገርም፡፡ ሔዋንን እግዚአብሔር ከአዳም ጎን አስገኛት ስንል ስለ እግዚአብሔር ብቻ ነው የምንነጋገረው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወለደ ስንል ስለ ሰውም ጭምር ነው የምንነጋገረው፡፡ በሁለት ምክንያት፡፡
1ኛ. እሱ ከሴቶች ሁሉ መርጦ እሷን በንጽህና በቅድስና ጠብቆ በብስራተ መላእክ ማንም በማያውቀው መልኩ ስለተወለደ፡፡
2ኛ. እነዚህ ሁሉ የአዳም ከምድር መወለድ የሔዋን ከአዳም ጎን መገኘት ስለ እግዚአብሔር ብቻ የምንናገርባቸው ናቸው፡፡ አሁን ግን እሱ መለኮት ከሥጋ ፣ ሥጋ ከመለኮት ተዋህዶ ሲወለድ ሥግው ቃል ሰው የሆነ አምላክ (አምላክና ሰው በተዋህዶ አንድ ሆኖ) ስለ ሰውም ጭምር የምንነጋገርበት ምስጢር ስለሆነ ነዉ፡፡ ሰውን ያከበረበት ነው፡፡
እግዚአብሔር አዳምን ከምደር ሲያበጀው ምድር ከእግዚአብሔር ምንም አልወሰደችም፡፡ መለኮት ሰውን ለማዳን ሲፈቅድ ግን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ልዩ ነው፡፡ የማይቻል ነው፡፡ የማይደረስበት ነው፡፡ አዳም ከምድር ቢወለድ የሚደርስበት የሚቻል ነው፡፡ የሔዋን ከአዳም ጎን መውጣት ውስን ናትና የሚቻል የሚደረስበት ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ ግን የማይቻለው ተችሎ ፣ የማይወሰነው ተወስኖ ፣ የማይደረስበት ተደርሶበት ፣ የማይለካው ተለክቶ ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው በቤተልሄም ተወለደ አልንና ቦታውን ተናገረን፡፡ ቅዳሴያችን ለመለካት ቦታ የለውም ይላል፡፡ አሁን ግን እኛ በቤትልሄም ተወለደ ብለን ቦታ ሰጠነው፡፡ በከብቶች በረት ተወለደ አልን፡፡ ታህሳስ 29 ቀን ብለን ቀን ሰጠነው፡፡ ለመለኮት ቀን የለውም፡፡ አሁን ግን አምላክ ሰው ሲሆን ቀን ሰጠነው፡፡ ሌሊት ተወለደ ብለን ደግሞ ሰዓት ወሰንለት፡፡

በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ቀንና ሌሊት ጨለማና ብርሃን የለም፡፡ መለኮት ይሄን ያህላል ይሄንን ይመስላል አይባልም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ ግን (በግዕዘ ሕጻናት) በሕጻናት ጠባይ ጥቂት በጥቂት እያደገ ብለን መጠንና ልክ ሰጠነው፡፡ ሕጻን ሆነ አልን፡፡ በ12ት ዓመቱ አለ ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ 2)፡፡ በሁለት ዓመቱ አለ ቅዱስ ማቴዎስ (ማቴ 2)፡፡ በሠላሳ ዓመቱ አለ ቅዱስ ሉቃስ ( ሉቃ 3)፡፡ ዕድሜ የተቆጠረለት ለምንድን ነው ቢባል ሰው ስለሆነ ነው፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰማይንና ምድርን ያስታረቀ ነው፡፡

ሥጋ በመለኮት ላይ አምጾ ነበር፡፡ ሕግን በመሻር ሥጋ በእግዚአብሔር ላይ አምጾ ነበር፡፡ አሁን ግን መለኮት ከሥጋ ሥጋ ከመለኮት ተዋህዶ ሲወለድ ማንም መልሶ ሊለየው የማይችል ፍጹም ዕርቅ ነው የተካሄደው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የወደደበትና የተገለጠበት መንገድ በእውነት ተናግረን የማንጨርሰው ነው፡፡

