መልእክተ ዳዊት

መልእክተ ዳዊት

Share

Truth Matters

Operating as usual

09/01/2025

የሌለ ሲፈለግ
ከእግዚአብሔር ሌላ መፈለግ ጉዳት ነው
ሰው የወደቀው ከእግዚአብሔር ሌላ ሌላ ነገር ስለፈለገ ነው። በኤደን ገነት ውስጥ, እግዚአብሔር የሕይወትን ዛፍ ለአዳም አዘጋጀለት፣ ያ ዛፍ ደግሞ እግዚአብሔር ን የሚያመለክት እና የሚወክል የህይወት ዛፍ ነበር። እግዚአብሔር ለአዳም ህይወቱና ሁለ ነገሩ ሆኖ እንዲኖረው ፤ እንዲበላውና እንዲደሰተው ቀረበለት። ያ ከጌታ የተሰጠው የህይወት ዛፍ በቂው ነበር። አዳም ግን የህይወትን ዛፍ ትቶ መልካምና ክፍን ከምታሰታውቀው መብላትን ወደደ። በላም በበላም ጊዜ ከእግዚአብሔር ህይወት፣ መገኘቱን ከሚደሰትበት አለም ወጣ።
አኛም የሀዲሱ ኪዳን አማኞች ክርስቲያኖች እርሱን ክርስቶስን እንደ ሕይወታችን፣ ደስታችን፣ ሃይላችን ምግባችን እና ሁሉም ነገር አድርገን ልንቀበለው ፣ ይገባል። እንበላው ፣አንጠጣ ዘንዳ የህይወት እንጀራ፣ የህይወት ውሀ ሆኖ መጣ። እኔን ብሉኝ ፣ ጠ ጡኝም በህይወትም ትኖራላችሁ አለን። ሆኖም፣ የሰይጣን ትምህርትና ፈተና ከሕይወት ዛፍ ውጪ ሌሎች ነገሮችን እንድንቀበል እና እንድንፈልግ ያደርገናል። መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀው ዛፍ ምንድን ነው? እሱ የሚያመለክተው ከ ክርስቶስ ውጪ ያሉትን ነገሮች ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ ነገር ሁሉ መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ ፍሬ ነው። ይህ ዛፍ በጣም የተወሳሰበ ነው; መልካም ነገር፣ ክፉ ነገር እና እውቀት አለው ይህም ሁሉ ሞትን ያስከትላል። ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ ነገር ምንም መልካም ቢመስልም መልካምና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ, ሰው በሰይጣን ተንኮል ተታሏል እና ከእግዚአብሔር ሌላ መረጠ. ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ በተወሰነ መልኩ፣ ሰው እግዚአብሔርን አጥቷል፣ እናም በውስጡ ሞቷል።
አንድ ሰው ለአደጋ ሲጋለጥ፣ ጥበቃ ይፈልጋል; አንድ ሰው በስጋት ከሆነ, ደህንነትን ይፈልጋል; አንድ ሰው ደስተኛ ባልሆነ ቁጥር የበለጠ ደስታን ይፈልጋል። በዘፍጥረት 4፡21 መሰረት አዳም ከእግዚአብሔር ከተለየ በኋላ የቃየን ዘሮች ሰዎችን ለማዝናናት እና ለማስደሰት ክራስና ዋሽንት ይጫወቱ ነበር። በሰው ህይወት ውስጥ ስቃይ ስላለ ሰዎች ደስተኛ መሆን አለባቸው። የሰው ደስታ እግዚአብሔር መሆን አለበት, ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን ሲያጣ, ምስኪን እና ባዶ ነው. በዓለም ላይ ላሉ ሰዎች፣ ለመዝናናት ትልቅ ፍላጎት አላቸው። ያለ ክርስቶስ ሰው ደስታ የለውም; ስለዚህ ሰው መዝናኛ ፈላጊ ሆኖ ቀረ። ከቃየን ዘሮች መካከል፣ የነሐስ እና የብረት ዕቃዎችን የሚቀጥፉ ሰዎችም ነበሩ (ቁ. 22)። ይህ ራስን ለመከላከል እና ለደህንነት ሲባል ነበር። ሙዚቃ ለመዝናኛ ሲሆን የነሐስ እና የብረት መሳሪያዎች ደግሞ ለደህንነት ሲባል ነው። ቃየንም በድንኳን የሚቀመጡና ከብት የሚያረቡ ዘሮች ነበሩት (ቁ. 20)። ይህ ለኑሮ አስፈላጊ ነገሮች ነበር. የቃየን ዘሮች ከእግዚአብሔር የራቁ ህዝቦች ነበሩ, እና መዝናኛን, ደህንነትን እና የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን ያሳድዱ ነበር. ሰው እግዚአብሔርን ባጣ ቁጥር እነዚህን ነገሮች ያሳድዳል። ስለዚህ ክርስቶስ ን የሌላቸው ሰዎች ከመዝናኛ፣ ከደህንነት እና ከኑሮአቸው ጋር የተያያዙ ነገሮችን በመፈለግ, እየተሰቃዮ ይኖራሉ። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠው ህይወትና ደሰታ ክርስቶስን ብቻ ነው።
በክርስቶስ የሆናችሁ ክርስቶስን ተደሱቱ፣ ብሉት ጠ ጡት, አብ ደሰታችንን በልጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አደረገልን። ሌላ ደሰታ የለንም አልተሰጠንምና። የተሰጠን እንጂ ፈልገን የምናገኘው ደሰታ የለንም።

