IDEA ሃሳብ

IDEA ሃሳብ የሽያጭ ሰራተኞች ለቀጠራቸው ይሰራሉ፥ ደላሎች ለራሳቸው ይሰራሉ፥ ሻጭም በፍጥነት ከእጁ እንዲወጣ ይፈልጋል፥ በገዢ በኩል ሆኖ ሁሉንም ነገር በማስተዋል የሚያግዝ ያስፈልጋል።

እርሶን እኛ እናግዞታለን!!!

06/09/2026

ቤት ስትገዙ ውል በደንብ እዮ

ለምሳሌ:- አልሚው ቤቱን በተባለው ጊዜ ቤቱን ማሴረከብ ባይችል እና ገዢ ውሉን ማፍረስ ቢፈልግ ሪልስቴቱ ቤቱን ሸጦ ይመልሳል ይላል።

ላለመሸጥ ቢለግምስ?! ብሬ እንዴት ይመልሳል ብላችሁ ጠይቁ።

በግሽበት ለሚጠፋው ገንዘቤ ምን ማካካሻ አለኝ በሉ

06/08/2026

ቤት ግዢ ስሜታዊ ያደርጋል፤ በተለይ ከድህነት ለመውጣት ለሚጣጣር ሰው አንዱ "የስኬት" ማሳያ ነው። ብዙ ሰው ግን ትናንሽ ሸመታ ላይ የሚወስደውን ጥንቃቄ እና ጥናት ሳያደርግ ይወስናል።

የምትገናኙት የህጉን ክፍተት ከሚያውቁ ፥ የደንበኛን ስሜታዊነት ከሚረዱ ፤ በደንብ ከሰለጠኑ ሰራተኞች ጋር ነው። የህይወታቹ ትልቁ የገንዘብ ውሳኔ ስለሚሆን በደንብ ጊዜ ወስዳቹ አስቡበት።

ይህ ፔጅ ለቤት ገዢ የወገነ ነው!

06/08/2026

እኔ መገናኛ ታክሲ ተራ መሃል "የትላልቅ" ሪልስቴት ሽያጭ ሰራተኞች ምን አይነት ገዢ ሊያገኙ ነው!? ብዬ በከንቱ ልፋት እጠረጥራቸው ነበረ።

እውነቱ ግን እኔ ነኝ የዋህ!

እዛ ታክሲ ተራ ሊኖር የሚችለው ባለገንዘብ ለከተማው አዲስ ይሆናል፥ የሆነ ውርስ አግኝቷል ወይ ሊያገኝ ነው ፥ የተወሰነ ቁጠባ አለው ፥ኮንዶሚኒየሙን ሸጦ መክፈል ይችላል፥ ከመስሪያ ቤቱ የተወሰነ መበደር ይችላል፥ ቢያንስ ቢያንስ ያለችውን ቁጠባ ይሰጣል።

እነዚህን ገዢዎች በአብዛኛው የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ እሱም የመለወጥ ትልቅ ጉጉት እና ስለቤት ገበያው ደሞ አነስተኛ እውቀት።
ሁለቱም ባህሪያት ደንበኞችን ለአደገኛ ሻጮች የተመቹ ያደርጋቸዋል

06/06/2026

ወላ ትዳር፥ንብረት ፥አሜሪካ፥ካናዳ
ምንም ነገር በእጃቹ እስኪገባ እና ተሳክቶ እክትኖሩት አታውቁትም !!

06/06/2026

ቺስታ የቤት ባለቤቶች(House Poor)

አንድ ወዳጄ የመለስተኛ ባለሃብት ረዳት ነው። ስለባለሃብቱ ሲያወራ " እኔን ግርም የሚለኝ አለቃዬ ካንድም ሁለት ንግዶች አሉት ፤ በዛላይ ሪልስቴት እየገነባ ይሸጣል ለራሱ ግን ተከራይቶ ነው የሚኖረው ፤ ይባስ ብሎ ደሞ የስራ እንጂ የቤት መኪና የለውም "

በድህነት የሚንገላታ ሰው ህልም ደሞ ቤት እና መኪና ነው ፤ መሃከለኛ ኑሮ የሚንኖረው የሚሯሯጠው G+3 ለመስራት እና መኪና ለመንዳት ነው ።

እውነት ግን ቤት እና መኪና መግዛት ከድህነት ያወጣል??