ሰው ከተጣለው ጋር ዝምድና ይመሰርታል፡፡ ቢበዛ ይጋባል፣ ልጁን ያጋባል፣ ክርስትና ይናሳል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ሲታረቅ ሊያዩም እኛ አይደለንም ከእርሱ ጋራ የታረቅነው፡፡ እርሱ ነው ከእኛ ጋራ የታረቀው፡፡ እኛ አንችልም ነበር፡፡ ባሕር እሳቱን ተሸግረን ፣ የተዘጋውን የገነት በር አስከፍተን መሄድ አንችልም ነበር፡፡ አቅማችን ውሱን ነበር፡፡ ስለዚህ እርሱ ወደኛ መጣና ፍጹምና ምንም እንከን የሌላው እንዲህ ዓይነት ስንፍና አለው ብለን የማንናገርለትን ዕርቅ ነው የፈጸመው፡፡

ይህ ዕርቅ ሲፈጸም ሰውና እግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን መላእክትም ከሰው ጋር ታረቁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት ወርደው ለሰው መዝሙርን አስተማሩ፡፡ ሰው እና መላእክት አንድ ላይ ዘመሩ፣ ድሮም በገነት አዳም እንደዚህ ነበር፡፡ አዳም የመላእክትን ዝማሬ ነበረ የሚዘምረው፡፡ አዳም ከገነት ሲባረር ከቅዳሴው ነው የወጣው፡፡
ዛሬ አንድ ሰው ሲያጠፋ አታስቀድስ ፣ አትቁረብ ፣ ከማኀበረ ምዕመናን ተለይ ይባላል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለ ፣ እንዲህ አይነቱን ዝሙት የፈጸመውን ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት ይላል፡፡ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት ማለት ሰይጣንን ፈልጋችሁ እንካ በሉት ሳይሆን ከምዕመናን ጉባኤ ከቤተክርስቲያን ጸጋ ለዩት ፣ ንስሐ ሳይገባ ሥጋወ ደሙን እንዳይቀበል ፣ አብሯችሁ እንዳይዘመር ፣ እንዳያስቀድስ ፣ እንዳያገለግል ካደረጋችሁት ከቤተክርስቲያን ጥበቃ ስለሚለይ ለሰይጣን ቅጣት አሳልፋችሁ ሰጥታችሁታል፡፡

አዳም እንዲህ ነበር የተቀጣው፡፡ ከመላእክት ቅዳሴ ታጉሎ ከመላእክት አገልግሎት ተሰናብቶ ከመላእክት ጸጋ ወጥቶ ከማይቀድሱት ከማይሰልሱት እንዲሁ በተፈጥሮ ብቻ ከሚያመሰግኑት ከዕጽዋት ፣ ከድንጋዮች ፣ ከውኃዎች ጋር እንዲኖር ነበር የተደረገው፡፡ አሁን ግን እርቅ ሲፈጸም መላእክት መጡና ወደ ጥንቱ ቅዳሴ መለሱት፡፡

ልበ አምላክ ዳዊት የመላእክትን እንጀራ ሰው በላ ብሏል (መዝ 77)፡፡ መላእክት እንጀራና ዳቦ ኖሯቸው ሰው ሊበላው የሚችል አይደለም፡፡ የመላእክት አንጀራቸው ምስጋናቸው ነው፡፡ የመላእክትን እንጀራ ሰው በላ የተባለውም የተፈጸመው በልደቱ ቀን ነው፡፡ እውነትም ሰው የመላእክትን እንጀራ በላ፡፡ ይሄ ዛሬ የምናመሰግንበት ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና ይሁን ለሰውም በምድር ላይ ፍቅር ፣ ዕርቅ ፣ አንድነት የምንለው መዝሙር የመላእክት መዝሙር ነው፡፡ እረኞቹ ከመላእክት ነው የተማሩት፡፡