07/01/2025

ቤዛዬ
ክርስቶስ ቤዛዬ ሆነ፣ቤዠኝ ታደገኝ፣ በቅዱስ እና በክቡር ደሙ አጠበኝ። በክቡር ደሙ የታጠቡ ሁሉ በድፍረት ወደ እግዚአብሔር መምጣት ቻሉ ይችላሉም። እግዚአብሔር በኃጢያተኞች ላይ ሲፈርድ ከበጉ ደም በታች ያሉትን ሁሉ በጽድቅ ሊያልፋቸው ወደደ (ዘፀ. 12፡12-13፤ ሮሜ. 3፡25-26)። ሁሉም የተዋጁት ሙሉ ቤዛን አግኝተዋል። አንግዲህ እግዚአብሔር ሲያይ ሁሉን በክርስቶስ ነው የሚያየው። ዓይኑ የሚያየው ክርስቶስንነው። ክርስቶስ የታረደው በግ ነው; ደሙ በእግዚአብሔር ፊት የሰውን የኃጢአት መዝገብ ያስወግዳል። አንድ ሰው በክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ሲመጣ እግዚአብሔር ከእንግዲህ አይፈርድበትም፣ ምክንያቱም ክርስቶስ ሰውን ወክሎ የእግዚአብሔርን የጽድቅ መስፈርት አሟልቷልና። ቤዠን ታደገን። ሰውን ወክሎ የኃጢአትን ቅጣት ተሸክሟል። አንድ ጊዜ ሰው ክርስቶስ ካገኘ፣ ቤዛነት አለው። ኢየሱስ ሞቶለታልና ቤዛው ይሆንለታል። እግዚአብሔር ክርስቶስን ሲያይ ቤዛነትን ያያል። ሰለዚህም ኢየሱስ በአብ ፊት በድፍረት እንድቆም ያበቃኝ ፣ ከአብ ጋር ያሰታረቀኝ ፣ ፅድቄ ቅድስናዬ፣ ንፅህናዬና ቤዛዬም ሆነልኝ። ኢየሱስ ቤዛዬ፣ ቤዛዬ ኢየሱስ። ወድሀለሁ።

07/12/2024

Portland for JESUS.
Gospel Conference
All About JESUS
December 27-29. In Portland Orgon
Address: - 8048 SE Woodstock Blvd
Portland, OR 97206.
All are invited.