06/04/2026

ለድህነትህ ወላጆችህን ታማርራለህ፤ አሁን ደግሞ ሜዳውም ፈረሱም ላንተ ተሰጥቶሃል። እስኪ መኖር ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እናየዋለን

06/04/2026

አንድ ፈረንጅ ሃብታም የተናገረው

​እዚህ ያለውን ቤት በካሽ (በጥሬ ገንዘብ) ነው የገዛሁት። ምንም ብድር የለም፣ ምንም ዕዳ የለም። አሁን ይህንን የምነግራችሁ ለመፎከር ሳይሆን በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ለማጉላት ነው።

​ዕድሜዬ በ20ዎቹ አካባቢ በነበረበት ጊዜ ጥቂት ገንዘብ አግኝቼ ነበር። እናም አንድ ሰው “ሲሞን ምን ማድረግ እንዳለብህ ታውቃለህ? ቤት መግዛት አለብህ” አለኝ። በወቅቱ ልገዛ ምንም አልቀረኝም ነበር። ያንን ትንሽ የማይረባ ቤት ልገዛው ተቃርቤ ነበር።

​ነገሩ ግን ሰዎች የማይረዱት ነገር፣ ያንን ካፒታል (ገንዘብ) ወስጄ ያንን ትንሽ የማይረባ ቤት ገዝቼው ቢሆን ኖሮ፣ ሁሉንም ገንዘቤን ተጠቅሜ፣ በየቀኑ ተጨማሪ ገንዘብ እያወጣሁበት፣ ያ ቤት ዛሬ የሚኖረው ዋጋ ወደ £400,000 (አራት መቶ ሺህ ፓውንድ) አካባቢ ነበር።

​እኔ ግን በዚያ ፈንታ ያንን ገንዘብ የራሴ በሆነ ንግድ (ቢዝነስ) ላይ አዋለኩት። ዋጋው እንዲጨምር ወይም እንዲቀንስ በእኔ ጥረት ተጽዕኖ ልፈጥርበት የምችልበት ነገር ላይ ማለት ነው። የዚህ ቤት ዋጋ እንዲጨምር እኔ ምንም ተጽዕኖ ልፈጥርበት አልችልም። እንዲያውም ይህ ቤት ገንዘብ የሚበላ እንጂ ሀብት (asset) አይደለም፤ እሱ እዳ/ኪሳራ (liability) ነው። በየሳምንቱ ገንዘብ እያወጣሁበት ነው።

​ይህንን ቤት ዛሬ በጥሬ ገንዘብ ልገዛ የቻልኩበት ብቸኛው ምክንያት፣ ያንን አይነት የአስተሳሰብ ዘይቤ (mentality) ስላለኝ ነው። ሰዎችንም ላስተምር የምፈልገው ይህንን ነው። ወጣት እያላችሁ ትልቅ አስቡ፣ ስጋት (risk) ለመውሰድ አትፍሩ፣ በአንድ ቦታ ላይ አትታጠሩ፣ እናም ሀብት (asset) ያልሆነንና በየጊዜው ገንዘብ የሚጠይቅን እዳ (liability) አትከዝኑ።

​ያንን ገንዘብ በጥሬ ገንዘብ ገዝቼ ይህንን ቤት ለመግዛት የቻልኩበት ምክንያት ያ አስተሳሰብ ስለነበረኝ ነው። ለዛ ነው ሰዎችን ማስተማር የምፈልገው። ወጣት እያላችሁ ትልቅ አስቡ፣ ስጋቶችን ውሰዱ፣ በአንድ ቦታ ላይ ብቻ አትወሰኑ፣ እናም ሀብት (asset) ያልሆነንና ወጪ ብቻ የሚጠይቅን እዳ (liability) የራሳችሁ አታድርጉ።