እረኞችንም የመረጠበት አንዱ ምክንያት ለፈሪሳዊያን ፣ ለሰዱቃዊያን ወይንም ለኤሲያዊያን ቢያስተምሩት ከራሳችን አንቅተን አብቅተን ዘመርነው ብለው ችሎታቸውን ማሳያ ያደረጉት ነበር፡፡ ከጉባኤ ያልዋሉ መጽሐፍ ያልተማሩ ምንም ሰው ያውቃሉ ብሎ የማይጠረጥራቸውን እረኞችን ግን አስተምረው ሰብከዋል፡፡ ስለዚህ ሰውና መላእክት አብረው አምልከዋል፡፡ እንጂማ ሰው የመላእክትን ተራዳኢነት ድሮም ያገኝ ነበር፡፡ መላእክት ወደ ሰው ይላኩ ነበር፡፡ አምላክን ግን አብረው አያመሰግኑም ነበር፡፡ አሁን ግን በሩ ተከፈተ፡፡

በልደቱ ሰውና መላእክትም ብቻም አይደሉም የታረቁት፡፡ ሕዝብና አህዛብም ታርቀዋል፡፡ ሕግና ሥርዓት የተሰጣቸው እስራኤላዊያን ሕግና ሥርዓት ካልተሰጣቸው ከአህዛብ ከሰብዐ ሰገል ጋራ አንድ ሆነው በአንድ ሌሊት ተገናኝተዋል፡፡ አንድ ቤተልሄም አገናኘቻቸው፡፡ እነዚያ ከሩቅ መጥተው እነኚህ ከዛው ከእስራኤል መጥተው ተገናኝተዋል፡፡ ሰብዐ ሰገልና የእረኞች ቋንቋ፣ አለባበስ፣ ጠባይ ልዩ ነዉ፡፡ ልዩነት ያላቸውን ዕረኞችንና ሰብዐ ሰገልን አንድ ቦታ አገናኛቸው፡፡ ቤተክርስቲያን እንዲህ ናት፡፡

ከተለያየ ብሔረሰብ፣ ቋንቋ፣ ባሕል፣ አቅጣጫ፣ የዕውቀት ደረጃ ልንመጣ እንችላለን፡፡ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ግን አንድ መዝሙር ነው የምንዘምረው፡፡ አንድ አገልግሎት ነው የምናገለግለው፡፡ መገናኛችን ቋንቋችን አንዱ ራሱ ክርስቶስ ስለሆነ ፡፡ ሌላ ቋንቋ የለንም፡፡ ምስጋናችን ራሱ ስለሆነ፡፡ ተልዕኮአችን ራሱ ስለሆነ፤ አነዚህ ሕግ፣ ግዝረት ለያይቷቸው የሚኖሩትን ልደት፣ ዕርቅ ፣ ፍቅር ፣ ትህትና ልዩ ምስጢር አገናኛቸው፡፡
ልደት የድንግል ማርያም ክብር ከፍ ያለበትም ቀን ነው፡፡ በእውነት እግዚአብሔር ለብዙ ቅዱሳን የሰጠውን ጸጋ ልናስበው እንችላለን፡፡ ልንገምተውም ፣ ልናነበውም ፣ ልናውቀውም ፣ ልንደርስበትም እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ለአቡነ ተክለሃይማኖት ፣ ለአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ ለክርስቶስ ሰምራ ፣ ለወለተ ጴጥሮስ የሰጠው ጸጋ በእነሱ መንገድ በመሄድ እንደርስበታለን፡፡

