12/11/2025
አዎ እናት ስታለቅስ ማየት በጣም ከባድ ነው! ግን ግን
እናትም አባትም መጀመርያ ነበር ተው ልጄ ብሎ መምከር….. ለካ ልጁ አይደለም የራሱን የሌላውን ወላጅ እትስሙ ይል ነበር::
መንግስት የሚያጣራውን አጣርቶ የሚለውን እንጠብቃለን::
አዎ እናት ስታለቅስ ማየት በጣም ከባድ ነው ነገር ግን ደግሞ እናትም ሀላፊነት አለባት ልጅ ሲንፈራገጥ እና ያዙኝ ልቀቁኝ ካለእኔ ሰው የለም ሲል እናት ደግሞ ልጄ ረጋ በል እስቲ ነገሮችን ከመናገርህ እና ከማድረግህ በፊት በደንብ አስብ ብላ መምከር አለባት: አባትም በበኩሉ ልጄ ብሎ ብይለው ልምድ መምከር እንደውም ገጨት እያደረገ ማስተማር ነበረበት::
ግን ለካ ምን ዋጋ አለው ልጁ አይደለም የራሱን የሌላውን ልጆች ወልጅ እንኳን እትስሙ ብሏል::
12/01/2025
በኢትዮጵያ የተለያዩ የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች በተለይ ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ለሚመሩት የትምህርት ምኒስቴር እንዲሁም አማኑኤል የአዕምሮ ህክምና
ሰሞኑን የቲክቶክ አዋርድ በሚል ስም የተዘጋጀው ድግስ ላይ የተገኙትንም ሆነ በምርጫው የተሳተፉትን እንዲሁም ስለዝግጅቱም ሆነ ተወዳዳሪዎቹን ኢንተርቪው ያደረጉ የሶሻል ሚድያዎችን ጨምሮ ቁጥራቸውን፣ጾታ፣ እድሜ፣ የተማሩበትን ትምህርት ቤት እንዲሁም የሚኖሩበትን አካባቢ በማጥናት እና ፈቃደኛ የሆኑትን ደግሞ ለምርምር ረዘም ያለ ኢንተርቪው በማድረግ ሀገራችን ላይ የገባውን የአእምሮ ወይም የአስተሳሰብ ንቅዘት ለመቅረፍ ትልቅ ጥናት በማድረግ ቀጣዩን ትውልድ ከዚህ ወረርሽኝ የሚታደግ ክትባት መዘጋጀት አለበት::
በትምህቱም የሚጨመር የትምህርት አይነት ካለ እንዲጨመር ጤና ጥበቃም ማውጣት ያለበት የድንገተኛ ቫይረስ ወረርሽኝ ማስጠንቀቂያ ሰቶ ህክምና ቢጀምር ጥሩ ነው ባይ ነኝ
ግልባጭ:-
የትምህርት ምኒስቴር
አማኑኤል የአእምሮ ህክምና
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
ለሴቶችና ህፃናት ጉዳይ
ለሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎችና ጥናት ምርምር ለሚሰሩ
እንዲሁም የቀጣዩ ትውልድ እጣ ፋንታ ለሚያሳስባቸው ሁሉ!
12/01/2025
ኢትዮጵያ የሚለውን ሥም ስንጠቀም በኅላፊነት እና በጥንቃቄ መሆን አለበት
ኢትዮጵያ የሚለው ሥም ከ130 ሚሊዮን በላይ ያለ ህዝብ እሴት ባህል እና ኀይማኖትና ታሪክ ያቀፈ የገዘፈ ቃል ነው። ዛሬ ላይ ይህን ገናና “ኢትዮጵያ” የሚል ሥም ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና ቡድኖች በህዝብ ፊት ፣ በፕሮሞሽን ወይም በየሶሻል ሚድያው ላይ እንዲሁም ለተለያዩ ፕሮግራሞች እየተጠቀሙበት ነው። ከነዚህ ወስጥ ብዙዎቹ የሚያቀርቧቸው የፕሮግራሞች ይዘቶች ከኢትዮጵያውያን እሴት፣ ከእምነት እና ባህል ጋር የሚጣረሱ መሆናቸው ላይ ነው ጥያቄው። አልፎ ተርፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር እንደማንኛውም ሙዚቃ ሪሚክስ ተደርጎ ሲለቀቅ እስከማየት ደርሰናል!