28/10/2024

አገልጋይ እና ተግባሩ
ቅዱስ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው መገልገል ፈልጎ አይመስለኝም ወይም አገልጋይ አስፈሎጎት ወይም ጎሎት አደለም። ለምን ሲባል እልፍ አ እላፋት መላእክት እንዲሁም ሌሎች ፍጥረታት ነበሩት። ግን እኛን ወይም አገልጋይ ተብዬዎችን የፈጠረን ወይም በልጁ በጌታችን ሞት በኩል የጠራን፣ ባህሪውንና ማንነቱን እንድንገልጥ ሰለወደደ ነው።
ሰለዚህ ስራችን ከእኛ የሚጠበቀው
እርሱን እለት እለት መፈለግ
እርሱን እለት እለት መውደድ
እርሱን እለት እለት ለፈጥረት በሕይወታችንና በኑሯችን መግለጥና መናገር እንዲሁም በትምህርቶችና በስብከቶች እርሱን ብቻ ማውራትና ማስወራት ይሆናል። የአገልጋይ ስራው ይኸው ነው።

አቤቱ እኔን በእውነትህ አፅናኝ
በፀጋህም ደግፈኝ። አሜን።

07/10/2024

መፀሀፍ ቅዱሳዊው ክርስትና
ከአለም ይለየሀል ከዚያም
ለእግዚአብሄር ተለይተህ እንድትኖር ያደርገሀል።

04/10/2024

እውነትን ያለ ፍቅር ስንናገር እንፈርዳለን ፣
ፍቅርን ያለእውነት ስናደርገው እንሸነግላለን ፣
ሁሌም ቢሆን እውነትን በፍቅር፣ ፍቅርንም በእውነት እንጠብቅ።

17/08/2024

ያማል፣ ልብን ይሰብራል፣
ምንስ ተብሎስ ይነገራል? ጆሮስ እንዴት ብሎ ችሎ ሊሰማ ይችላል? ሰው ሆይ ዝም አትበል። የአንድ ደቂቃ የወላጅ እናቷን የኢንተርቪው ቨድዮ ብቻ ሰማው መቀጠል አልቻልኩም። ይብቃኝ። ለመናገርም እንኳ ያማል። እኔ ልቤ በውስጤ ደከመችብኝ። አልቅሼ አልወጣ አለኝ፣ ሰው ሆይ ተነስ። ይህ እንግዳ ነገር ነው፣ አውሬ እንኳ ይህንን ተግባር አይፈጽምም። ሰው ሆይ ይህቺ ብላቴና ፍትህ ያስፈልጋታልና ተነስ፣ ፍትህ ከምድር ቢጠፈ ፣ የፍጥረት ሁሉ ባለቤት የሆነው የሁሉ ዳኛ ይነሳ። ጌታ ሆይ በምህረትህና በፍርድህ ተነስ። ሌላ ምን ልበል???

16/08/2024

ቅዱሳን ዘወትር በፀሎት በጌታ ፊት ለመሆን የምትወዱ ደግሞ በተለዪዮ ርእስ ጉዳይ በፀሎት እገዛ የምትሹ ወገኖች ከዚህ በታች ያለውን የቴሌግራም ኮድ በስልኮት ካሜራ እስካን በማድረግ ሊንኩን በመከተል body of Christ 24/7 virtual prayer room ይቀላቀሉ። ጌታ በምህረቱ በኩል ብዙዎችን እየጎበኘ፣ እንደፍቃዱ ልመናችንን እየሰማ ነው። እግዚአብሄር በዙፈኑ ላይነው ደግሞም በመካከላችን በስራ ላይ ነው። ከሰኞ አሰከ እሁድ ቀንና ለ ሊት የማይቋረጥ የፀሎት መስመር ነው። ተባረኩ።

14/08/2024

እኛ በክርስቶስ መኖራችን የሚለካው እርሱ( ክርስቶስ) ስፍራ አግኝቶ በእኛ በመኖሩ ነው።
የእኛ ሰዋዊ ሩጫዎቻችን ግን መንፈሳዊ ሽፋን ብንሰጣቸውም ሁልግዜ ጌታ በእኛ ደስ መሰኘቱን የሚያረጋግጡ አይሆኑም።
አገልግሎትም ቢሆን ጌታ በእኛ ሆኖ በመንፈሱ የሚሰራው እንጅ የእኛ የችሎታ ውጤት አይደለም። እኛ ለእርሱ ስንመች እሱ በእኛ የሚሰራውን ያውቃል። በእኔነት ልንቀድመው ስንሞክር ግን ያለፍሬ ኋላ እንቀራለን።

ስለዚህ ኢየሱስ ላይ ልናተኩር ይገባል። ከጋሪው ይልቅ ፈረሱን እናስቀድም!