ለድንግል ማርያም የሰጠውን ጸጋ ግን አይደረስበትም፡፡ በፍጹም አይታሰብም፡፡ ከዚህ በኋላ እንደገና አምላክን መውለድን ስለማይቻል፡፡ እንደገና የአምላክ እናት መሆን ስለማይቻል፡፡ ከዚይ በኋላ እግዚአብሔር ከሰው ከስጋ ስጋን ከነፍስም ነፍስን ስለማይነሳ፣ ኀሊበ ድንግልናን ማጥባት ስለማይቻል፣ እግዚአብሔር እናቴ ብሎ የሚጠራው፣ ጡት የሚያጠባው፣ በትከሻው የምትሸከመው ሌላ ስለማትመጣ የእርሷ የማይደገም ነው፡፡ ፊትም አልነበረም በኋላም የማይመጣ ነው፡፡ እንዲሁ ብቻውን ለዘላለም አብሯት የሚቀመጥ ጸጋ ነው፡፡ ይታሰባል ፣ ይደነቃል ፣ ሊደረስበት ግን አይችልም፡፡

ለዚህ ነው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው "ድንግል ሆይ ሰባቱ የእሳት ነበልባል መጋረጃ በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘጋጀ? ወዴትስ ተጋረደ? ከጎንሽ በቀኝ ነውን ወይስ ከጎንሽ በግራ ነውን? ትንሽ አካል ስትሆኝ ይሄን ባሰብኩ ጊዜ ህሊናዬ የልጅሽን የባሕሩን ጥልቅነት ሊዋኝ ይወዳል የወዳጅሽ የመሰወሪያው ማዕበልም ያማታዋል፡፡ በሁሉም ዘንድ በሁሉም ይዞራል፡፡ አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል” ይላል፡፡

በዜና ሐዋርያት ላይ ሐዋርያት እመቤታችንን ጌታችን ካረገ በኋላ በጽርሃ ጽዮን አብሯቸው እያለች አንድ ጥያቄ ጠይቀዋት ነበር ይላል፡፡ ድንግል ማርያም ሆይ ኢየሱስ ክርስቶስ ካንቺ በድንግልና ተጸንሶ በድንግልና መወለዱን እናምናለን፡፡ ግን በማኀጸንሽ ምንድን ነው የተከናወነው? በእናቶቻችን መኀጸን የሚከናወነውን ሲነግሩን እናውቀዋለን፡፡ ባሎች ከሚስቶች ወንድሞች ከእህቶች እንሰማዋለን ፤ በአንቺ መኀጸን ግን ምንድን ነው የተፈጸመው? እርሷም ቅዱስ ገብርኤል መጣና ትጸንሻለሽ አለኝ፡፡ ተከራክሬ እንዴት ይቻላል አልኩት፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም አለኝ፡፡ ለእግዚአብሔርማ ምን ይሳነዋል ፤ ያልከው ይሁንልኝ አልኩት፡፡ ከዚህ በኋላ ያለውን ልነግራችሁ አልችልም ነው ያለችው፡፡

ጎርጎሪዎስ ዘኑሲስም ስለ ድንግል ማርያም በጻፈው ድርሳን ላይ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ትጸንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ፣ ካንቺ የሚወለደው የብረቱን በትር የሚገዛው አለቃ ነው ብሎ ነገራት፡፡ ተከራከረችው ፤ ሔዋንን በትዕቢት ንግሥተ ሰማይ ወምድር ብሎ ያሸነፈ ዲያቢሎስ እኔንም ሊያሸንፈኝ ነው ብዬ ለሐዋርያት እንደነገረችው ተከራከረችው፡፡ መጨረሻ ለመሆኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን ሲላት ለእግዚአብሔር ምን ይሳነዋል እግዚአብሔር ካለ ሁሉን ይችላል፡፡ እንደወደድከው ይሁንልኝ እኔ ለእግዚአብሔር የተዘጋጀው ባርያው ነኝ አለችው፡፡ ከዚያ ቃሏን ተቀብሎ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ያከናወነውን ቅዱስ ገብርኤልም አላየው ነው የሚለው፡፡ አበሰራት ነገራት እንጂ በድንግል መኀጸን ለመሆኑ ምን ሆነ? ምነ ተፈጠረ? ምን ተከናወነ? እንዴት ነው የሆነው? ይሄንን ምንም አላየም፡፡ ይሄንን ያወቀች የእግዚአብሔር የምስጢር መዝገብ እርሷ ብቻ ናት፡፡
ብዙ ሊቃውንት ተነስተዋል እስከ ሰማየ ሰማያት ደርሰዋል፡፡ ብዙ ቅዱሳን ተነስተዋል የተሰወሩትን ምስጢራትን አምጥተዋል፡፡ ይሄንን ምስጢር የቻለ ግን የለም፡፡ የእርሷ ነገር የተለየ ነው፡፡ የእርሷ እናትነት በድንግልና ጸንሶ በድንግልና መውለድ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያም በላይ የሚልቁ ነገሮች በእርሷ መኀጸን ተከናውነዋል፡፡