“ኢትዮጵያ”፣ “ኢትዮጵያዊ” ወይም ተዛማጅ ቅጂዎች በማንኛውም ህዝብ ፊት ለንግድም ሆነ ለተለያዩ ፕሮግራሞች ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ፤ በመንግሥት ለምን ጥቅም እንደሚውሉ የሚረጋገጡ እና የሚፈቀዱ መሆን አለባቸው። ይህ የሀገራችንን ክብር ለመጠበቅ እና ከ130 ሚሊዮን ለሚበልጡ ዜጎች ኃይማኖት እና እሴት ያለአግባብ እዳይስተጋባ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።
ሙሉውን ካነበቡት አስተያየቶን ይስጡን👇
11/28/2025
አቶ እሌክስ - በመጀመሪያ የዚህ ጽሁፍ ስህተት የተፈጠረውን ክስተት አሳንሶ እና ተራ የሰፈር ውስጥ ጠብ አድርጎ ለማሳየት ከመሞከር ይጀምራል። በረራ መሰረዝ “በየትም ሀገር ይከሰታል” ብሎ ማቅረቡ በግልፅ እውነት ነው ፤ ግን ያ በወጣቶቹ የተደረገው ባህሪ መጮህ፣ ከሰራተኛ ጋር መጨቃጨቅ፣ ቪዲዮ በመቅረጽ አንድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ወደ ቀለጠ መንደር መቀየር ፤ እስቲ በሌላ ሀገር አድርገው እና ውጤቱን ታየዋለህ። ይህ ስሜታዊ በመሆን ሳይሆን መብቴ ነው የሚል ጥያቄ ከጀሮባው እንዳለ ይገባኛል። የሶሻል ሚድያው ጀማ ያወጣኛል ብለው ሲጮሁ የነበረውም ለዚያ ነው።
መጨረሻ ላይ ደግሞ “እንዲፈቱ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለሀል! እሱ የግል መብት ቢሆንም አስተሳሰቡ ግን በራሱ ያስጠይቃል።
እንዲህ አይነት ጉዳዮች በልብ ወለድ ድርሰት ወይም በስነጽሁፍ ብቃት የሚታዩ ሳይሆን እንደማንኛውም ዜጋ በህግ ይሆናል። እንደው ግን እነዚህ ሰዎች የማይታወቁ ቢሆን እንደዚህ ወርደህ ትጽፍላቸው ነበር? ሌላው ጥያቄ ነው። ምን ቢያገኝ ነው፣ ምን አቅምሰውት ነው የሚል ሌላ ጥያቄ ቢያስከትልም ምክኒያታዊ ጥርጣሬ ነው!
ሰዎች ትንሽም ይሁን ትልቅ ላጠፉት ነገር በህግ የሚቀጡና የሚጠየቁበት የራሱ ምክኒያትና ጥቅም አለው። ዋነኛው ሰው ባጠፋው ልክ ሲቀጣ ሌላው ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይሰራ ለማድረግ ነው።
በየትኛውም ዓለም ድንበር እና አየር ማርፊያ የተለየ ጥበቃ ያስፈልገዋል፣ ይደረግለታልም። አየር መንገዱ ብቻ አይደለም ይህን በህግ የሚጠይቀው። አየር መንገዱ እንደ አንድ ተቋም ክስ ሊመሰርት የሚችልባቸው ህጋዊ መሰረቶች አሉት ፤ መንግስት ደግሞ ከፀጥታና ደህንነት ጋር በተያያዘ መክሰስ የሚችልባቸው ከበቂ በላይ ምክኒያቶች አሉት።
እዛው አንዱ ቢሮ አስገብቶ አረጋግቶ ምናምን ላልከው ሀሳብ፣ አየር መንገዱን የረበሹት የ10 እና 12 ዓመት ልጆች አይደሉም! ነብስ ያወቁ እና ስራ የሚሰሩ ዜጎች ናቸው። በዛ ላይ ቀጥሎ የሚመጣውንም ረባሽ እንዲሁ እያባበሉ ሊኖር ነው!? ከዚህ ሁሉ ያንተን ጽሁፍ ለጠበቃቸው ልከህለት ፍርድ ማቅለያ ቢጠቀምበት ትርጉም አለው።
ፍርድ ቤት ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰጠውን ቅጣት ማግኘት የግድ ነው ፤ ጠበቃቸውም ተከራክሮ ነጻ ማስለቀቅም ሆነ ቅጣት ማስቀነስ የሱ የቤት ስራ ነው።
11/27/2025
ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ዐይኑን በጨው አጥቦ በጠራራ ፀሀይ ፓርኖግራፊ በስነጽሁፍ ስም "እንካችሁ በገንዘባችሁ" ብሎ! በውጭው ዓለም በፊልም ያለውን በጽሁፍ ያበላሸውን ትውልድ አሁን አዶናይ መጣብህ ብትለው አይሰማህም:: ነገር ግን እውነትን ከመናገር እና ጥቂት ሰሚ ካለ እሱን ለማትረፍ እንሰራለን!