13/08/2024

የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች አላማቸው ክርስቶስ ፣ እርሱንም በህይወታቸውና በትምህርታቸው ማሳየት ፣ መኖር እና እግዚአብሄርን ማስደሰት ነው። ይህን ለማድረግ አስፈላጊ ከሆነ በዐለም ላይ ያለውን ማንንም ሰው ከማስከፋት ወደ ሁዋላ አይሉም።

10/08/2024

የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር ውጭ ማንንም ወይም ምንም ነገር አይሹም።

07/08/2024

ስለ እውነት በእውነት
ክርስቶስን የወደደ
በቃ ራሱን ካደ።
አለቀ።

ራሱን ያልካደ በቃ
ክርስቶስን አልወደደ።
ተፈፀመ።

26/07/2024

ከሰፈር እንውጣ
ከሰፈር የዋለ ጥጃ አቁሞ ይቀውጣል ህዝብ ያስቀውጣል። ከተራራው የቆየ የላይኛውን ክብር አምጥቶ ትውልድን ይለውጣል። ከመንደር የዋለ የሚያስፈፅመው ህዝብ የሚፈልገውን ሲሆን አገልግሎቱም ህዝብ ለህዝብ ነው። ከተራራው የቆየ ግን ይዞ የሚወርደው የእግዚአብሔርን ፍላጎት ሲሆን የሚያገለግለውም ህዝብ የሚልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገውን ነው። ውሎና አዋዋላችን ኑሮና አገልግሎታችንን ይወስናል።
ሰፈር ሰፈር ያለ የመንደር አገልጋይ የእግዚአብሔር በአል ነው እያለ ጥጃ አቁሞ ትውልድ ያሴስናል። አምላክን በአምላክ እያዳበለ ህዝብን መረን ለቆ ያስገለሙታል። መንደርተኛው አሮን የእግዚአብሔር በአል ብሎ ህዝብ የሰበሰበው ምትክ ጥጃ አቁሞ ከግብፅ ያወጣ አምላክህ ይህ ነው እያለ ነበ...ር። በዚህም ሃገር ያስተጋባ ጩኸት የናኘበት በአል ተደርጓል። ድምፁ ግን ሰሚን ያደናገረ የድል ነሺ ይሁን የድል ተነሺ ያለየ ድብልቅልቅ ነበር። በዚህ አሮን በደገሰው ቀዋጭ በአል ላይ ተጥዶ እየፋነነ ያለውን ትውልድ ሰፈር ሰፈር ሲል የቆየ አገልጋይ ሃይ ሊለው አቅም የለውም። የመንደር አገልጋይ መረን የለቀቀውን ህዝብ መንደርተኛ አገልጋይ ሊታደገው አይችልምና!። ከተራራው የክብሩን መገለጥ ለብሰው የሚወርዱትን ሙሴዎች ይሻል። በነርሱ መገለጥ ሰው ሰው የሚለው ጌታ የሌለበት ቅወጣ እድሜው ያጥራል። እነዚህ ከተራራው የሚገለጡ የክብሩ አገልጋዮች ፈፅሞ መንፈሰ ቀዝቃዞች አይደሉም። ይህን የመንፈስ ምንዝርና አመቻምቸውና አቻችለው አያልፉም። ሲገለጡ ጥጃውን በቁጣ ይወጡበታል ይሰባብሩታል። በመሰባበርም አይቆሙም ምስሉን ፈጭተው ግተው ሳያጠጡህ አይመለሱም። ይህ ነው ለውጥ አምጪና ትውልድ ታዳጊ የልዑል የቅናቱ አገልጋይ!! አንተስ የቤቱ አገልጋይ ውሎህ ከወዴት ነው ከሰፈር ነው ወይስ ከተራራው? የሰፈር አገልጋይ ይቀውጣል የተራራው ይለውጣል። እባክህ ከሰፈር ውጣ ከተራራው ላይ ለውጥ አምጪው ክብር እየጠበቀህ ነውና ጉዞ ወደ ተራራው!!!