ኪሩቤል ሲያመሰግኑ ድንግል አንገቷን ጎንበስ አድርጋ ታዳምጥ ነበር፡፡ የመላእክት ምስጋና ሲመሰገን በሰማይ ኪሩቤል ሊያዩት እንኳን ሳይቻላቸው ሱራፌል ሲያመሰግኑት ሊያዩት ያልተቻላቸውን በመኀጸን ስትሸከም በመላእክት ዓለም ምን ተከናወነ ይሆን? ፍጥረታት ምን አሉ ይሆን? ምስጋናቸው በላይም እያለ የነበረው በታችም በድንግል ማርያም መኀጸን ሲያድር እንዲሁ ምስጋና ነበረ፡፡

ድንግል የአራቱን ኪሩቤል እርሷ ምድራዊት ኪሩቤል ስትሆን ምንድን ነው የሆነው? ለዚህ ነው አባ ሕርያቆስ ዙፋኑ የትነው የተዘጋጀው ያለው፡፡ እሱ ንጉሥ ነውና ዙፋን አለው፡፡ ያንችስ መኀጸን እንዴት ነው የቻለው ብሎ የጠየቀው ለዚህ ነው፡፡ ጥያቄ ጠይቋል መልስ ግን አላገኘም፡፡ በመጨረሻ ግን ሲደመድም ገናንነቱን አንመርምር ጥልቅነቱንም አንጠናቀቅ፡፡ የገናንነቱንም መጠን ለማመስገን የነቢያትና የሐዋርያት አንደበት የማይቻለው ነው ብሏል፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ፍቅር የገለጠበት አንዱ መንገድ ስለሆነ ልዩ ነው፡፡ አንድ የሶሪያ ሊቅ "እግዚአብሔር ሰውን ምን ያህል እንደሚወደው ከገለጸበት አንዱ ድንግልን (ሰውን ) እናቱ በማድረግ ነው” ይላል፡፡

በልደቱ ቀን የምናነሳው ብርቱዎችን ብቻ አይደለም፡፡ እንደ ቤተልሄም ሰዎች ሰነፎችም አሉ፡፡ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላልተገኘለት በበረት የበኩር ልጇን ወለደችው፡፡ ቤተልሄምን እንግዶች ሞልተዋት ነበር፡፡ በቤተልሄም ያ ሁሉ ታሪክ ሲፈጸም ሰብዐ ሰገል ከሩቅ ሲመጡ ፣ እረኞች መዝሙር ሲዘምሩ ፣ መላእክት ከሰማይ ሲወርዱ ፣ ሰማይና ምድር የፈጠረ አምላክ ራቁቱን ሲጠቀለል ፣ በብረት ሲተኛ ፣ ከብቶች ሲያሟሙቁት የቤተልሄም ሰዎች አልሰሙም ነበር፡፡ አላዩም ነበር፡፡ በመሐል ቤተልሄም ነው ይሄ የተከናወነው፡፡