06/01/2026

መጀመሪያ የቂጤን

የግል ቤት ኖሮን ስለማያውቅ እናቴ ብዙ ግዜ ስለቤት ወሳንኝት ስታወራ በዚ ተረት ትገፋለች፤ ካደኩ በኋላ ቤት እንድገዛ ካነሳሱኝ ምክንያቶች አንዱ ይህ ተረት ነው። ሙሉውን ከእናቴ እንደሰማሁት እንደወረደ አቀርበዋለሁ።

ዝንጀሮ ናት አሉ በአንድ ክፉ አጋጣሚ ከገደል አፋፍ ላይ ትንከባለላለች፤ በዚህ የተነሳ እሾህ መላሰውነቷን ይወጋጋታል። ቂጠ ባዶ (butt naked) ስለሆነች የበለጠ እሱ ላይ ይጎዳታል፤ መንጋው ተሰብስቦ

" ምን እናድርግልሽ? ምንሼ? " ሲሏት

"መጀመሪያ የቂጤን ንቀሉልኝ ሌላውን እኔ ራሴ ቁጭ ብዬ እነቅለዋለው አለች "አሉ

መጀመሪያ የቂጤን የተባለው መቀመጫ ፣ ቤት መሆኑ ነው። መረጋጋት ፤ ፋታ ፤ እረፍት ፤ በራስ መተማመን ይሰጣል ፤ ይሄ ሁላ ነገር ካለ ሌላው ቀላል ነው ለማለት ነው።

ግን ቤት መግዛት እነዚህን ነገሮች ይሰጣል???

05/31/2026

ቤት መግዛት ለሁሉም አይደለም ፤ እኔ በሄይወቴ ተጓዥ መሆን ብፈልግ ቤት አያስፈልገኝም። ቤት በምፈልልገው ህይወት ውስጥ ምን ቦታ አለው ብሎ መጠየቅ እና ቅደም ተከተሉን ማወቅ ያስፈልጋል።

ቤት ገዝቼ ቢዝነስ ልስራ ወይስ ቢዝነስ ሰርቼ ቤት ልግዛ?

05/31/2026

ከምን ልቆጥብ

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳይት ሰዎች የሚያውቁት እና የሚቀሊቸው ቦታላይ ነው ሀተታ የሚያበዙት፤ ብዙም አይቸገሩበትም፤ ይተነትኑታል ። ለምሳሌ አንድ መስሪያ ቢሮ ውስጥ ሶስት የበጀት ስብሰባ ቢኖር እና
>ለግድብ 1ቢሊዮን ብር
> ለመኪና ማቆሚያ ጥላ 250 ሺ እና
> ለሰራተኛ የስራ ጫማ 75ሺ ብር ቢኖር

ገምግሙት ቢባል

አትጠራጠሩ የግድቡ ስራው ወዲያው ይፀድቃል፤ የመኪና ማቆሚያ ጥላው የተወነሰ ክርክር ይኖረዋል ፣ ጫማው ግን ብዙውን ጊዜ ይወስዳል።ምክንያት የምንበረታው የምናውቀው እና የሚቀለን ነገር ላይነው።

ቤት እና መኪናን የሚያካክሉ ግድንግድዬ ውሳኔዎች በቀላሉ ወስናቹ በየቀኑ ምሳቃ ብቋጥሩ፣ ቡና ሳትጠጡ ስታዛጉ ብትውሉ፣ ግሮሰሪ ላይ የቅናሽ ቅናሽ ብታሳድዱ ብዙም ዋጋ የለውም።

ትናንሽ ቁጠባ የሚሰራው በትላልቅ በመስሪያ ቤት ፣ በትተላልቅ ንግድ ቦታ ፣ በመንግስት ደረጃ እንጂ ለግል ህይወት እንደነገሩ ነው ፤ ለሳይኮሎጂ እየታተርኩ ነው ለማለት ነው እንጂ ውጤቱ እምብዛም ነው።
_________________________________
ሀሳብ ከArt of spending money Morgan R

Address

AYAT 49
Toronto, ON

Telephone

+14374294808

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when IDEA ሃሳብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to IDEA ሃሳብ:

Shortcuts

Share