20/07/2024

Lord God, I pary that would give me ( us) a longing to know you and love you more and more each day.

10/07/2024

ኢየሱስን ፈላጊ ፣ አሳይም ጠፈ

በዚህ ዘመን በቤተ ክርስቲያን እየታየ ያለው አንዱ ችግር፥ ጌታ ኢየሱስን የሚፈልግ ምእመንና፤
እርሱን የሚያሳይ አገልጋይ ቍጥር እየተመናመነ መምጣቱ ነው።

06/07/2024

ድንቄም አገልግሎት

አገልግሎት ክርስቶስን ሸፍኖ ራስን ማሳየት ሳይሆን ራስን ስለእርሱ ጥሎ እርሱን በሁለንተና ማጉላት ነው። እርሱ በሰራው ነገርና ስራ ተንጠላጥሎ ለመታየት መሮጥ ትልቅ ውድቀት ና በደል ነው።
በአገልግሎታችን እኛን የእኛን ነገር ማሳያ ሳይሆን እኛ ዝቅ ብለን የምናገለግልበትና በእኛ ሁኔታ ክርስቶስ ይገለጥ ዘንድ የምንተጋበት እርሱን ብቻ የምናልቅበት መድረክ ነው። ያለ እርሱ እኛ ምንም ነን ይልቅ እርሱ በእኛ ልቆና ጎልቶ ይታይብን ዘንድ ራሳችንን አገልግሎታችንን በፊቱ እንጣል። አዎ እኛ ምንም አይደለንም። ዋጋችንም የሰበሰብነው ነገር ላይ ሳይሆን ሰለእርሱ በተውነው ነገር ላይ ነው።
ስለ እርሱ ሁሉን መተው
ስለ እርሱ ሁሉን ማጣት
ስለ እርሱ ሁሉን መሆን ።

አቤቱ እኔ ዝቅ ልበልልህ
ያን ጊዜ በእኔ ከፍ ትላለህና።

03/07/2024

ተወዛዋዥ ክርስቲያን
ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል ፣ማንበብና መፀለይ ሲያቆም፣ የቀኑ ወሬ፣ የሳምንቱ ክስተት ፣የወሩ ፊልም እና የሶሻል ሚዲያው ርእስ ፣ እንደ ጉድ ሲወዘውዘው ይከርማል፣ አንዳንዴም እየተወዘወዘ ይኖራል።
እና ወደ ቅዱስ ቃሉና ወደ ፀሎታችን እንመለስ ለማለት ነው። መወዝወዙ ይብቃነ። አንዳንዴ ለካ ፣ መወዛወዝ ፣ ለተወዛዋዡ አይታወቅም ለካ? በቃ ቃሉ እንዲመረምረን እንፍቀድለት።

አቤቱ እኔንም እርዳኝ ፣ አፅናኝም።

Want your school to be the top-listed School/college?

Videos (show all)

ኢየሱስን ፈላጊ ፣ አሳይም ጠፈበዚህ ዘመን በቤተ ክርስቲያን እየታየ ያለው አንዱ ችግር፥ ጌታ ኢየሱስን የሚፈልግ ምእመንና፤ እርሱን የሚያሳይ አገልጋይ ቍጥር እየተመናመነ መምጣቱ ነው።
መለየት እና መኮነን
እግዚአብሄር የሌለበት አምልኮ
worship
ንሰሃ ለምን?
አይመጥኑህም ( 1000x)ምንም ብሆንልህ ምንም ባደርግልህ        የሰጠኸኝን ሁሉ መልሼ ብሰጥህ         ሰውነቴን ለአንተ ቀድሼ ባቀርብም        ካረክልኝ ጋራ ከቶ አይመጥኑህም  ...
እንዳመንኩህ ልሙት
ንሰሃ
ብጹዕ  የተባረክ ሰው
ሳያይ ሞትን እንዳያይ ... ሰምዖን የእስራኤልን መጽናናት ጠባቂ ...
የእግዚአብሄር እንጀራ.  ዮሃንስ 6፡1-71
የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት

Telephone