እረኞችን ከሜዳ ጠርቶ መልአኩ ሲያመጣ አልሰሙም ነበር፡፡ በኋላ ሰብአ ሰገል ሰምተው የተወለደው የአይሁድ ንጉስ ወዴት ብለው ሲጠይቁ ነው "አንቺ ቤተልሄም የይሁዳ ምድር ከአይሁድ ገዥወች ከቶ አታንሺም፡፡ ሕዝቤ እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉስ ተወልዷልና በቤተልሄም በኤፍራታ ነው አሉ”፡፡ የእውቀት ችግር አልነበረባቸውም፡፡ የሚወለዱበትን ቀን ብቻ ያውቁት ነበር፡፡ ግን አልሄዱም ፡፡

ዛሬም በቤተክርስቲያን ጸጋው ሲፈስ ፣ እግዚአብሔር ሥራ ሲሰራ ፣ ለቅዱሳን ከሚንቀለቀለው እሳት እነሱንም አብልቶ እሳት ሲያደርጋቸው ፣ ከሚፈሰው ውሀ እነሱንም አጠጥቶ ከሆዳቸው የሚመነጭ ውኃ ሲሰጣቸው የሚያውቁ ግን ተኝተው የሚያድሩ ብዙ ወገኞች አሉ፡፡ በሕይወታቸውም በአኗኗራቸውም ፣ የተገኙ ለሃይማኖት ግድ የሌላቸው ፣ ለጸሎት ፣ ለጾም ፣ ለስግደት ፣ ለቅዳሴ ፣ ለቁርባን ግድ የሌላቸው የቤተልሔም ሰዎች ዛሬም አሉ፡፡ ቤተልሔም የጌታችንን ልደት ለማክበር በየዓመቱ ሰዎች እየሄዱ ይሳለሟታል፡፡ ሁልጊዜም ሰዎቹ ይነሳሉ ይወቀሳሉሉ፡፡ ሰው ሁሉ ይገረምባቸዋል፡፡ ዕድሉ አምልጧቸዋልና፡፡

ሊቃውንት በፈሰሱበት ፣ ጉባኤው ካለበት ፣ ጸጋ ከሞላበት ላይ እያለን እየዋልን የጎረቤት ጠበል የልጥ መንከሪያ ይሆናል የሚባለው እንዳይደርስብን ያስፈልጋል፡፡ የቤተልሔም ሰዎች እጅ መንሻቸውን ይዘው ጌታን የሚጠቀልሉበት ፣ ሸማውን የሚያለብሱበት ፣ ምድጃቸውን አሙቀው የተወለደውን ልጅ ለማማሞቅ ከብቶች የሰሩትን ስራ ለመስራት የሚነሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ከእረኞች የተሻለ መዝሙር አለን ብለው የሚቀርቡበት ነበር፡፡

ፈሪሳዊያንና ሰዱቃዊያን ዕውቀታቸውን ይዘው የሚመጡበት የሚንበረከኩበት ጊዜ ነበር፡፡ ግን አልታደሉም፡፡ አንድ ሰው ስላወቀ ፣ ስለተማረ ፣ ስላነበበ ፣ ሊቅ ስለሆነ ፣ ወይም በክህነት ቅልቅ ማዕረግ ላይ ስለደረሰ ብቻውን ለጽድቅ አያበቃም፡፡ ከፈሪሳዊያን በላይ አዋቂ ከሱዱቃዊያን በላይ ተመጻዳቂ ማንም አልነበረም፡፡

ከቤተልሐየም ሰዎች በላይ ለበረቱ ቅርብ ማንም አልነበረም ፤ በክርስትና መቅረብ አይደለም፡፡ መሆን ነው ፤ ማድረግ ነው ፤ የበረከቱ ሱታፌ ሊኖረን ሲችል ነው፡፡ ልደትን ስናከብር ሕይወታችንን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋራ አንድ አድርገን በልደቱ እንደተጠቀሙት እንደ ሰብዐ ሰገል ፣ እንደ እረኖቹ ፣ እንደ ዮሴፍና ሰሎሜ ከዚያም ካለፈ በእስትንፋሳቸው ካሟሟቁት ከብቶቹ እድል ፈንታ እየተሳተፍን ነው መሆን ያለበት፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Adama?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Adama