በነገራችን ላይ ካለፈው ይበልጥ አሁንም ድረስ መጽሀፎቹ ገበያ ላይ መሆናቸው በተለይ እድሜያቸው ያልደረሱ ልጆች በቀላሉ ሊያገኙት የመቻላቸው ጉዳይ ያሳስባል!
ደራሲው ሌላ በሰራቸው ስነጽሁፎች ስህተቱን ማስተባበል አንዱ የድንቁርናችን ምልክት ነው::
ክርስትና እና የእስልምናን የመሳሰሉ የተከበሩ ኃይማኖታችንን መከተል እና በተግባር መኖሩ ነው የሚያዋጣንም ትውልዱን የሚያተርፈውም!
11/12/2025
🇪🇹 የዚህ ፌስቡክ ፔጅ እና የቻናሉ አዲስ አቅጣጫ | The New Direction
ኢትዮዺያዊ ካልሆንክ/ካልሆንሽ ሀይማኖት እና የኢትዮዺያ ባህል እና እሴቶች ከሌለህ/ ከሌለሽ ወይም የማይመችህ/የማይመችሽ ከሆነ ይሄን የፌስቡክ ገጽ ፣ ይሄን ቪድዮ ሆነ የኔን ስራዎች እንዳታዩ ግዜያችሁን እንዳታባክኑ
🇪🇹 የቻናሉ አዲስ አቅጣጫ | The New Direction 🎯 #Ethiopia #Truth #Awareness
🇪🇹ኢትዮዽይዊ ካልሆንክ/ካልሆንሽ ሀይማኖት እና የኢትዮጵይ ባህል እና እሴቶች ከሌለህ/ ከሌለሽ ወይም የማይመችህ/የማይመችሽ ከሆነ ይሄን ቪድዮ ሆነ የኔን ስራዎች እንዳታዩ ግዜያችሁን...
10/05/2025
ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ፌስቡክ ፔጅ አላማ እና ስራ ሙሉ
በሙሉ ተለውጧል
ፔጁ ከዛሬ ጀምሮ ዓላማው ለህዝቡ እና ለቀጣዩ ትውልድ
የሚጽፉት ወይም ቪድዮዋቸው እንዲታይላቸው ወይም ሌላ ጥቅምን አገኛለው ብለው በልጆቻችን፣ በእህቶቻህችን ባጠቃላይ በህዝባችን አእምሮ እና ግዜ ላይ የሚጫወቱትን ሰዎች ፣ አካውንቶች እና ፖድካስት ነን ባዮች መርምሮ ለህዝብ ማሳወቅ ነው::
በስመ ኮንቴት ክሬተር ፣ ኢንፍሉዌንሰር እና ሪሌሽን ሺፕ ኮች የሚባሉትን ነው
ኢትዮጲያዊ ላልሆነ ፣ ሀይማኖት ለሌለው ፣ ኢትዮጲያዊነትን የሚወክሉ ባህል እና እሴቶች ለሌለው ወይም የማይመቸው ካለ ይሄ ፔጅ ሆነ ከዚህ ፔጅ ስራዎች ጋር አይመቻቹም!
ሀሳባችን እና ስራችን ከተመቾት ላይክ ሼር እንዲሁም ሀሳቦን በኮመንት እየሰጡን እንጏዛለን ፤ ነገር ግን ያቀረብነው ስራ ወይም ሀሳብ ካልተመቾት ከመሄዶ በፊት በኮመንት መስጫው በጨዋ ደንብ ይሞግቱን🙏 🇪🇹
መልካም ግዜ